ቀጠሮ የለውም
ዛሬም የይቅርታ ቀን ነው….
መጽሐፍ ቅዱስ ጸሀይ ሳትጠልቅ በፊት ይቅር መባባል እንዳለብን ቢነግረንም በዓመት አንድ ቀን ጠብቀን ‹ያስቀየምኩት ካለ› ተብሎ እርስ በእርስ ይቅር መባባሉ ሌላ ይቅርታ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው ባይ ነኝ::በመጀመሪያ ይቅር ከመባባላችን በፊት የበደልነውን/የበደሉን ምን እንደሆነ ማወቅ አለብን ሲቀጥል ደግሞ ሁኔታውን ማየት አለብን ይህም ጥፋቱ ሰው የሚያውቀው ከሆነ ይቅርታ መጠየቅ ያለብን በሰው ፊት ነው በግል ከሆነም እንዲሁ::ያጠፋነውን ጥፋት ስም ጠርተን መናገር አለብን እንጂ ያስቀየምኩት ካለ በሚል ስልክ ላይ ብቻ ያሉ ሰዎችን ይቅርታ መጠየቅ የዓፍ ወለምታ በድሊት አይታሽም ነው ነገሩ::ደግሞ ለክርስቲያን የይቅርታ ቀን ጳጉሜ 1 ብቻ ሳይሆን ዓመቱን ሙሉ ነው!
‹እውነተኛ ኑዛዜ ሁል ጊዜ ጠቅለል ተደርጎ የሚቀርብ ሳይሆን እያንዳንዷን ሐጥያት በዝርዝር ማውሳት ይጠይቃል::ምናልባትም የሰራነው ሀጥያት በእግዚአብሔር ፊት ብቻ መቅረብ ያለበት ሊሆን ይችላል::ሰውን ጎድተን ከሆነ ወደዚያ ሰው ቀርበን ድርጊታችንን ማመን ተገቢ ነው::በህዝብ ፊት መናዘዝ የሚያስፈልገው ሀጢያት ሰርተንም ከሆነ በድረክ ላይ መናዘዝ ተገቢ ነው::ይሁን እንጂ የትኛዉም ዓይነት ኑዛዜ ግልጽና ቀጥተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ በደለኛ የሆንበት ጥፋት የቱ እንደሆነ የሚገልጽ መሆን አለበት››ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ ገጽ 36
https://t.me/joinchat/AAAAAEfX223-mkRE5vFvWA