አዲስ መረጃ እና ሰበር ዜና🇪🇹


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


➪ ፈጣን ፣ ተአማኒ የሆኑ ብቻ ሰበር ዜናዎች ከሀገርቤትም ከ ውጭም ይቀርቡበታል፡፡
● ከውጭ
● ከሀገር ውስጥ
● ሰበር ዜናዎች
● ተአማኒ ዜናዎች
● አዲስ መረጃዎች ያገኛሉ ፡፡

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ኡጋንዳ ይገኛሉ።

የኡጋንዳው ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ውይይቱ በምን በምን ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዳደረገ ፕሬዜዳንቱ በዝርዝር አልገለፁም።

ሙሴቬኒ ጠቅላይ ሚኒኒስትሩን እንኳን ደህና መጡ እንዳላቸውም ገልፀዋል።


©tikvahethiopia

@Ethio_addis_Mereja


አሜሪካ ከካቡሉ ጥቃት ጋር በተያያዘ የአጸፋ እርምጃ ወሰደች

አሜሪካ በአፍጋኒስታን ካቡል ሃሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ የአጸፋ እርምጃ ወሰደች፡፡
በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የታገዘው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ ጥቃቱን አቀናብሯል ባለችውና ለጥቃቱም ኃላፊነቱን በወሰደው የአይ ኤስ አይኤስ የአፍጋኒስታን ክንፍ (ISIS-Khorasan) ላይ የተወሰደ ነው፡፡

በምስራቃዊ ናንጋርሃር ክልል በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ዒላናዬ ነበር ያለችውን አንድን ሰው መግደሏን አሜሪካ አስታውቃለች፡፡ ጥቃቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለካቡሉ ጥቃት የአጸፋ ምላሽን እንደሚሰጡ በዛቱ በማግስቱ የተፈጸመ ነው፡፡ በሃሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና በአቅራቢያው በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ በተፈጸመው ጥቃት 13 የአሜሪካ ሰራተኞች እና 170 አፍጋናውያን መሞታቸው የሚታወስ ነው፡፡


@ethio_Addis_Mereja


Congratulations !

የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዛሬ ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።

#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 726 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለ13ኛ ጊዜ ባካሄደው የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ስርዐት 5 ሺህ 726 ተማሪዎችን በመጀመሪያ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 448ቱ በ2ኛ ዲግሪ እንዲሁም ሰባቱ በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆኑ ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 31ዱ ሴቶች ናቸው።

#ወራቤ_ዩኒቨርሲቲ

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 132 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

#ኦዳቡልቱም_ዩኒቨርሲቲ

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 354 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ባካሄደው 3ኛ ዙር የምረቃ ስነስርዐት የተመረቁ ተማሪዎች፤ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች ስልጠናቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎች አስመርቋል።

3ኛ ዙር ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲው አራት ኮሌጆች በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብሮች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው። ዛሬ ከተመረቁት ተማሪዎች 428ቱ ሴቶች ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

የተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።

ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ፣ ግሬት ኮሌጅና ኤልኤም ኢንተርናሽናል የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።

@ETHIO_ADDIS_MEREJA


ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ የመፍታት አቅም ስላላት የውስጥ ጉዳይዋ ተደርጎ ሊታይ እንደሚገባ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት አመለከቱ !

በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ በመከረው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ከቋሚና ተለዋጭ አባል አገራት ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷው አቅም ልትፈታው ይገባል ብለዋል።

በተለይ ሩሲያ እና ህንድ አሸባሪው ህወሓት የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ተላልፎ በአጎራባች የአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ የፈጸመውን ግፍ አውግዘዋል።

ሩስያ በተወካዩዋ በኩል "ሰኔ ላይ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠና አቅም ያለው መንግስት በኢትዮጵያ ስላለ ችግሩን ራሳቸው ኢትዮጵያውያን ይፈቱታል" ብላለች።

ቻይና በበኩሏ"በሰብአዊ እርዳታ ስም  የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመጣስ መሞከርን ቻይና በፍፁም አትቀበለውም፤የአለም ሀገራት በሙሉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን ሊሆኑ ይገባል፤ በእርዳታ ስም ችግር ለመፍጠር የሚሞክሩ ቡድኖች የተመድን ህግ ሊያከብሩ ይገባል" በማለት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንደምትቆም አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ያስታወቀችው ህንድ ደግሞ፣ "ችግሩን ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት በቂ ነው" ብላለች።

ኬንያም  ኢትዮጵያ ላይ ለመጣል የሚታሰብ ምንም አይነት ማዕቀብ እንደማትደግፍ አመልክታለች።

በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሞከሩት የአሜሪካና እንግሊዝ  ሀሳብ ኢትዮጵያ ችግሯን ለመፍታት በምታደርገው ጥረት የውጭ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም በሚል በሌሎች አገራት በተነሱ ሀሳቦች ተቃውሞ ቀርቦበታል።

@ETHIO_ADDIS_MEREJA


ክህደት የፈጸሙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በጽኑ እስራት ተቀጡ፡፡

በሀገርና በሀገሪቱ ሰራዊት ላይ ክህደት በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እስከ 18 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ዉሳኔ ተላለፈባቸዉ፡፡የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ የጦር ፍርድ ቤት ባስቻለው ወታደራዊ ፍርድ ቤት አስር ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በሰሩት ወንጀል መጠን የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከሀገር አፍራሽ አሸባሪዎች ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር የሀገር ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል፣ ክህደት በመፈፀም አሸባሪዎቹን የህወሓት ጁንታ ለመቀላቀል ማሴር፣ ለሸኔ መረጃ ማቀበል፣ ከግዳጅ ቀጠና በመሸሽ የወገን ጦርን ለአደጋ ማጋለጥ፣ ያለ በቂ ምክንያት ሲቪሎችን መግደል፣ የበላይን ትዕዛዝ ችላ በማለት ለንፁሐን ሞት ምክንያት መሆንና የመንግሥትና የህዝብን ወታደራዊ ንብረትን ይዞ ለመሸሽ ሙከራ ማድረግ የሚሉ ክሶች ዋነኛ ጭብጥ ሆኖ መቅረቡን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ሲመረምር ቆይቶ ተከሳሾች እራሳቸውን መከላከል ባለመቻላው የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሰረት፡-
1. ሻለቃ ክፍሌ ካሳይ በ17 አመት ፅኑ እስራት፣

2. ኮሎኔል ክፍሌ ፍሰሃዬ በ14 ከ 2 ወር ፅኑ እስራት፣
3. ሀምሳ አለቃ መብራቱ ጥላዬ በ18 አመት ፅኑ እስራት፣
4. መሰረታዊ ወታደር መኮንን ክንፈ በ13 አመት ፅኑ እስራት፣
5. ሀምሳ አለቃ ፈረደ ይባስ በ11 አመት እስራት፣
6. ምክትል አስር አለቃ ሀጎስ በርሄ በ11 አመት ፅኑ እስራት፣
7. ምክትል ክፍሌ ንጉስ በ9 አመት ፅኑ እስራት፣
8. ኮሎኔል ካሱ ሀብቱ በ11 አመት ከ2 ወር፣
9. ኮሎኔል ሀጎስ አሰፋ በ8 አመት ፅኑ እስራት እና
10. ሌተናል ኮሎኔል ሀይላይ ገብሩ በ10 አመት ከ2 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡በቀጣይም ከ150 በሚበልጡ ተጠርጣሪዎች ላይ የፍርድ ሂደት እንደሚታይ ተገልጿል፡፡

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@ethio_Addis_Mereja


ህወሓት በፈጸመው ጥቃት በአፋርና አማራ ክልል ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል!

አሸባሪው ህወሓት በፈጸመው ጥቃት በአፋርና አማራ ክልል ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሰላም ሚኒስትር እና የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባሪያ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል በሰብአዊ ድጋፍ እየተንቀሳቀሱ ላሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አጋር አካላት በሰብአዊና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅትመንግስት ወደ ትግራይ የሚያስገቡ አራት መንገዶችን ሲጠቀም የነበረ ቢሆንም ህወሓት በከፈተው ጥቃት መስመሮቹ መዘጋታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈም መንግስት በእነዚህ መንገዶች ያደርስ የነበረው ሰብአዊ ድጋፍ እንዲቋረጥና በአካባቢው ያለው ሰብአዊ ቀውስ እንዲባባስ ማድረጉን አስረድተዋል።

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ፣ በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል ወደ ትግራይ ክልል የሚያስገባ መስመር ቢኖርም አሸባሪው ቡድን ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችንና ንጹሃን ዜጎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየፈጸመ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሰብአዊ ድጋፍ የማድረስ ሂደቱን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል። እስካሁን ከህልውና ዘመቻው ወዲህ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ለሰብአዊ ቀውስ መዳረጋቸውን አንስተዋል።

በአማራ ክልል ብቻ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ ጠቁመው፥ አሁን ላይ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ነው የተናገሩት። መንግስት በትግራይ ክልል በ47 ወረዳዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት አድርጓልም ብለዋል ሚኒስትሯ። ከዚህ ባለፈም እስካሁን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ 321 ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባታቸውን ጠቁመዋል።



T.ME/ETHIO_ADDIS_MEREJA
T.ME/ETHIO_ADDIS_MEREJA


#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ1 ሺህ 500 በላይ ግለሰቦች በሕገ-ወጥ መንገድ በቤት ማኅበር ተደራጅተው እንደተገኙ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።

በደብረ ብርሃን ከተማ በተለምዶ 633ቱ የቤት ኅብረት ስራ ማኅበራት በሚል ከተደራጁና ዕውቅና ከተሰጣቸው ማህበራት ውስጥ ከ1 ሺህ 500 በላይ ግለሰቦች በህገወጥ መንገድ ተደራጅተው ተገኝተዋል።

ይህን የተገለፀው የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ም/ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ ከከተማና ከቀበሌ አመራሮች ጋር በማኅበራቱ አደረጃጀት ዙሪያ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው።

633ቱ ማህበራት ሲደራጁ 73 የተለያዩ ቦታዎቸ ክፍት የነበሩ ቢሆንም በ65ቱ ክፍት ቦታዎች 1 ሺህ 408 ሰዎች በህገወጥ መንገድ በመደራጀታቸው የከተማው ከንቲባ ኮሚቴ ማህበራቱ ሙሉ በሙሉ እዲሰረዙ መወሰኑ ተገልጿል።

በቀሪ 560 ማህበራት ውስጥ 110 ግለሰቦች በህገወጥ መንገድ ተደራጅተው ተገኝተዋል ያሉት ከንቲባው እነዚህ ግለሰቦች ማሕበራቱ ሳይፈርሱ ግለሰቦችን ብቻ እንዲወጡ መወሰኑን አስረድተዋል።

አሁንም መረጃ የማጣራት ስራው ቀጣይነት እዳለው የገለፁት ከንቲባው በዚህ ህገወጥ ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በህግ ለመጠየቅ ይሰራል ብለዋል።

በውይይቱ ላይ በማኅበራት ከተደራጁ ግለሰቦች መካከል ፦
- በከተማዋ የማይኖሩ ፣
- መሸኛ ያላመጡ ፣
- ሐሰተኛ የጋብቻ ፍቺ የፈጸሙ ፣
- ሐሰተኛ መሸኛ ያመጡ እና ባልተሟላ መረጃ የተደራጁ መኖራቸው ተመልክቷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት የተሳተፉ አካላት ፖለቲካዊ ፣ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ ርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል።

መረጃው ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የተገኘ ነው።


@ETHIO_ADDIS_MEREJA


“አሸባሪውን ቡድን በቅርቡ ግብዓተ መሬቱ ይፈፀማል” ሴት የመከላከያ የሠራዊት አባላት

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሴት የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የአሸባሪ ቡድኑን ግብዓተ መሬት ካልፈፀመን አንመለስም፤ ይህም በቅርቡ ይሆናል ብለዋል፡፡ የደቡብ እዝ ሴት የሠራዊት አባላት ጠላትን በመደምሰስ ላይ ይገኛሉ፡፡ አስር አለቃ ሰላማዊት ኀይሉ በግንባር ካገኘናቸዉ ሴት የመከላካያ ሠራዊት አባላት መካከል አንዷ ናት፡፡ ጀግንነት የአባቶቻችን ነዉ የምትለዉ አስር አለቃ ሰላማዊት ጠላትን ለመደምሰስ ከመቸዉም ጊዜ በላይ [...]

☞መረጃው የአሚኮ ነው፡፡

@ETHIO_ADDIS_MEREJA
@ETHIO_ADDIS_MEREJA


ሰበር ዜና❗️

ምስራቅ ወለጋ ዉስጥ ከ200 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ40 ሺሕ ያሕል መፈናቀላቸው ተሰማ!

በኦሮሚያ መስተዳድር ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ኪራሙ ወረዳ ዉስጥ «የኦነግ-ሸኔ ሸማቂዎች» ናቸዉ የተባሉ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች መግደላቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች አስታወቁ። ከ40 ሺሕ በላይ ነዋሪም ተፈናቅሏል።በስልክ ያነጋገርናቸዉ የዓይን ምስክሮች እንዳሉት ታጣቂዎቹ ካለፈዉ ሳምንት ሮብ ጀምሮ በወረዳዉ የሚገኙ 6 ቀበሌዎችን ወርረዉ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ነዋሪዎችን ልጅ ካዋቂ፣ ሴት ከወንድ ሳይለዩ በጥይትና በገጀራ ገድለዋቸዋል።

ከጥቃቱ ያመለጡ አንድ ዓይን ምስክር እንዳሉት አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ከየቤታቸዉ እንዳይወጡ፣ከወጡም ዉጪ እንዳያመሹ የሚያስጠነቅቅ ወረቀት ባለፈዉ ነሐሴ 11 በየሥፍራዉ ተለጥፎ ነበር።«ነዋሪዉ ላንድ ሳምንት ያክል በየቤቱ ተሸሽጎ ከሰነበተ በኋላ የአካባቢዉ ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያዉን እየገነጠሉ ስለጣሉት ነዋሪዎችም ሠላም ነዉ ብለዉ ከየቤታቸዉ መዉጣት ጀመሩ፣ወዲያዉ ግን ታጣቂዎች አካባቢዉን ወርረዉ ከየቤቱ የወጣዉን ገደሉት፤ ከብቱን ዘረፉት፤ ሰዉ እቤት ዉስጥ ተቀምጦ የቤቱን ጣራ እየነቀሉ ወሰዱት።»ይላሉ።የዓይን ምስክሩ እንዳሉት በአካባቢዉ ልዩ ኃይል ከገባ በሕዋላ ከትናንት በስቲያ ብቻ ነዋሪዎች 72 ሰዉ ቀብረዋል።

ስለጥቃቱና ስለደረሰዉ ጉዳት ለማረጋገጥ ስልክ ከደወልናላቸዉ የምሥራቅ ወለጋ ዞንና የኦሮሚያ ባለስልጣናት መካከል አንዱ ማንነታችንን ከጠየቁ በኋላ «ሥራ ላይ ነኝ» በማለት ስልኩን ዘግተዋል።

የጀርመን ድምፅ| DW
@ETHIO_ADDIS_MEREJA
@ETHIO_ADDIS_MEREJA


''ቱኒዚያ በድጋሜ ለተባበሩት የፀጥታው ምክር ቤት ለግብጽ ተገቢ ያልሆነ ድጋፍ ለማድረግ እየተዘጋጀች ነው'' - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

ቱኒዚያ ድጋሚ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የግብፅን ሀሳብ ብቻ የሚደግፍ የውሳኔ ሀሳብ ለማቅረብ እየተዘጋጀች በመሆኑ አፍራሽ አካሔዷን ለመቀልበስ የላይኛው የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት በጋር መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ይህን ያሉት ከላይኛው የናይል ተፋሰስ አባል ሐገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

የላይኛው ተፋሰስ አገራት አምባሳደሮችም በበኩላቸው በቀረቡት ሃሳብ ላይ በመንተራስ ድንበር ተሻጋሪ ሃብቶችን ለጋራ ልማት ለማዋል የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ እንዲሁም የአፍሪካን ጉዳይ በአፍሪካዊያን መፍታት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ቱኒዚያ ለተባበሩት የፀጥታው ምክር ቤት ለግብጽ ተገቢ ያልሆነ ድጋፍ ለማድረግ ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ቢደረግባትም በድጋሚ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጓን አንስተው፣ ይህ ውሳኔ ቢወሰን የሁሉም የላኛው ተፋሰስ አገራት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችልና ይህን ሃሳብ ለመቀልበስ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን የቱኒዚያ አካሄድ በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን የሶስትዮሽ ድርድር ጥረት የሚያደናቅፍ መሆኑን ገልጸው፣ አገራቱ ኒውዮርክ ለሚገኙት ሚሲዮኖቻቸው ይህንኑ እንዲገልጹላቸው ጠይቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ ጽ/ቤትንጠቅሶ የዘገበው Tikvah ነው።

@ETHIO_ADDIS_MEREJA
@ETHIO_ADDIS_MEREJA


ወደ ውጭ ከተላከ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት 9 መቶ 27 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርቶችን በከፍተኛ መጠን የላኩ ድርጅቶችን እውቅናና ሽልማት እየሠጠ ነው።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ባለፈው በጀት ዓመት በተሰሩ ሥራዎች ውጤት ተመዝግቧል ተብሏል። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ እንደተናገሩት ከአርሦ አደሩ እስከ ላኪው ድረሥ ውጤታማ ሥራ በመሠራቱ 927 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በበጀት ዓመቱ በተለይም በሥፔሻሊቲ ቡና ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሠራቱ፣ የቡናን ዝቅተኛ ዋጋን በማሥቀመጥ የመደራደር አቅምን በማሣደግ፣ እንዲሁም በቴክኖሎጅ ማዘመን ዘርፍ ትልቅ ሥራ መሠራቱን አሥታውቀዋል።

በሌላ በኩል የሀገሪቱን የቡና መለያ/Brand/ በማዘጋጀት በሀገር ውስጥ የተመዘገበ ሢሆን በአውሮፓ፣ በሠሜንና ደቡብ አሜሪካ እና በሌሎችም ክፍላተ ዓለማት ለማሥመዝገብ እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል።
T.me/ethio_Addis_mereja
T.me/ethio_Addis_mereja


የኤርትራ ወታደሮች ሰሞኑን በብዛት ወደ ትግራይ ክልል እየገቡ መሆኑ እንዳሳሰባቸው አሜሪካ እና አውሮፓ ኅብረት መግለጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ብዛት ያላቸው የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ እየገቡ ነው ሲሉ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ትናንት ተናግረዋል። ሑመራ እና አዲ ጎሹ በተባሉ የምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች የኤርትራ ወታደሮች ምሽግ እየያዙ፣ ታንኮችን እያሰለፉ እና መድፎችን እየተከሉ እንደሆነ ሮይተርስ አየሁት ባለው የአውሮፓ ኅብረት የውስጥ ማስታዎሻ ላይ ተጠቅሷል።

[Wazema]
@ethio_Addis_Mereja


አሜሪካ በኤርትራ ጦር አዛዥ ላይ ማዕቀብ ጣለች።

አሜሪካ የኤርትራ ጦር በትግራይ ክልል ፈጽሟል ባለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት በጦሩ ዋና አዛዥ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች።

ማዕቀቡ በኤርትራ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ የተጣለ ነው፡፡

ማዕቀቡን የተጣለው በአሜሪካ የፌዴራል ግምጃ ቤት (ትሬዠሪ) በኩል ሲሆን አዛዡ በአሜሪካ ያላቸው ሀብት እንዲታገድ እንደተወሰነ ግምጃ ቤቱ በድረገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

አሜሪካ በጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ የሚመራው የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽሟል፤ ሴቶችን ደፍሯል እንዲሁም ወጣቶችን እና ንጹሀን ዜጎችን ቤት ለቤት በመግባት ገድሏል ስትል ከሳለች።

የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ካደረገ በኋላም ተመልሶ ወደ ትግራይ ክልል ገብቷል የሚለው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ጦሩ በአስቸኳይ ወደ ኤርትራ እንዲመለስ ጠይቋል።

ውሳኔው አሜሪካ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ላላት ቁርጠኝነት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችልም ነው ግምጃ ቤቱ ያስታወቀው።

አሁንም ጦርነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው የሚለው የህ ተቋም በቀጠለው ግጭት ምክንያት እርዳታ የሰብአዊ መብት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ማድረስ ባለመቻሉ ሁሉም አካላት ግጭቱን እንዲያስቆሙ ጠይቋል።

ኤርትራ ማዕቀቡን በተመለከተ እስካሁን የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡

የመረጃ ባለቤት፦ አል አይን ኒውስ

@ETHIO_ADDIS_MEREJA
@ETHIO_ADDIS_MEREJA


#BREAKING

ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ቀን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ።

ድምፅ አሰጣጡ የሚከናወነው ፦
- በሶማሌ ክልል፣
- በሐረሪ ክልል
- በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የሚሆን ሲሆን የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔም በተመሳሳይ ቀን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከናወን ይሆናል ተብሏል።

በቀሪ የምርጫ ክልሎች ላይ የሚኖረውን ሂደት አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ መረጃዎችን እሰጣለሁ ብሏል።

* ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ምሽት ያሰራጨው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@ETHIO_ADDIS_MEREJA


#FDREDefenseForce

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በህወሓት ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን ማስለቀቁን አስታወቀ።

የመከላከያ ሰራዊት ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የአማራ ሚሊሻ ጋር በመሆን በወሰደው እርምጃ፦ ጋሳይ፣ ክምር ድንጋይ፣ ጎብጎብ፣ ሳሊና ንፋስ መውጫ ነፃ ማውጣቱን ገልጿል።

የንፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች ህወሓት በንፋስ መውጫ ከተማ ንፁሃንን መግደሉንና በርካታ ውድመት ማድረሱን የተናገሩ ሲሆን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደከተማቸው ሲገባ አቀባበል አድርገዋል።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን ፤ ከሰሞኑን ህወሓት ህዝቡን በጣም እንደጎዳው፤ የቀረ ነገር ሳይኖር ዘርፊያ እንደፈፀመ ገልፀው፥ "ህዝባችን እንዲህ ያለ ወራዳ ተግባር ማየቱ የሚያሳዝን ነው፤ ነገር ግን አሁን ላይ ቡድኑ ዋጋውን እያገኘ ነው" ብለዋል።

ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ፥ "ህወሓት በወረራ የያዛቸውን ቦታዎች በሙሉ የማስለቀቅ እና የማፅዳት ስራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ከመኪና ወርዶ እየተበታተነ ነው እሱን የመልቀም ስራ እየተሰራ ነው፤ የሚሸሽበትም መንገድ ተዘግቷል፤ ትግራይ ውስጥ ያየውን ጉድ እዚህም ያየዋል፤ እዚህ ገብቶ መውጣት የሚባል ነገር እንደሌለ ያየዋል" ብለዋል።

አዛዡ ፥ ህወሃት ስርዓት መቀየር ነው ፍላጎቴ ይላል እንጂ ተግባሩ ሀገር ማፍረስ እና ሀገር ማውደም ነው ፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው የማፍረስ ምልክቱም ህዝቡን ምን እያረገው እንዳለ ማየት በቂ ነው ፤ የከተማውን ህዝብ ጠይቁ ምን አድርጓቸው እንደሄደ፤ እነሱ የስርዓት አራማጅ አይደሉም ፤ ድሆች ናቸው ፤ ከድሆቹ አፍ ነጥቆ ሽሮ ሳይቀር እየጫነ እየወሰደ ያለው" ሲሉ አስረድተዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/ENDF-08-23


የማይካድራ ጭፍጨፋ ከባድ የህሊና ቁስል ጥሎብን አልፏል !

አሸባሪው ህወሃት በማይካድራ የፈፀመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከባድ የህሊና ቁስል ጥሎብን አልፏል ሲሉ የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

በዓለም ላይ ለሰው ልጆች መብት የቆሙ ሁሉ ድርጊቱን በፅኑ በማውገዝ የህወሃትን የሽብር ቡድን ተጠያቂ እንዲያደርጉላቸውም ጠይቀዋል።

“በህይወት ዘመኔ በኢትዮጵያ በሰው ልጆች ላይ እንዲህ አይነት ዘግናኝ ወንጀል ሲፈፀም የተመለከትኩበት አጋጣሚ ማይካድራ ላይ ነው” ያሉት ወይዘሮ ብርቄ እሸቴ፥ የህወሓት አሸባሪ ቡድን ማይካድራ ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ ዓለም በሚገባው ልክ እንዳላወገዘው ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ በሰው ልጆች ላይ የማይታሰብ ወንጀል በመፈፀም የጭካኔ ጥጉን ማይካድራ ላይ አሳይቷል” ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ትንሳኤ ሙላው ናቸው።

ቡድኑ ያደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ በሁሉም አዕምሮ ውስጥ እያቃጨለ ያለ ታሪክ የማይረሳው የህሊና ቁስል እንደሆነ ጠቅሰዋል።

“የማይካድራን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ዓለም በሚገባው ልክ አውግዞ ወንጀለኛውን ተጠያቂ ለማድረግ አልጣረም” ያለችው ደግሞ እናንየ አሻግሬ ነች።

አሸባሪው አሁንም የአገር ክህደት በመፈፀም ኢትዮጵያን ለመበታተን እየሰራ ቢሆንም በሁሉም የጋራ ክንድ እንደሚመከት ገልጻለች።

የማይካድራ ነዋሪ በህወሃት የአገዛዝ ዘመን ሲረሸን፣ ሲሰቀል፣ ሲንገላታና በወጣበት እንዲቀር ሲደረግ መቆየቱን አስተያየት ሰጭዎቹ አስታውሰዋል።

በጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ማይካድራ ላይ በንፁሃን ላይ የፈፀመው ጅምላ ጭፍጨፋ ደግሞ የሽብር ቡድኑ የክፋቱን ጥግ ለሰው ልጆች ሁሉ ያሳየበት እንደሆነ ተናግረዋል።

ድርጊቱ በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይጠበቅ ጭካኔ ቢሆንም በዚህ ልክ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የድርጊቱን ፈጻሚ አሸባሪው ህወሃትን በቅጡ እንዳላወገዘው ገልጸዋል።

የማይካድራ ነዋሪዎች አሸባሪው ዳግም እንዳያንሰራራ እንደሚመክቱ አረጋግጠው፤ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍም ገልጸዋል።

ለሰራዊቱ ስንቅ በማዘጋጀት አጋርነታቸውንም በተግባር አሳይተዋል።

የአሸባሪው የህወሃት ቡድን እስከሚጠፋ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠው፤ የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታ በንቃት እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ምንጭ :- ኢዜአ

@ethio_Addis_Mereja
@ethio_Addis_Mereja


ወደ አፋር ሰርጎ የገባውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ‼️

ወደ አፋር ክልል ሰርጎ የገባውን የህወሓት አሸባሪ ቡድን ከገባበት ሳይወጣ ለመደምሰስ የጸጥታ ሃይሉ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የአፋር ክልል ልዩ ሃይል ምክትል አዛዥ ኮማንደር መሃመድ ሰናይ ገለጹ።

የአፋር ክልል ልዩ ሃይል ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር በመቀናጀት ወደ ክልሉ ሰርጎ የገባውን የህወሓት አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብላዋል፡፡

በእስካሁኑ የህልውና ዘመቻ በርካታ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች ሲደመሰሱ የተማረኩም እንዳሉ ጠቅስዋል።

ቡድኑ ከባድ መሣሪያ ህዝቡ ላይ በመተኮስ በበርካታ ንፁሃን ላይ የፈፀመውን ድርጊት አስታውሰው÷ አሁን ላይ የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአፋር ክልል ልዩ ሃይል ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት የጥፋት ቡድኑን በመመከት ወደ ኋላ እንዲሸሽ አድርጓልም ነው ያሉት፡፡

በክልሉ አራት ወረዳዎች ሰርጎ የገባውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ የተቀናጀ ዘመቻ እየተከናወነ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ጋሊኮማ በተባለ ቦታ ጥቃት ያደረሱ የአሸባሪ ቡድኑ ታጣቂዎች ብዙዎቹ መደምሰሳቸውን ምክትል አዛዡ ተናግረዋል፡፡

አሸባሪው ኪልባቲ ረሱ በራህሌ ወረዳ ሰሞኑን ጥቃት መፈጸሙን አስታውሰው÷ በአጸፋው የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድበት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@ethio_Addis_Mereja
@ethio_Addis_Mereja


#Alert🚨

በሀገራችን በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ ነው።

ዛሬ ምሽት ዘግይቶ በወጣው የጤና ሚኒስቴር እና የአትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት መሰረት በ24 ሰዓት 1,282 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

እነዚህ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተለዩት ከተደረገው 9,017 የላብራቶሪ ምርመራ ነው።

በሌላ በኩል በበሽታው ተይዘው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት 14 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥርም 478 ደርሷል።


ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊላክ የነበር 2 ሺህ 900 ጥይት ተያዘ።

በአንድ የሲሚንቶ ማጓጓዣ ከባድ ተሽከርካሪ በድብቅ ተጭኖ ከደብረ ብርሃን በአዲስ አበባ በኩል ወደ ሰሜን ሸዋ ሊጓጓዝ የነበረ 2 ሺህ 900 የሚሆን ጥይት ከአዲስ አበባ ከተማ ሳይወጣ በተደረገበት ልዩ ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋሉን የደኅንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ገልጿል።

ጥይቶቹ የክላሽንኮቭ መሳሪያ መሆናቸውን ያመለከተው መግለጫው፤ ለሸኔ የሽብር ቡድን እንዲደርስ ታስቦ ሲጓጓዝ መያዙንም አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ ስሚንቶ ከጫነ ከባድ ተሸከርካሪ በተለምዶ ደርብራተር ተብሎ ከሚጠራው የውስጥ አካል ውስጥ ጥይቶችን ደብቀው በመጫን ለማሳለፍ ሲሞክሩ አዲስ አበባ ሲደርሱ፤ ከመነሻው በደኅንነትና በጸጥታ አካላት ጥብቅ ክትትል ሲደርግባቸው ስለነበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ብሏል መግለጫው፡፡

የወንጀል ድርጊቱ ተወናያን የነበረው ሹፌር እንደተደረስበት ሲያውቅ አደጋ በማድረስ ለጊዜው የተሰወረ ቢሆንም፤ በክትትል ስር በመሆኑ እንደሚያዝ ያስታወቀው መግለጫው፤ ተሽከርካሪውን በፒክ አፕ መኪና ሲከተሉት የነበሩት ሌሎች የወንጅሉ አራት ተጠርጣሪዎች ግን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል።

የሸኔ የሽብር ተግባር መፈጸሚያ የሚውሉ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲጓጓዙ በደኅንነትና በጸጥታ አካላት ጥብቅ ክትልልና ፍተሻ በተደጋጋሚ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የፌደራል የደኅንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኀይል መግለጫው አስታውሷል።

http://T.me/ETHIO_ADDIS_MEREJA



20 last posts shown.

378

subscribers
Channel statistics