#ለወንድማችን ጠሀ የተሰጠ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ:–
"የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ለናንተ ልትጠቀሙባቸው የሚገቡ ጥሩ እድሎች ናቸው። ለተንኮለኞችና ለጥመት ሰባኪዎች እንዳትተዋቸው።" (አሀምይየቱል ዐቂደቲ አስሶሒሐህ)
እናስተውል!
መስጂዶች በጥመት ቡድኖች እጅ ሆኑ ብለህ ተስፋ እንዳትቆርጥ። መስጂድ ተነጠቅን ብለህ እጅህን አጣጥፈህ አትቀመጥ። ጉልበተኞች አላንቀሳቀሱንም ብለህ አትርበትበት።
አስታውስ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በድብቅ ያስተማሩበትም ዘመን እንደነበር ከታሪክ ተማር። አማራጮች ሲጠቡ ወደ ሌላ አማራጭ ተመልከት። ዛሬ ላይ በእጃችን ከሚገኙ የማስተማሪያ መንገዶች ውስጥ እንደ ፌስቡክ፣ ዋትሳፕ፣ ቴሌግራም እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ።
በፍፁም ለአጥፊ ኃይላት እጅ እንዳትሰጥ። የሚጠበቅብህን ሃላፊነት ተወጣ። ሶሐቦች ሕይወታቸውን ሳይቀር እንደገበሩ አትርሳ። ስለሆነም እውነቱን ለማድረስ፣ ሀሰትን ለማርከስ ከቻልክ በእውቀትህ፣ ካለህ በገንዘብህ፣ በምትችለው ሁሉ ተንቀሳቀስ። ከፊትህ ያለው ወይ እጅግ የሚያስቋምጥ ጀነት ነው። ወይ ደግሞ አስፈሪ የሆነ እሳት። ካለህ አትሳሳ። የፈለግከውን ብትለፋ፣ የፈለግከውን ብትለግስ የቂን ብለህ ጀነትን ካለምክ ውድ አይደለም። ነገ የቂያማ ቀን እራሳቸውን ከጀሀነም ለማትረፍ ዱንያን ሁለት እጥፍ ቢሰጣቸው ቤዛ አድርገው ለማቅረብ የማያመነቱ ሰዎች ይኖራሉ። ያ ጊዜ ከመምጣቱ በፊት ዛሬን ተግተህ ስራ። ለዲንህ ታገል፣ ለሱንናህ ታገል፣ ለተውሒድ ታገል። የአጋር መቅለል፣ የጠላት መብዛት አያሳስብህ። መስጂዱን ብታጣ ባሉህ ሚዲያዎች ተጠቀም። ፌስቡክህ፣ ዋትሳብህ፣… ከሃዲው፣ አህባሹ፣ ኢኽዋኑ፣… የማይነጥቅህ መስጂድህ የዳዕዋ መድረክህ ናቸው።