በባምባሲ ወረዳ በጸጥታ አካላትና በህብረተሰቡ መካከል በተፈጠረ ያለመግባባት የሶስት ግለሰቦች ህይወት አለፈ!‼️
በባምባሲ ወረዳ በጸጥታ አካላትና በህብረተሰቡ መካከል በተፈጠረ ያለመግባባት የሶስት ግለሰቦች ህይወት ማለፉን የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ያሲር አብዱልማጅድ እንደገለጹት፥ ችግሩ የተከሰተው የጸጥታ አካላቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማስተግበር ስራ ላይ እንዳሉ ነው።የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ እንዳስረዱት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተጣለ ወዲህ የፖሊስ አካላት ህብረተሰቡ ተራርቆ ከበሽታው እራሱን እንዲጠብቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፥ ችግሩ በተከሰተበት በመንደር 47፣ 48 ና 46 ቀበሌዎች መካከል የሚገኘው የገበያ ቦታ በሽታው እስኪገታ ድረስ እንዲቆም ከህዝቡ ጋር ውይይት የተደረገ ቢሆንም መልሰው ጠዋት መገበያየቱን እንደቀጠሉበት ተናግረዋል።
ይህንንም ችግሩን ለመፍታት የወረዳው ፖሊስ ተልኮ ሙከራ ቢደረግም ከአቅም በላይ ሆኖ ስለቀጠለ በቀን 26/09/2012 ዓ/ም የወረዳና የአሶሳ ዞን አመራሮች በቦታው ተገኝተው ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅትም ገበያችንን በኮሮና በሽታ ሰበብ ለሶንካ ቀበሌ ሊሰጥብን ነው፤ መሬት የምናርሰው የለንም ይሰጠንና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ተነስተው መግባባት ላይ መደረሱን አስረድተዋል።ይሁንና ውይይት በተደረገበት እለት በብዝሃ ህይወት በተከለለው አንበሳ ጫካ አካባቢ የሚያርሱ ግለሰቦች ቤት እየተቃጠለ ስለሆነ ድረሱልን የሚል በ26/09/2012ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 አካባቢ ጥሪ ሲደርሰን የፖሊስ አካላትን ወደቦታው የላክን ሲሆን ከቁጥጥር ውጭ ሲሆንብንና የፖሊስ አካል ሲመታብን ተጨማሪ ልዩ ኃይል በማከል ለመቆጣጠር እየተሰራ ባለበት ወቅት በተፈጠረ ግብግብ የሶስት ግለሰቦች ህይወት እዳለፈ ተናግረዋል።በዚህም የመንደር 47 እና 48 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የ3 ሠዎች ህይወት አልፏል።የ3 ሠዎች ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ አዛዡ ገልጸዋል።
©የክልሉ መ/ኮ/ቢሮ
@Tfanos
@tfanos