✞
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ ✞
ንሴብሖ ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ(፪)
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
ለምስጋና ቀሰቀስከኝ በእኩለ ሌሊት
በተመስጦ ስለፍቅርህ ልጀምር ማኅሌት
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
ስመለከት ወደ ሰማይ በጨረቃ ብርሃን
ግርማ ለብሶ አስገረመኝ የአምላኬ ዙፋን
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን በመንፈስ እንዘምር
እልል እንበል በምስጋና ጸጋውን እንጀምር
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
አእዋፉ በማለዳ መዝሙር ሲጀምሩ
በቋንቋቸው የአንተን ክብር በምስጢር ሲያወሩ
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
ከበሮ ሆይ ጸናልናል ሆይ ለምስጋና ተነስ
በማለዳ ለጌታችን ምስጋና እናድርስ
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
✥•┈•●◉
༒ ናሁ ሰማን-ዜማ
༒◉●•┈•✥
╭✥◉●•┈•✨◍❀◍●✨◉●•┈•✥╮
/╭✧✞
@Nahuseman256✞ ✧╮\
\╰✧ ✞
@Nahuseman256 ✞✧
╯/
╰✥◉●•┈•🌿◍❀◍●🌿◉●•┈•✥
╯