ስሜትን በግጥም


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified



Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


አፋልጉኝ

እኔነቴን አፍቅራ
እኔን በልቧ አኑራ
ዝና ሀብት ያልደለላት
ሰው መሆን የሆነላት
በማክበር የከበረች
ንፅህናን የታደለች
ለፈተና ያልወደቀች
ለቃሏ የታመነች
ስለ እውነት የኖረች
የኔ ሴት እሷ ነች

በማጣቴ ያልናቀችኝ
በማንነቴ የወደደችኝ
የኔን ሳይሆን
እኔን ፈልጋ የቀረበችኝ
የኔን ሴት አፋልጉኝ

ከራሴ በላይ ያመንኳት
ህይወቴን የሰጠኋት
ከልቤ ያፈቀርኳት
የኔ ሴት እሷ ናት

ከእውነት ጋር የተጋባች
ማስመሰልን እርም ያለች
እሷነቷን ያስወደደችኝ
በውበቷ የማረከችኝ
በከፋኝ ጊዜ አለሁ ያለችኝ
ቀን ጠብቃ ያልከዳችኝ
የኔን ሴት አፋልጉኝ።

✍️ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ያኔ የመጣሽ ቀን
አይንሽን አይቼ ፍላጎትሽን ሳውቅ
እንዴት አወ'ክ አልሽኝ
አንቺ እኮ ስትገርሚኝ

እንዴት አወ'ክ አልሽኝ?
አንዴ ብቻ አይደለም
ደጋግመሽ ገረምሽኝ

ግን....
እኔ የነገርኩሽ ፍላጎቴን ነበር
ሀሳብሽ ሀሳቤ መሆኑን ባይገባሽ ሳትረጂው ቢቀር
አልተቀየምኩሽም ትንሽ ግን አዘንኩኝ
አንቺ እኔን ሳትሆኚ
እኔ አንቺን መሆኔ ሞኝነት መሰለኝ

ያኔ የመጣሽ ቀን
እንዴት አወ'ክ ብለሽ እኔን ስጠይቂኝ
ደግሞም ስትገርሚኝ
ትንሽ ግን አዘንኩኝ
ቢሆንም...
እኔም ባንቺ አልፈርድም
ብቻ አደራሽን እኔን ደስ እንዲለኝ ሁሌም እንድትይ ብቅ
ባንቺ ፍላጎት ነው ፍላጎቴን የማውቅ።

  ✍️ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


መረሳት ምንድነው
ህመሙ ሚከብደው
በብዙ ሰው መሀል
አስታዋሽ ማጣት መከፋት
የመከዳት ስሜት የመገፋት

ምንድነው መረሳት ማለት
ሰዉ ሞልቶ መናፈቅ ብቻነት
ሀሳቡን አካፍሎ ከሌለው ተረጂ
ለምን ሰው ይለምዳል
ብቻነትን እንጂ
ለመሳቅ ሚሞክር ሊመስል ደስተኛ
ሰው ማጣት የጎዳው የሆነ ቁስለኛ
ውስጡ በፍቅር እጦት
መንምኖ የከሳ
ስንቱ ይሆን የተረሳ?


✍️ ተጻፈ በአብዱ(የእሙዬ ልጅ)


እውነት ሰለጠንን
ወይስ ሰየጠንን
ዘመናዊነት ሳይገባን ዘመንን እያልን
ፈጣሪን አምፀን ለሰይጣን አደርን
"የሰው የማያልቅ ሀብቱ ምክንያቱ"
ሰበብ ሲደረድር ለሁሉም ጥፋቱ
አዬ ጊዜ እያለ በጊዜ አሳበበ
የማያልቅ ሀጥያት በራሱ ከመረ
ያወቅን መስሎን እያለቅን
የነቃን ሲመስለን
እልፍ አእላፍ ዘመን ተኛን አንቀላፋን
ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን
ብለን ተረትንና እኛኑ አሞኘን

ተማር ሲለኝ አያቴ ናቅኩኝ
መቃም መጠጥ ማጨስ እርድና መሰለኝ
የራሴን እንቁ ባህል አርክሼ
የነጭ ባዕድ አምልኮ ወርሼ
በሴሰኝነት ሱስ ተጠመድኩኝ
ሴት በሴት ቀያየርኩኝ
የዘመንኩ መስሎኝ ራሴን አረከስኩኝ
መልካሙ እኔነቴ ጠፋኝ
ከረፈደ ወዲያ ከየት ብዬ ላግኝ

እኔ የመከንኩኝ የከሸፍኩኝ ትውልድ
ለግል ዝናዬ በህዝብ የምነግድ
ጥቅም ቢደልለኝ አያቴን ሰጠሁኝ
በአባቴ የሰራሁት በልጄ እንዳይደርሰኝ
አሁን ለኔ ፈራሁ እኔም አባት ሆንኩኝ


ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ሀሳብ መች ይጠፋል
ድራማ እየሰራ ሁሉም ያስመስላል
ራሴን ለማግኘት የጠፋ እኔነቴን
የራስ እውነት ይዤ ፍትህ መፈለጌን
ኔጌቲቭ ሀሳብ ነው ብለው ቢያስቡም
ፍትህን መፈለግ አሉታዊ ሀሳብ
ሆኖ እንኳን አያውቅም
ቅር አልተሰኘሁም
ርዝራዥ ተስፋ ውስጤ አላጣሁም
እውነትን ለማግኘት አላመነታሁም
ወይ ትቼ አልተውኩም
ድራማው አይቆምም
ሻል ሲለኝ ህመም
ለምን እንደሆነ እኔም አልገባኝም
ሁኖም መልሱን ላገኝ ወደ ኋላ አላልኩም።


✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


አካልሽን ታቅፌ ውሎ ማደር ብመኝ
እጆቼን ክንድሽ ላይ አርጎ መሄድ ቢያምረኝ
እኔ አንቺን ስወድሽ
አንቺ ሌላ ወደሽ
ላይሳካ ሀሳቤ ሊቀር እንዳማረኝ
አምሮ አምሮ ሊተወኝ ምን አለ ባልመኝ

በኔም አይፈረድ
አደንዛዥ ነው ገላሽ
አፍዛዥ ነው ፈገግታሽ
ችላ ብለው አልፈው ትተው የማይተዉሽ
የቀኑ ሳይበቃሽ በሌ'ት ምትመለሽ
አረ እንዲያው ምን ጉድ ነሽ

ግዴለም የኔ አይሁን ይህ ያማረው ገላሽ
ያ ውብ ፈገግታሽ
ያ'ይኔ ርሀብ ነሽ
ተርቤሽ እንዳልሞት
ብቻ ካ'ይኔ አልጣሽ።


✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ጥርስ ባይኖር ኖሮ ስቆ ማሳለፊያ
የውስጥን ጭንቅ ህመም ደብቆ ማቆያ
እምባ ባይኖር ኖሮ ህመም ማስታገሻ
ምን ይሆን ነበረ የሰው መጨረሻ።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ውጪ ልደር እንጂ ከጅብ ተጋፍቼ
እቤትሽ አልገባም ጨለማን ፈርቼ
ብርዱም ይውረድብኝ መሞቅን አልሻም
አተርፍ ባይ አጉዳይ ልሆን አልከጅልም

ትዝ ይልሽ እንደሆን
አምና በዚ ሰአት እንደዚው ብለሺኝ
በዉብ ቃላቶችሽ በመልክ ሸንግለሺኝ
ና ከቤቴ ግባ ጨለማን ተሻገር ብለሽ አግባብተሽኝ

እኔም
ጅቡ ቢያስፈራራኝ ጨለማው ቢከብደኝ
ውበትሽ ቢስበኝ ቃልሽ ቢያታልለኝ
እቤትሽ ገብቼ ማረፍን ተመኘሁ
ሙያሽን ቤትሽን እስካይልሽ ጓጓሁ

ነገር ተቀይሮ ባይሆን እንዳሰብኩት
ማመኔ ቀፈፈኝ ራሴን ጠላሁት
እኔ የአብረሀም በግ
ተኩላ እንዳይበላኝ ነቅቼ ስጠብቅ
አቁስሎ እንዳይጎዳኝ ከጅብ ስጠነቀቅ
ለካስ ከጉያዬ ከእቅፌ ያኖርኳት
የኔ መጥፊያ ሆነች እረኛዬ ያልኳት

ዘንድሮም እንደ አምና
ቃልሽን አምኜ ልታለል አልሻም
ይብላኝ እንጂ ጅቡ እቤትሽ አልገባም
ጠላትን ለይቶ መጠበቅ አይከፋም

ተኩላን ስጠብቅ እረኛው አጥቅቶኝ
እየመረቀዘ ቁስሌ ፋታ ነስቶኝ
በደልሽን ልረሳ አልቻልኩም አቃተኝ።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


አብሮነትን ትተን ብቻነት ለመድን
ይቸገር ይከፋ ለጎረቤታችን
ግድ የማይሰጠን ቸልተኞች ሆንን
ገና ሳይመሽ ፀሀይ ሳለች
በር ዘግተን ከቤት ዋልን
ይራብ ወይ ይጠማ
ይብረደው ይሙቀው ሁኔታውን ሳናውቅ
ታሞ ካልጋ ውሎ በስቃይ ቢማቅቅ
አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ
ትተን አለፍን እንጂ እኮ ምን አደረግን

ሰበብ ስንደረድር ለእኩይ ተግባራችን
ይሁን ለበጎ ነው
ነገም ሌላ ቀን ነው ብለን እያለፍን
ክፋታችን በዝቶ እንዳንሆን ሆንን
ስንዴ ዘራን እንጂ መች አረም አረምን
ዛሬ ያልሰራነው ነገ ላይ ላይገኝ
መልካሙን እናድርግ መልካም እንድናገኝ።


✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ሆድ ከማይሞላበት
አንዲት ድሀ ሀገር ተወልደን ተፈጥረን
ከዳቦ ያለፈ ጥያቄ እንዳንጠይቅ በርሀብ ተጠፍረን
ማን ይሙት ማን ይኑር ግድ የማይሰጠን
ሆድ አምላኪ ባርያ ለቁስ ሰጋጅ ሆንን

የገዳይ ዳቦ አብሳይ ሟች ሆኖ ምጣዱ
ሟችም ሲንሰፈሰፍ ለጎደለች ሆዱ
አልገባውም ነበር ማገዶ እንደነበር
የተስፋ ዳቦ እንጂ አልታየውም አፈር።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


አትቀስቅሱኝ


እንደምነሽ ሲሉኝ
ሰላም ነኝ ነው መልሴ
ውስጤ ቢረበሽም
ደህና ነኝ ይመስገን
ቢጠናብኝ ህመም
ጥርሴን ከፈገግታ ነጥዬው አላውቅም
ወደ ውስጤ አልቅሼ
እምባዬ ጉንጬ ላይ ሲፈስ አይታይም
መሳቄን ነው እንጂ ማዘኔን አያውቁም

ከተሻለ ብዬ ጉዳቴን ማጋራት
ስቃዬን ማካፈል ከሆነልኝ እረፍት
ህመሜን አልቅሼ
ዘክዝኬ ነግሬ መፍትሔ ስላቸው
ከንፈር መምጠጥ እንጂ
ምን አተረፍኩባቸው

ዝምታን መረጥኩኝ ብዬ ከገባቸው
እነሱም ዝም አሉኝ ደህና መስያቸው

ንግግሬ ካልገባቸው
ዝምታዬ ካስረሳቸው
ርቂያቸው ልሂድ
እኔም ልተዋቸው

በእውን አለም መኖር
ህመም ካተረፈኝ
እጓዳ ገብቼ
ካ'ልጋዬ ተኝቼ
ህልሜን እኖራለሁ
በቃ አትቀስቅሱኝ።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ዛሬ ትላንት ሳይሆን ነገ ሳይሆን ዛሬ
እንዲህ ይሉ ነበር እትዬ ሸንኮሬ
ሁሉም ጥሩ ነገር በነበር የሚቀር
ያኔማ ተብሎ በታሪክ ሚነገር
ያኔ ፍቅር ነበር ያኔ ሰላም ነበር
ጥሩ ተፈቃሪ አፍቃሪ ሰው ነበር
ኩንታል ጤፍ በ50 እንሸምት ነበር
መሬት በ150 እንገዛ ነበር
በዘር ያልተካፈልን
አንድ ህዝቦች ነበርን
ነበር ነበር ነበር
ነው መሆኑ ሲቀር
አለ ማለት ሲያቅር
ሰላም ይጠፋና ፍቅርም ያልቅና
ሁሉም ነገር ነበር

በነገራችን ላይ እኔም ......... ነበር።


ባዶ ቦታው ላይ የራሳቹን ሀሳብ ሙሉበት፤አስተያየታቹ አይለየን እናመሰግናለን🙏 ።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ጉዞ
ከ ነን ወደ ነበርን

እኔ(ድሮ)
እኔ አንተን ሳፈቅር ገደብ ያላበጀሁ
ሳልሰስት ያለኝን በሙሉ የሰጠሁ
ከልብ ያፈቀርኩህ ደስታን የለገስከኝ
ካንቺ ወዲያ ብለህ ጮቤ ያስረገጥከኝ
ቃልህን ጠብቀህ እኔን ብቻ አፍቅረህ
ታማኝ አጋር ሆንከኝ በልብህ አኑረህ

እኛ(ድሮ)
ጉድ የተባለልን
'ላፍታ ማንለያይ ማ'ኔድ ተነጣጥለን
ያየን ካይን ያውጣቹ ብሎ የመረቀን
ተጋብተን ልጅ ወልደን መኖርን ያሰብን
ያልተሰለቻቸን ከልብ የተፋቀርን
አርአያ የሆነ ፍቅር ያሳለፍን

እኔ(ድሮ)
ስለ ፍቅር ብዬ እንባዬን ያፈሰስኩ
አንተን ላለማጣት እራሴን የገበርኩ
አንተን ባሌ ማድረግ ካንተ ልጅ መውለድን
እንደተመኘሁት በውስጤ የቀበርኩ
ፍቅር ወይ ቤተሰብ ምርጫ ውስጥ የወደኩ

እኔ(ያኔ)
ፍቅርን ረግጬ
ጥቅሜን መርጬ
እምነቴን ያጎደልኩ
ልብህን የሰበርኩ

አንተ(ያኔ)
በኔ ቦታ ብትሆን ምን ታደርግ ነበር
ዘጠኝ ወር አርግዛ የወለደችህን
ችላ ትላታለህ ቀልቧ እንዲሰበር
ወይስ አይዞህ ልጄ ብሎ ያሳደገ
መከታ አባትህን ታስቀይመው ነበር

እኔ(አሁን)
እኔና ሀሳቤ ሁለት መንገድ ይዘን
በአንድ ሰው አካል ሁለት ሰዎች ሆነን
እኔ ራሴን ስመርጥ ሀሳቤ ሲል አንተን
ያው እንደተካፈልን ሳንስማማ ቀረን
ሰው እንዴት በራሱ በአካሉ መብት ያጣል
በገዛ ገላው ላይ ሌላ ሰው ይፈርዳል
አንተን ማጣት ያመመኝ
ትዝታህ መዳኒት የሆነኝ
ማፍቀር ካንተ ወዲያ እርም የሆነብኝ
ፍቅሬን የተነጠኩ እኔ ከርታታ ነኝ

እኛ(አሁን)
የምንፈላለግ ግን የማንገናኝ
የምንነፋፈቅ ግን የማንተያይ
እድል እጣፈንታ ያላገናኘችን
ግድ የሆነብን መለያየታችን
በነበር የቀረ ሆነ ታሪካችን።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ይድረስ
ግጠምልኝ ላልሽው

ለደንዳና ልብሽ ፍቅር ለማይገባው
ሳነባ የጻፍኩት መልክቴ ይድረሰው
ካሰኘሽ....
ዜማ አንቺ ስሪለት እኔ ግጥም ጻፍኩኝ
እንዳሻሽ አንብቢው ለኔ ግድ አይሰጠኝ

ልጆችን ሰብስበሽ
አንድ ሰው ነበረ
በፍቅሬ የሰከረ
ሚዛኑን ሳተና
ወድቆ ተሰበረ
ተረቴን መልሱ
አፌንም አብሱ
ብለሽ ቀልደሻል
የመኖሬ ምክንያት የምለውን ፍቅር
አቅለሽ አይተሻል

የኔ ጥልቅ ስሜት
አፈቀርኩሽ ማለት
ላንቺ ቢሆን ተረት
ይብላኝልሽ ላንቺ
መፈቀር ላልገባሽ
ማፍቀርስ ፀጋ ነው
ሰፊው ያልታደለው
ይድረስ ይሄ ግጥም
ግጠምልኝ ላልሽው

እኔን ያብቃኝ እንጂ
ባል ኖሮሽ ለማየት
እጄ አይሰስትም
ብዕሬም አይነጥፍም
አንቺ ያፈቀርሽ ለ'ት።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ቦግ እልም እንደሚል
እንደ ሀገሬ መብራት
ውሉ ያለየለት
ውጥንቅጡ የወጣ
ላንተ ያለኝ ስሜት

እንደ ሰሞነኛው
ልክ እንደ ደህንነት
ድንገት ከተፍ ብለህ
ልቤን አፍነሀት
ፍቅር ከሚባለው
ከጨለማው ክፍል
ታሰቃያታለህ
ደ'ሞ ባሻህ ጊዜ
ጥፍት ትልና ከኔ ትሸሻለህ
እሱስ አይገርመኝም
እኔም አልናፍቅህ

እኔን የሚገርመኝ
ሰው እንዴት ካ'ፋኙ ሙጥኝ ብሎ ይቀራል
ዛሬ ለምን ቀረ ነፃነትን ሰጠኝ
ብሎ ይበሳጫል
ራሱን ይወቅሳል
ስሜቱን ይጎዳል
ብቻነት ይለምዳል

እኔን የሚገርመኝ
እሱ እንዳይመስላቹ
ይሄ ሞኙ ልቤ
ከጠላቱ ለምዶ ክርትት አለላቹ
ይህ እንዳይገርማቹ
አፌ ተሳሰረ መውደዴን ልነግረው
ቃል አጣሁላቹ

ይመጣል ሊያለፋኝ
ይሄዳልም እሩቅ
እኔም ደ'ሞ አልናፍቅ
ግን ሲዘገይ ጊዜ
ጭንቅ ጥብብ ስቅቅ

ስሜቴ ግራ ነው
እኔም ግራ የገባኝ
ፍቅር ይሁን ስሜት
ስላንተ የተሰማኝ
ልነግርህ ፈልጌ
ግን አፌ የከዳኝ።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


እሷን ላላገኛት ራሴን አጣሁኝ
መራር እውነት ትቼ
በአብረቅራቂ ውሸት ስሰቃይ ከረምኩኝ
እርግጥ ነው አልክድም
ልረሳት ፈልጌ ብዙ ሰው ቀረብኩኝ
ጉድለቴን ሸፍነው እሷን እንዲያስረሱኝ
እሷ ብትኖር ኖሮ ከሚል ምኞት አለም
ነጥቀው እንዲያወጡኝ
ቢሆን ኖሮ እያልኩ በቅዠት እንዳልኖር
በትናንት ህይወቴ ተቸንክሬ እንዳልቀር
አዲስ ሰው ለመድኩኝ
ቢሆን ኖሮን ትቼ የሆነውን ልኖር
እርግጥ ነው አልክድም
እርሷን ልርሳ ብዬ የማደርገው ነገር
ይበልጥ ሲያስታውሰኝ ባስ ሲል ሲጎዳኝ
በብዙ ህመሞች ስታገል ነበርኩኝ
ነበርኩኝ? ወይም ነኝ
ብቻ ግልጽ አይደለም
ቢሆንም
ጉዳቱ ጥልቅ ነው
ከቃል በላይ ሲሆን ህመም
እርግጥ ነው አልክድም
ትልቁ ስህተቴ አጉል ፍላጎቴ
እሷን ላላገኛት ራሴን ማጣቴ
ቢሆንም....።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


እውነትን ቀበርናት
ተባብረን ባንድነት
ነብስ እንዳትዘራ
ሀውልት አቆምንባት

ፍቅርን ፈለግናት
አንድ ሆነን ለመኖር
ሞክረን ሞክረን
ፈልገን ስናጣት
ፍቅር ድሮ ቀረች
ብለን ወሰንባት

እውነት ቀድመን ቀብረን
ፍቅር የለም ማለት
እውነት ገፍተን ጥለን
ፍቅርን መናፈቅ
ባቄላውን ዘርተን
ስጋ እንደመጠበቅ።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ደግሞ
ላይሽ ፈልጋለሁ
የፍቅሬን ርሀብ በአይኖቼ ላስታግስ
መጓዝን እሻለሁ ካለሽበት ስፍራ ፈጥኜ እንድደርስ
የኔ ምኞቴ ነው
ቀርቤ ሳልነግርሽ ከሩቅ አንቺን ማፍቀር
በአይኔ ብቻ እያየሁ ስወድሽ እንድኖር
ለምን? አትዪኝም
እሺ ወይም እምቢ ግዴለኝ ለመልስሽ
መልስሽን ሳልጠብቅ ነውና ማፈቅርሽ
እኔን የሚያስፈራኝ
ቀርቤ ባወራሽ ሰጋሁ እንዳላጣሽ
ያሰብኳትን ሳይሆን ሌላኛዋን ሆነሽ
ያቺ ዘመናዊ ቄንጠኛዋን መስለሽ

ደግሞ
ልሰማው እሻለው አልሰለች ድምጽሽን
ጆሮዬ ንቁ ነው ሳፈቅር እኔ አንቺን
ዘመን አመጣሹን ስልኬን ከጄ አርግቼ
ባለ አስር ዲጂቱን ቁጥር ነካክቼ
ከጆሮዬ አውልና እጠብቅሻለው
እስከምታነሽው ምሆነው አጣለው
ስልኩን ስታነሽው ሄሎ ስትዪማ
ፍንድቅድቅ እላለው ድምጽሽን ስሰማ

ደግሞ
ልነካሽ እሻለው አካልሽን ልዳሰው
ከእቅፌ ስትገቢ ስሜቱን እንዳውቀው
ታውቂዋለሽ አይደል የጥንዶቹን መንገድ
ህልም አልማለው ጥንድ ሆነን እንድኔድ
ይታየኛል ደግሞ
መንገደኛው ሁሉ ወደኛ ሲያማትር
በዚህ ዘመን አለ እንዲ ያለ ፍቅር?
እያለ ተገርሞ አፉን ከፍቶ ሲቀር

ዳሩ ግን...
ላይሽ ብፈልግም
ልነካሽ ብጥርም
ድምጽሽን ለመስማት
ጉጉት ቢኖረኝም
ድምጽሽን አልሰማም
ልዳስሽ አልችልም
እንጃ እኔ አላውቅም
እያለሽ የለሽም።

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


ማፍቀሬ ስህተት ነው?
ጥያቄ አንስቼ ስወዛገብ ከራሴ
ጥቅም ለማይኖረው ትላንትን ማስታወሴ

ባንድ በኩል
ተመርጦ አይፈቀር ሚል እምነት አኑሬ
እንዳልተሳሳትኩኝ ራሴን አሳምኜ
ልክ እነደሆንኩ አስብና እፅናናለው
ባይጠቅመኝም እጎዳለው

ደግሞ ባንድ በኩል
የሌላ ሆነህ ሳለ ወይ አልቆረጠልኝ
ትላትን ያለፍኩኝ የረሳሁ ሲመስለኝ
ስላንተ ስሰማ ፍቅርህ አገረሸብኝ

ምናልባት
ትተኸኝ ስለሄድክ ስለተለየኸኝ
አዲስ ገላ አቅፈህ እኔን ስለተውከኝ
ክፉ ነው እያልኩኝ ስምህን አላጠፋም
ሳገኝህ ማወድስ ሳጣህም ምወድህ
ባንተ ተስፋ ማልቆርጥ ነበርኩኝ አፍቃሪህ

ደሞ አላፍርም ነበርኩኝ እላለው
ዛሬ እንደጠላሁህ እንደረሳሁ ሰው
ልውቀስህ ብልም ልቤ መች ታዘዘኝ
ከኔ ይልቅ ላንተ ሁሌ እያደላብኝ
ባንተ ላይ ጨክኖ መቁረጡ ተሳነኝ

ስምህን ባጠፋ
ያሳለፍነው ጊዜ አይታዘበኝም?
ማንም ያልሰጠኝን ፍቅርን ሰጠኸኝ
አይቼ ማላውቀው አለም አሳየኸኝ
ካንተ ወዲያ ለምን እንድል አደረከኝ

ደሞ'ኮ አላፍርም
ያሳለፍነው ጊዜ
የሰጠኸኝ አለም
አይታዘበኝም?ብዬ ለፍፋለው
ስምህን ለማጥፋት አቅሙ እንዳለው ሰው

ስትፈልግ ስትመጣ ሳትፈልግ ስትቀር
ምቀበል ምጠብቅ ምንም ሳልሰኝ ቅር
ሌላ ምን ይባላል ቢሆን እንጂ ፍቅር
እንዳንተ ማፈቅረው ወደፊት አይመጣም
ካለፈውም የለም
የፍቅሬ መጠኑ ይሄ ነው አልልህ
ምስካሪ ካሻህ
ትራሴ ይንገርህ እንባዬን ያበሰው
በማጣት ስሰቃይ አብሮኝ የነበረው

ብትለየኝ እንኳን ትተኸኝ ብትሄድም
እኔ አንተን ከማፍቀር ወደኋላ አልልም
እና ፍቅር
እኔ ተጎድቼ ከተሰማህ ሰላም
አዲስ ጎጆህ ይድመቅ
ደህና ሁን የኔ አለም።


"ፍቅር አስገራሚ ነገር ነው መገናኘት እጣ ፈንታቸው ላልሆነ ግን......"

✍ ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)


እያሰብኩሽ መሸ
ዕያሰብኩሽ ነጋ
ከበቴ ወጣሁኝ
አንቺኑ ፍለጋ
አንቺን ያወጣዉ በር
የወሰደሽ መንገድ
ብዙ ተማፀንኩት እኔንም እንዲወስድ

ከጎጆ ዉስጥ ገብቶ
የቤቱን በር ዘግቶ
ድምፁ እንዳይሰማ
በትራስ ታፍኖ
ነዉ ወንድ ሚያለቅሰዉ
ማንም ሳይሰማ አዝኖ

ወጉ ይድረሰኝ ብየ
እኔም እንድያ አረኩኝ
የወሰደሽ መንገድ
ዱካሽን አስሶ
አንቺ ጋር ቢያደርሰኝ

ያደርሰኝ እንደሆን
እኔን ካንቺ ዘንዳ
አልቅሼ ለመንኩት
ገብቼ ከጓዳ
ፍላጎት ከሌለሽ
እኔ እንድመጣ
ልክ እንደወሰደሽ
አንቺን እንዲያመጣ

ካልሆነ ግን.......
አንዴ ከሄድሽ አንቺ
አትመለሽ እንደሁ
ነፍሴን መልሽልኝ
እንዴት እኖራለሁ

እኮ እንዴት?
ነፍሴን ይዘሽ ሄደሽ
በድኔንም ትተሽ
እኔን በቁም ገለሽ

ርቀሽ ከሄድሽስ
አስከፋኸኝ ብለሽ
እኔ ለብቻዬ እንዴት እዘልቃለሁ
አንቺ ያልኖርሽበት
ህይወቴ ምንም ነው
ብበድልሽ እንኳን ውስጥሽን ባስከፋ
ባፈቀሩት ሰው ላይ አይቆረጥ ተስፋ

ስለዚህ...
ጥፋቴን አውቄ ይቅርታ ስጠይቅ
ትመጫለሽ እያልኩ በጉጉት ስጠብቅ
ምናል ብትመለሽ በናፍቆት ስማቅቅ።

✍ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)

20 last posts shown.

109

subscribers
Channel statistics