TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
English
Site language
Russian
English
Uzbek
Sign In
Catalog
Channels and groups catalog
Search for channels
Add a channel/group
Ratings
Rating of channels
Rating of groups
Posts rating
Ratings of brands and people
Analytics
Search by posts
Telegram monitoring
SearcheeBot
Your guide in the world of telegram channels
Start bot
ad
Telegram Analytics
Subscribe to stay informed about TGStat news.
Read channel
ad
TGStat Bot
Bot to get channel statistics without leaving Telegram
Start bot
ad
TGAlertsBot
Monitoring of keywords in channels and chats
Subscribe
ad
Statistics
Favorites
መሰልጠን ወይስ መሠይጠን
@elohe19
Channel's geo and language:
not specified, not specified
Category:
not specified
የምዕራባውያን ስልጣኔ ወዴት እየወሰደን ነው?
Related channels
Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Favorites
Is this your channel?
Confirm
Канал в реестре блогеров РКН?
Confirm
Channel history
Posts filter
Select month
July 2020
Hide deleted
Hide forwards
መሰልጠን ወይስ መሠይጠን
31 Jul 2020, 14:45
Open in Telegram
Share
Report
ይህ ጦማር የተከፈተበት አላማ አሁኑ ያለውን ልቅ የሆነ ስልጣኔ በመተው ባህላችንን በድጋሜ እንዲያንሰራራ እንድንማማርበት በማሰብ ነው።
በዚህ ጦማር ውስጥ ፕሮሞሽን አይሰራም
የምንማማረው ትምህርት እንዳንሰላች በሳምንት ፫ ቀን ብቻ ነው ምንለቀው
አባላቶች በዛ ሲሉ ቀኑን እናንተው ትመርጣላችሁ
ጦማሩን መቀላቀል የምትፈልጉ
@elohe19
157
2
0
መሰልጠን ወይስ መሠይጠን
31 Jul 2020, 14:45
Open in Telegram
Share
Report
" ለመሆኑ ስልጣኔ ምንድነው?...የሰው ልጅ ፣ አስቀድሞ በነፍሱ ካልሰለጠነ ፣ በሰውነቱ ካልሰለጠነ ምኑን ነው ሰለጠነ ምንለው?...መገልገያ ቁሱን ነው?... በእርግጥም የሰው ልጅ ቁሶች ከሰራቸው ከሰው ልጅ በላይ ሰልጥነዋል። ተራርቀውማል። እነዚህ ቁሶች እንደ ሰው ልጅ ነፍስ ቢኖራቸው ኖሮ ከሰው ልጅ በላይ አስተዋዮች በሆኑ ነበር።
እስቲ ይሄን ስልጣኔ ያላችሁትን ነገር በጥሞና ተመልከቱት። የዘመነኛው ቁሳዊ ስልጣኔ ግኝቶች ልብ በሏቸው። ዓለም ላለባት ችግር መፍተሔ ከመሻት ይልቅ ፣ ግኝቶቹ ራሳቸው ከምንም የከፋ ችግር እየሆኑ እንዲያውም የቀደሙትን ችግሮች እስከማስረሳት ደርሰዋል። ግኝቶች ከሚያስከትሉት ጠንቅ ይልቅ በግኝቶቹ የሚያገኘው ኅይል ገንዘብና ዝና ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶታል።
በዚህ ሠለጠነ ባላችሁት ዘመን ሰላምን በምድር ላይ ለማራቀቅ የተደረገ ጥረት ሳይኖር፣ የጦር መሳሪያዎችን ይበልጥ አጥፊ አድርጎ ለማራቀቅ በየደቂቃው ብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ይወጣል። በዚህም ሳቢያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት በሦስት ዓመት ተኩል ዕድሜ ብቻ ፳ ሚሊዮን ያህል ወታደሮችና ብዙ ሚሊዮን ሰላማዊ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል። ለ ፳፪ ዓመታት ያህል ይበልጥ ሲራቀቅ ቆየና ደግሞ ፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የ ፭ ዓመት እድሜ ውስጥ ከ ፶ ሚሉዮን በላይ ሰዎችን አጨደ። ከዚያም ዘመን በኋላ የዓለም ጦርነት ተብሎ አይጠራ እንጂ በየሀገራቱ የተደረጉ ጦርነቶች ከ ፳ ሚሊዮን በላይ ሰዎች አጭደዋል።
ታድያ ሰው ያልሰለጠነበት ስልጣኔ ምንድነው? .... ስልጣኔ መጀመር ያለበት ከነፍስ ነው። በመንፈስ ስትሰለጥን በማንነትህ ላይ ስልጣኔ ይኖርሀል። ስራህም መልካም፣ ፍሬህም ፍቅርና ሰላም ይሆናል። በዚህ የዘመናዊው ስልጣኔ ዘመን የረሀብና የቸነፈር ክንድ ይበልጥ በርትቷል። ለምን ቢባል ለአንድ የተፈጥሮ በሽታ መድሀኒት ለመፈለግ ከሚወጣው ገንዘብ ይልቅ ሌላ አዲስ በሽታ ለመፍጠር ይሄ ነው የማይባል ገንዘብ ይወጣልና ነው። ብዙ ሚሊዮን የዓለም ረሃብተኞች የረሃብን ስሙን እንኳ እንዳይሰሙ ለማድረግ፤ ከጦር መሳሪያው ስልጣን ካዝና ላይ ጥቂት ገንዘብ መዝገኑ ብቻ በቂ ነበር።
ለዚህም ነው የሰው ልጅ በመንፈስ ካልሰለጠነ በቀር ፍቀርና ሰላምን አያገኝም የምልህ። ለዚህም ነው ከእርካታ እልፍኝ ተጋብዛችሁ ሳለ ታዳሚዋ መሆን ሳትችሉ እንደተራባችሁ የምታልፉት። ኑሯችሁ ሊበጠስ አንድ ሀሙስ የቀረውን ያህል ከሯል። በዚህ የኑሮ ግብግብ ውሰጥ ላለመውደቅ ሳያለሰልሱ መሮጥ ነውና ፤ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ፣ ህብረተሰብ ፣ ሀገር መላው የሰው ዘር ሳይሉ በግለኝነት መገስገስ የዓለም ሁሉ ታሪክ ሆኗል። ታዲያ እርካታን የቱ ጋ ቆማችሁ ትረኩባት? ደስታን ከማን ጋ ሆናችሁ ታጣጥሟት?
የዘመናዊው ስልጣኔ ግብ ገንዘብና ኃይል ነው። ኃይልንና ገንዘብን ቅድሚያ ባደረገ ግስጋሴ ውስጥ ከፍቅር ይልቅ መናናቅ ይንሰራፋል። ከወዳጅነት ይልቅ ጠላትነት ይበረታል። መንፈሳዊ ስልጣኔ የተመሰረተው ፍቅር ላይ ነው። ፍቅር ደግም የሰብአዊነት ቁልፍ ነው። ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት ሰው ራሱን ለፍቅር ያስገዛል። በዘመናዊው ወይም በቁሳዊው ስልጣኔ ውስጥ ያላችሁ ተዋናይነት ያልገዛችሁ እርካታ እና ሰላም በመንፈስ ብትሰለጥኑ ኖሮ ሁሌም ከደጃፋችሁ ይኖራል። ወደ ውስጣችሁ ፣ ወደ መሰረታችሁ በመመለስ ላይ ትጉ። ትናንትን በገነነው ላይ ዛሬ ሌላው ገንኖ፣ የትናንቱን ገናና በማያስረሳው ዓለም አትወናበዱ። ዛሬ ተጨብጭቦለት ነገ በሌላው ጭብጨባ በሚዋጠው ወረተኛ ዓለም አትታለሉ።
ይች ዓለም ምንም ውብና የምታጓጓ መሳላ ብትታያችሁ፤ ጥንት የነገስታትና የባለፀጎች መናኸሪያ የነበራቸው ውቧ ባቢሎንም ከእነጌጧና ስልጣኔዋ ጠፍታለች።
ዛሬ ምስኪንና ተመፅዋች የሆነችው ኢትዮጵያ ለዚህ ሁሉ ችግር መድኃኒትና መፍትሄ ትሆን ዘንድ ነበር ጥንት የተፈጠረችው። ለዚህ በቆዳ ቀለም፣ በዘርና ሀይማኖት ለምታጫረስ ዓለም አንድ የመሆን ምሳሌና መፍትሄ ነበር መሰረቷ። ዛሬ ግን ያን መሆን አልቻለችም። እናንተ ልጆቿ በነፍሳችሁና በማንነታችሁ ላይ በርትታችሁ ስትሰለጥኑ እሷንም ወደ መሰረቷ ትመልሷታላችሁ። ያኔ ዓለም ለኢትዮጲያ ከምትሰጠው በላይ ኢትዮጲያ ለዓለም የምታበረክተው ይበዛል።"
© ዮቶር ( ኮብላዩ ካህን) አለማየሁ ደመቀ
170
2
0
2
last posts shown.
Show more
28
subscribers
Channel statistics