ይህ መፅሀፍ የፖርኖ ግራፊ(Porn) ሱስ አስከፊ ጉዳቶቹና ከፖርኖ ግራፊ ሱስ እንዴት መውጣት ይቻላል ጨምሮ ብዙ ጠቃሚ ምክሮች ይዟል።
በአንድ ወቅት ‘ጉግል’ አለም ላይ አብዝተው ወሲብ (Sex) የሚለውን ቃል ፈልግልን ከሚሉኝ 5 ሐገራት መካከል እናንተ ኢትዮጵያውያን ዋነኞቹ ናችሁ ብሎን ነበር። ይህ የሚያሳየን በሐገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰው የፖርኖግራፊ ተጠቃሚ ወይም በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ መሆኑን ነው። ይህ ሱስ
እንደሌሎች ሱሶች በግልጽ በሱሰኛው ላይ የማይታይ በመሆኑ እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት በቂ መረጃ ስለሌለ የተጠቂዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል።
ይህ ሱስ በዓለም አሳሳቢ የሆነና ብዙ ሰው እያጠቃ ያለ በሽታ ነው።በኢንተርኔት ውስጥ ከሚገኘው ወደ ግማሽ የሚሆነው መረጃ ፖርኖግራፊ ወይም ከፖርኖግራፊ ጋር ተያያዥ የሆነ መረጃ ነው።በየቀኑ ኢንተርኔት ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከል 25% የሚሆኑት ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ናቸው።ከኢንተርኔት ላይ ከሚወርዱ ቪዲዮዎች መካከል 35% የሚሆነው ከፖርኖግራፊ ጋር የሚገናኙ ናቸው ።
አሁን ባለን መረጃ ‘Pornography is not like a drug, it is a drug’ (ፖርኖግራፊ አንደ አደንዛዥ ዕፅ ሳይሆን እራሱ አደንዛዥ ዕፅ ነው) እንዲያውም መልከ ብዙ ዕፅ ነው።
ሰው ፖርኖግራፊ ሲያይ ብዙ ዕፅ በአንድ ላይ እንደወሰደ ይቆጠራል።
:::
ሌላውን ከመፅሀፋ ያገኙታል።
@blackberry1000@blackberry1000