📌ድብልቅልቁ የትምህርት ዓለም ዋይታ በእውነተኛው የኢስላም ብርሃን ሲፈታ📌
📝ተከታታይ ፅሁፍ
👉 ክፍል ( ሃያ ) 👈
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيم
... አብዛኛው ታዳጊ እፃናት እስከወጣቱ ድረስ እግር ኳስ ጫወታ ተመልምሎ ወደ ስራ ሲገባ ፦
1ኛ. በልምምድና በጫወታ ሰዓት የሚያደርገው ልብስ አውራውን
(አፍረተ-ገላውን) ያሳይበታል ።
ይህ ማለት ደግሞ በእስልምና እነዲሸፍነው የታዘዘውን የሰውነት ክፍል ባልተፈቀደ ሁኔታ ለእይታ ማጋለጥ ማለት ነው።
2ኛ. አብዛኛውን ጊዜ በልምምድና ውድድር ምክንያት ሶላትን ጨምሮ አንዳንድ "ዒባዳ"ላይ ከባድ ጉድለቶች ይከሰታሉ ። "አላህ" የደረሰለት ካልሆነ በስተቀር ከነጭራሹ እስከመተውም ይደረሳል።
3ኛ. በፉክክር ውሰጥ ለሚከሰቱ አላስፈላጊ "ሸሪዓ"ያወገዛቸው ለሆኑ ድርጊቶች ይዳረጋል።
ለምሳሌ፦
👉 ገንዘብ አሲዞ በመጫወትና ቁማር ላይ መውደቅ …
👉 ለሽንፈት ላለመዳረግ ሲባል አላስፈላጊ ድርጊትን መፈፀም ፤ ወንድሙን ጠልፎ መጣል የመሰለ፥
አካሉ እንዲጎዳ በማድረግ በቀለኛ እንዲሆን ማድረግ ፥ መጣላት ፣
መሳደብ ፣ እውከት መፍጠርና መጎዳዳት ... "ሸሪዓ" ያወገዘውን ጠላትነትን በእስልምና ወንድማማቾች መካከል እንዲከሰት ምክንያት መሆን...
4ኛ. በትላልቅ መድረኮች ላይ በቪዲዮ መቀረፅ ፥ ሴትና ወንዶች ተቀላቅለው እንዲታደሙ በማድረግ ለሚደረገው አላህን የሚያስቆጣ ወንጀል ምክንያት መሆን ፤ በዚያ ቦታ ላይ ለሚከሰቱ ጩኅቶቾ ፣ ስድቦች ፣ ብልግና ለሆኑ ክንውኖች ፥ ዘፈኖች ፣ አንድነትን የሚሸረሽሩ ቀረሮች ፣ ግጥሞችና ፉከራ ... ጠቅሰን የማንዘልቀው
ለሆነው ክስተት አንድ አካል ሆኖ መገኘትን እውን ያደርጋል ።
👉 ይህ ድርጊት በጣም በሚያሳዝን መልኩ ሴት እህቶቻችንንም ያካተተ መሆኑ ነው ። እስቲ ቆም ብለን እናስተውል ፤ ከላይ ከብዙ በጥቂቱ ለማየት የሞከርነውን ጥፋት በፆታ ሴት ወደሆኑ እንስቶች ቀይረን እንመልከተው።
❌ የት/ቤት ስፖርታዊ አለባበስና የሴቶች ልጆቻችን ተሳትፎሃቸው ፦
👉 ት/ቤት ውስጥ በስፖርት አስተማሪ የስፖርት ልብስ አምጡ በሚል አስገዳጅ ትዕዛዝ የስፖርት ልብስ ያዘጋጃሉ። ከዚያም ውዷ የኢስላም እንቁ በተዘጋጀላት የስፖርት ልብስ የደመቀች ይመስል ትራቆታለች። በአስተማሪያቸው እጅ ከጭናቹ ወደዚህ ፥ ከወገብ ወደላይ ፥ ከጉልበት ሸብረክ እየተባሉ ይዳሰሳሉ ፤ታዲያ ይህ ሁሉ በስፖርት ትምህርት ስም የሆነ እውነት ነው።
👉 ግን ምን ችግር አለ❓ልብ ከታወረ ምን ይደረግ❓ፈጣሪ የቀናባት ባሪያ የሚቀናላት ባሪያ አጣች❗
አባትም❓እናትም❓ወንድምም❓
ዘመድም❓በቃ አሆ❗ሁሉም ፀጥ አሉ !!!
"ነብዩ" ግን ገና ቀድሞኑ "ደዩስ"
"ጀነት" አይገባም አሉ !!!
ደዩስ ደግሞ ማነው❓
ደዩስማ በቤተሰቡ (በቤተዘመዱ) በእህት ወንድሞቹ ወንጀል ሲሰሩ አይቶ የማይቀና (የማይቆች) ማለት ነው።
💫 ((عن عبدالله بن عمر (ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ)ﻗﺎﻝ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ : "ﺛﻼﺛﺔ ﻻ ﻳﻨﻈﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ ﺇﻟﻴﻬﻢ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﻘﻴﺎﻣﺔ : ﺍﻟﻌﺎﻕ ﻟﻮﺍﻟﺪﻳﻪ ، ﻭﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﺍﻟﻤﺘﺮﺟﻠﺔ ، ﻭﺍﻟﺪﻳﻮﺙ ،"))
ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ
ﺣﺴﻨﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ
💫 (("አብደላህ ቢን ዑመር (አላህ ስራውን ይውደድለትና) ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አሉ በማለት አለ ፦
" የወላጆቹን ሐቅ ያጓደለ ፥ ወንዶችን የምትመሳሰል ሴትና በሴቶቹ የማይቀና ወንድ (እነዚህ) ሦስት ሰዎች እለት ትንሳዔ ቀን አላህ ወደ እነሱ አይመለከትም ።" ))
[ኢማሙ አሕመድና ነሳኢ ዘግበውታል]
(ኢማሙ አልባኒ ሐሰን ብለውታል)
አላህ ይጠብቀን!!!
📚 ታላቁ "ኢማም ሐሰነል በስሪ" በሴቶቻቸው የማይቀኑን ወንዶችን እንዲህ በማለት ወቅሶ ነበር ፦
قَالَ الحسَنُ البَصرِيِّ رَحِمَهُ اللهُ :
" أتدعُونَ نِساءَكُم لِيُزاحِمْنَ العُلُوجَ فِي الأسوَاقِ ؟! قَبَّحَ اللهُ مَن لا يَغَارُ ".
📚(إحيَاءُ عُلُومِ الدِّين ٤٦/٢).
ሐሰነል በስሪ አላህ ይዘንለትና አለ ፦
" በግብይይት ቦታ ላይ እንደ አህያ እንዲጋፉ ሴቶቻችሁን ትተዋላችሁን❓❗(በሴቶቹ) የማይቀና የሆነ ሰው "አላህ" ከሁሉም "ኽይር" ያርቀው።
[ኢሕያሁ ዑሉሚ አል-ዲኒ 2/46]
🔥 እስቲ ወገኖቼ ቆም ብለን እናስብ
(እንቆርቆር) የአብራካችን ክፋይ
የኢስላም እንቁ "የሁዳና ነሳራ" የአላህ ጠላት የሆኑ ካህዲያኖች "በፈበረኩላት"
እግር ኳስ ተጠምዳ ፤ የወደዱላት መስለው ባሴሩባት ፥ ያደነቋት መስለው በተሳለቁባት ፥ የጠቀሟት መስለው በጎዷት ነገር ላይ አሳልፈን
ሰጥተናቸዋል !!!
እንደፈለጋቸው እንዲያደርጓት ፈቀድንላቸው ፤ ብቻም አይደለም … ጭራሹንም እነሱ ከደከሙት በላይ ደከምንላቸውና ፍላጎታቸውንም ሞላንላቸው❗❗❗
አላህም የሚለው ይህንኑ ነው ፦
📖 (( "وَاللَّهُ يُرِيدُ أَن يَتُوبَ عَلَيْكُمْ وَيُرِيدُ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الشَّهَوَاتِ أَن تَمِيلُوا مَيْلًا عَظِيمًا" ))
النساء (27)
(( " አላህም በእናንተ ላይ ፀፀትን ሊቀበል ይሻል። እነዚያም ፍላጎታቸውን
የሚከተሉ የሆኑት (ከእውነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ
ይፈልጋሉ … ። " ))
[አል-ኒሳህ (27)]
በአላህ ፍቃድ ክፍል ሃያ አንድ
ይቀጥላል ፦
📝 … ኢስማኤል ወርቁ …
https://t.me/amr_nahy1