Forward from: Bahiru Teka
አሁን ውይይቱ ምን ያህል አስፈላጊ ነው ወደሚለው ነጥብ እናምራ ፡፡ በኢብኑ መስዑዶች ላይ አሁን ያላቸውን አቋም ግልፅ እንዲያደርጉ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ፣ ኢብኑ ሙነወር ፣ "ተብዲዕ እንደማናደርግ ከፊታችሁ አልተናገርንም ?" በማለት በጥያቄ መንገድ መልስ ሰጥቶበታል ፡፡ ባጭሩ የኢብኑ መስዑድ ሰዎች የቢዳዐ አራማጆች አለመሆናቸው እንደሚያምኑ እየተናገሩ ነው ፡፡
እኛም በግልፅ ማወቅ የፈለግነው ይህንኑ ነው ። የሰለፎችን መንሀጅ በተለያየ ጊዜ በመጣስ ትልቅ ስህተት ስለሰሩትና ከስህተታቸውም ስላልተመለሱት የኢብኑ መስኡድ አመራሮች እነኢብኑ ሙነወር ግልፅ በሆነ መንገድ አቋማቸውን እንዲነግሩን፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የውይይት ጥሪ በተለያዩ ወንድሞች ሲቀርብ አሻፈረኝ ብለው ባህር ዳር ሁለት ሆነው በመሄድ አመክኗዊ ( ሎጂካዊ) ነጥቦችን አንስተው ያገኙትን መልስ እንደ ድል ቆጥረው መመለሳቸውን ይሄውና ኢብኑ ሙነወር ነግሮናል፡፡
ሀቁ ይህ ከሆነ ፣ ውይይቱን ማካሄድ የሚያስገኘው ጥቅም ምንድ ነው ? የጥመት መንገድን ከመረጡ አካላት ጋር ውይይት ያካሄዱ ሰለፎች በጣም ውስንና የተወያዩትም አንዴ ብቻ ስለመሆኑ ከፍ ሲል ለማሳየት ተሞክሯል ፡፡ ታዲያ ከነዚህ ሰዎች ማለትም ከነኢብኑ ሙነወር ጋር መወያየት ያለብን ስንት ጊዜ ነው ? ከአሁን በኋላ ስንት ጊዜ እንድናካሂድ ነው ሶሻል ሚዲያውን እያጥለቀለቁት ያሉት ? እኛ ከሰለፎች አካሄድ በማፈንገጥ በውክልና ከእነሱ ጋር የምንከራከረው እስከ መቼ ነው ?
ሀቁን ማወቅ ለፈለገ ሀቁ ከጠራራ ፀሀይ የበለጠ ደምቆ ይታያል ። ሀቁን ላልፈለግ ቀኑ ከጨለማ የተለየ አይደለም ፡፡
ውይይት አይካሄድም እንጂ ቢካሄድ - ከዚህ በፊት ከነበሩን ውይይቶች በተግባር እንዳየነው - ለራስና ለጭፍን ተከታዮች የአሸናፊነት ስነልቦናን የሚያቀዳጁ ሶስት "የማሸነፊያ" ዘዴዎችን ታጥቀው ነው ወደ ውይይት ለመግባት እየተጣሩ ያሉት ፡፡
1 – በውይይቱ ላይ የመከራከሪያ ሀሳብም ሆነ ተቃውሞ የሚያቀርቡት የሰለፎችን መንሀጅ ተከትለው ሳይሆን በዚህ ምትክ አመክኒዮ (ሎጂክ) ነው የሚያቀርቡት ፡፡
ለምሳሌ፡- "እከሌ የተባለ አሊም እገሌ የተባለውን አሊም ሙብተዲዕ ብሎታል ፡፡ እንቶኔ የተባለው አሊም ግን የዘመናችን ምርጥ ሰለፍይ ብሎታል ፡፡ ይሄን ምን ትሉታላችሁ ?" በቃ - በሎጂክ ላይ ሎጂክ ፣ በሎጂክ ላይ ሎጂክ…
2 – የፈለገ የመረጃና የማስረጃ ክምር ከቁርአንና ከሀዲስ እንዲሁም ከሰለፎች ቢቀርብላቸው ፣ ሀቁን ባለመቀበል ሁሉንም "ድባቅ" የሚመቱበት ፣ "ላዩቅኒዑኒ" (አያጠግበኝም) የሚል ካርድ አላቸው ፡፡ የፈለከውም መረጃ ብትደርድር ፣ የፈለከውን ማብራሪያ ብታዥጎደጉድ ፣ "ላዩቅኒዑኒ"ን የማሸነፊያ ስትራቴጂ አድርጎ የሚጠቀምን ሰው ምንጊዜም ልታሳምነው አትችልም ፡፡
3 – ሶስተኛው "የማሸነፊያ" ካርዳቸው ፣ "ላየልዘሙኒ" (አይዘኝም) የሚል ነው ፡፡ ይሄ ውይይቱን ለማሳረግ ሲፈልጉ የሚመዙት ካርድ ነው ፡፡ "ላየልዘሙኒ" (አይዘኝም) ከሰለፎችም ሆነ ፣ ከሰለፍዮች የፈለገ አስተማማኝ የሆነ ማስረጃም ሆነ ፈትዋ ቢገኝ ፣ ውይይቱን "በአሸደናፊነት" ለመውጣት የሚመዘዝ ካርድ ነው ፡፡ "ላየልዚሙኒ" (አይዘኝም) ብሎ ድርቅ ካለ ምን ማድረግ ትችላለህ ?
እነዚህ ሶስት ካርዶች በሙመይዐነት የተጠቁ ወይም ለሙመይዖች ጋሻ አጃግሬ የሆኑ ሰዎች አዘውትረው የሚጠቀሙባቸው "የማሸነፊያ" ዘዴዎች ናቸው ፡፡
የሰለፎችን መንሀጅ አሽቀንጥሮ ጥሎ እነዚህን እንደ ስልት የሚጠቀም ሰው ፣ ማንኛውንም ውይይት "በአሸናፊነት" የሚወጣው እሱ ነው ፡፡ "በአደባባይ ካልሆነ አንወያይም ፤ ከዚህ በፊት ተነድፈናል ፤ ቅብጥርሴ" የተባለውስ ለዚህ ሳይሆን ይቀራል? እነዚህን ካርዶች የሚጠቀሙ ሰዎች ምሳሌያቸው ፣ ከጉድጓዷ ደጅ ላይ ሆና ድመት እያያት እንደምትደነስ አይጥ ብጤ ነው ፡፡ ድመቷ ገና ማድባት ስትጀምር ፣ ወደ ጉድጓዷ ጥልቅ ነዋ !!!!!! ።
ለማንናውም ወንድሜ ኢብኑ ሙነወር ከዚህ በፊት " ውሸታም ፣ ቀጣፊ ፣ ተንኮለኛ ፣ ዐቂዳን ለድርድር ያቀረቡ ፣ ወላእና በራእ የዐቂዳ ጉዳይ እንዳልሆነ ሊግቱን ይዳዳቸዋል" ። ስትላቸው የነበሩትን የመርከዙ ሰዎች ዛሬ እኔ ከፈለግሁኝ ድንጋይን ዳቦ ብዬ ማሳመን እችላለሁ በሚል አይነት ስሜት እነሱን ወክለህ እኛን ለመሞገት ቆርጠህ የተነሳህ በመሆኑ ላሳውቅህ የምወደው ከዚህ በኋላ ኢብኑ መስዑዶችን ከምንፋለመው በላይ ተወካዮቹን የምንፋለም መሆናችንን ነው ። አሸናፊነት በተመለከተ ፈቅደናል አሸንፈናል በሉ ። ዋንጫውንም ተረካከቡ በውይይቱ ፋንታ ህዝብ እያያችሁ ከኢብኑ መስዑዶች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ተከታዮቻችሁን አስጩሁ ።
ባህር ዳር ላይ የተካሄደውን ውይይትና ጥሪውን አስመልክቶ ከመሻኢኾቻችን ማሳረጊያ እንጠብቃለን ።
https://t.me/bahruteka