Forward from: قَنَاةُ الدَّعْوَةُ السَّلَفِيَّةُ
ውድእህቶቼ እራሳችሁን አትርሱ። ከሀገር የወጣችሁት የተሰደዳችሁት ባል አጥታችሁ አይደለም።የወጣችሁት እንጀራ ፍለጋ ነው። ከፋም ደላ የሰው ሀገር የሰው ነው። ህልማችሁ ቋጥሮ ወደ ሀገር ለመመለስ እንጂ በልቶ ለመውዛት፣ ለብሶ ለመድመቅ አይደለም። ለዚህ ደግሞ ብልጥ መሆን ያስፈልጋል። መስራቱን ቻሉበት። መያዙንም ቻሉበት። ለቤተሰብ ስትልኩም አቅማችሁንም፣ ኑሯቸውንም፣ ሁኔታቸውንም እያገናዘባችሁ ይሁን። ለጎረምሳ ጫት መቃሚያና መንሸራሸሪያ አትላኩ። በዚህ ወንድሞቻችሁን ታበላሻላችሁ እንጂ አትጠቅሟቸውም። ገንዘባችሁንም አጥታችሁ ወንጀለኛም ትሆናላችሁ። ባጭሩ የምትሰሩትን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ ለማዋል ተጣጣሩ። ባዶ እጃችሁን ላለመግባት በተቻላችሁ ተጠንቀቁ። ችግር መጥፎ ነው። ቤተሰብ እንኳን እንዲገፋችሁ ያደርጋል። አገራችን ለባዶ እጅ ቀርቶ ለያዘም እየከበደ ነው።
https://t.me/deawetu_selefiyya_Merssa
https://t.me/deawetu_selefiyya_Merssa
https://t.me/deawetu_selefiyya_Merssa
https://t.me/deawetu_selefiyya_Merssa