ethiomuslims


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በረመዳን ቁርአንን በቀላሉ ለማኽተም

1ጊዜ ለማኽተም በየ 5 ወቅት ሰላቶች 4ገፅ ማንበብ

2 ጊዜ ለማኽተም በየ 5 ወቅት ሰላቶች 8ገፅ ማንበብ

3 ጊዜ ለማኽተም በየ 5ወቅት ሰላቶች 12 ገፅ ማንበብ

4 ጊዜ ለማኽተም በየ 5ወቅት ሰላቶች 16 ገፅ ማንበብ

5 ጊዜ ለማኽተም በየ5 ወቅት ሰላቶች 20 ገፅ ማንበብ


10 የመልካም ሙስሊም ግለሰብ መገለጫዎች

1 ሰላማዊ እምነት
2 ትክክለኛ አምልኮ
3 ፅኑ ስነ ምግባር
4 ምጡቅ አመለካከት
5 ለጊዜው ጉጉ
6 የተሳለጠ አኗኗር
7 ብርቱ አካል
8 ነፍሱን የሚታገል
9 ለሌሎች ጠቃሚ
10 የምርታማነት ችሎታ


የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 2️⃣2️⃣
⏳ሻዕባን 22፣ 588 ወይም ሴፕቴምበር 2፣ 1192 በሰላሁድ-ዲን አል-አዩቢይና በሪቻርድ ቀልቡል-አሰድ መሀል “ሱልሁል-ረምላህ” (የአሸዋዋ ስምምነት) ተካሄደ። ይህ የሆነውም ሦስተኛው የመስቀለኞች ወረራ አላዋጣ ሲል ነበር። የስምምነቱ ውጤት ክርስቲያኖች ወደ አል-ቁድስ የሚያደርጉት ኃይማኖታዊ ጉዞ በሠላም ማከናወን እንዲችሉና ከሱር እስከ ያፋ የተሰኙት የሻም ሀገርን መስቀለኞቹ እዲያስተዳድሩ መፍቀድ አስችሏል።


የነብያችን (ሰዐወ) ሚስቶች ስም

1 ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ
2 ሰውዳ ቢንት ዘምዓህ
3 ዓኢሻ ቢንት አቢበክር አሲዲቅ
4 ሐፍሷ ቢንት ዑመር
5 ዘይነብ ቢንት ኹዘይማ
6 ኡሙ ሰለማ ሂንድ ቢንት አቢ ኡመያ አልመኽዙሚያ
7 ኡሙ ሐቢባ ረምላ ቢንት አቢ ሱፍያን
8 ጁወይሪያ ቢንት አልሐሪስ
9 መይሙና ቢንት አልሐሪስ አልሂላሊያ
10 ሰፊያ ቢንት ሁየይ ብን አኽጠብ
11 ዘይነብ ቢንት ጀህሽ

ሁሉንም የአማኞች እናት አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው።


10ሩ መላኢካዎች እና ተግባራቶቻቸው

1 ጀብሪል፦ ወደ ነብያት እና መልእክተኞች ወሕይ (ራእይ) በማድረስ ላይ የተወከለ

2 አስራፊል፦ በእለተ ትንሳኤ መለከት (ጥሩምባ) የሚነፋ

3 ሚካኢል፦ በዝናብ ላይ የተወከለ

4 መለከል መውት፦ በአላህ ትእዛዝ የባሮችን ነፍስ በማውጣት ላይ የተወከለ (አጋዦች አሉት)

5 ኪራም አልካቲቡን፦ የባሮችን መልካም እና ክፉ ተግባር የሚመዘግቡ

6 አልሙሰቢሁን፦ ቀን እና ሌት ሳያቋርጡ አላህን በማጥራት የሚያወሱ

7 አሰያሁን፦ አላህ የሚታወሰወበት ፣ ቁርአን የሚነበብበት እና እውቀት የሚስፋፋበት ስብስብ ላይ የሚገኙ

8 የአራህማንን ዓርሽ የሚሸከሙ፦ ብዛታቸው 8 ነው

9 ሙንከር እና ነኪር፦ በቀብር ፈተና ላይ የተወከሉ

10 አልሐፈዟህ፦ ባሮችን ከአደጋ የሚጠባበቁ


🕌ከሸይኽ ጀላሉዲን ሩሚ ትረካዎች🕌

🐥በድሮ ግዜ በአንድ ነጋዴ ቤት የወፎች ማስቀመጫ ፍርግርግ ውስጥ ተቀምጣ በጣፋጭ ድምፅ የምትዘምር ወፍ ነበረች። ነጋዴው በዚህች ወፍ ክፉኛ ሱስ የተያዘ ሲሆን የሷን ድምፅ ሳይሰማ ቀኑን ጤናማ ሆኖ ማሳለፍ ፍፁም አይችልም ነበር። ለርሷ ካለው ፍቅር የተነሳ ውሀ የምትጠጣበትን እንኳ ወርቅማ ሳህን አዘጋጅቶላት ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ታድያ ለንግድ ከአካባቢው ለመውጣት ያስብና ወደ ወፏ ሄዶ «ወፌ አሁን ወደ ተወለድሽበት እና ዘመዶችሽ ወደሚኖሩበት ጫካ መሄዴነው ታድያ ስላለሽበት ሁኔታ ለነርሱ የማደርስልሽ መልእክት ካለሽ አሳውቂኝ።» አላት። ወፏም «ወዳጄ! ዛሬም በተሰበረ ልብ ከፍርግርጉ ጀርባ የምርኮኞችን ዜማ እየዘመርኩ እንደሆነ ንገርልኝ። የነሱን ፊት እስከማይና በነፃነት ክንፎቼን ዘርግቼ አብሬያቸው የምከንፍበትን እለት በጉጉት እንደምጠብቅ አድርሳቸው። ከጣፋጭ የጫካ ህይወታቸው ልቤ የሚያሰክን መልእክት እዳላቸው ይልኩህ ዘንድ አደራ በላቸው። ወዳጄ! ወገኖቼ እንዴት እንደናፈቁኝ እና ምርኮኛ ክንፎቼ ከነሱ ጋር መብረር ምን ያክል እንደሚመኙ አታውቅም!! እስከዚያ ድረስ ግን ራሴን ከማንኛውም ጣፋጭ በሙሉ ማግለሌን ንገራቸው።» ብላ መለሰችለት። ነጋዴው የሰጠችውን መልእክት ይዞ ጉዞውን ጀመረ። ጫካ እንደደረሰ ድምፁን ከፍ አድርጎ «ወፎች ወፎች» ብሎ ተጣራ። ሲሰበሰቡ ወፊቱ የነገረችውን መልእክት አንድ በአንድ ነገሯቸው «እናንተስ እንዳድርስላችሁ የምተፈልጉት መልእክት አላችሁ?» ብሎ ጠየቃቸው። መልእክቱን ሲያዳምጡ ከነበሩት ወፎች መካከል አንዱ ከነበረበት ቅርንጫፍ ድንገት ተምዘግዝጎ ወድቆ ፀጥ አለ። ሞተ። ነጋዴው ያየውን ማመን አልቻለም። በድንጋጤ ልቡ እየዘለለች ወደ ቤቱ ተመለሰ። ቤቱ ሲደርስ መልእክት የላከቸው ወፍ የላኩላትን መልእክት ለማድመጥ በጉጉት እየጠበቀችው ነበር። ጨነቀው። ምን ብሎ ይንገራት!? ቤት ውስጥ ዝም ብሎ ወደ ቀኝና ግራ እየተንጎራደደ ለረዥም ሰአታት ቢቆይም ወፊቱ የላኩላትን መልክት እንዲነግራት ከመወትወት ለደቂቃ እንኳ አላረፈችም። «እባክህን ምን እንዳሉህ ንገረኝ» ወፊቱ ጠየቀቸው። «ተይው ባክሽ ምንም አይጠቅምሽም።» ነጋዴው መለሰላት። «እባክህን ምን እንዳሉህ የግድ ልትነግረኝ ይገባል።» ለመነችው። አማረጭ አልነበረውም «እየውልሽ···ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ግን የላክሽላቸውን መልእክት አድምጠው እንደጨረሱ ከመካከላቸው አንደኛው ወፍ ከቅርንጫፍ ወርድቆ ሞት» በሰቀቀን መርዶውን ነገራት። ንግግሩን እንደጨረሰ ወፊቱ በቁሟ ድፍት ብላ ፀጥ አለች። ነጋዴው ልቡ ትርትር እስኪል ደነገጠ። ለራሱ «ምንድነው የሰራኸው አንተ ሰው! ምንድነው ያደረከው!? ትናንት ወገኖቿን ዛሬ ደግሞ የራስህን ወዳጅ ገደልካት!···» እያለ የነበረችበትን የብረት ፍርግርግ ከፍቶ በእጁ ተሸክሞ አወጣት። «አይዞሽ ወዳጄ በክብር እያጫወትሽ እንዳኖርሽኝ በክብር ቆፍሬ እቀብርሻለው» ብሎ በጥንቃቄ መዳፉ ላይ አሳርፎ ልክ የቤቱን በር ሲከፈት ከእጁ ብር ብላ አፈተለከች። ያየውን ማመን አቃተው። ወፏ በአየር ላይ እንዳለች «አሳዳሪዬ መልእክቴን ስላደረስክልኝ በጣም አመሰግናለሁ። ወገኖቼ የላኩህ መልእክት እንዴት ዘዴ ተጠቅሜ ከፍርግርጉ ማምለጥና በነፃነት መኖር እንደምችል ነበር። በቃ የሞተ መምሰል። ይሄው ነው ዘዴው። ያኔ ራስህ ትለቀኛልህ። በል ደህና ሁን።» ብላው ወደ ጫካው ከነፈች።
አጂብ🤔


የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 2️⃣1️⃣
⏳ሻዕባን 21፣ 1208 እንደ ሒጅራ ወይም እ.አ.አ. ጁላይ 25፣ 1793 ታላቁ የአዝሐር ሼኽ ኢማም አሕመድ አልዓሩሲ አረፉ። ሰውየው በአዝሀር ሸይኾች ዝርዝር ውስጥ አስራአንደኛው ሼኽ ናቸው። ሼኹ ጀግንነታቸውን ባንጸባረቁ አጋጣሚዎቻቸው ይታወቃሉ። በአንዳንድ ንጉሶች በደል ያረረውን ህዝብ በመርዳት ይታወቃሉ። የዒልም መድረክ ላይም ጎልተው የሚታዩባቸው መጽሐፍትም አሏቸው። ከነዚህም መሀል “ሙኽተሰሩል-ዓሩሲ ፊል ፊቅህ” የታወቀ ነው።
⏳ሻዕባን 21፣ 489 እንደ ሒጅራ ወይም ኦገስት 15፣ 1096 የአውሮፓው ጳጳስ የመስቀል ጦረኞች ቆስጠንጢኒያ ላይ እንዲሰበሰቡ ቀጠሩ። ጥሪው ምስራቁን የሙስሊሙን ሀገር (ሶሪያ፣ ዒራቅ፣ ፊሊስጢን፣ ሊባኖስ) ለመውረርና አልቁድስን ከሙስሊሞች እጅ ለመመንጠቅ የሚደረግ ዝግጅት ለማድረግ ያቀደ ነበር።
⏳ሻዕባን 21፣ 559 ወይም ጁላይ 19፣ 1164 ሰላሁድ-ዲን አል-አዩቢይ ሑምስን ከመስቀለኞች እጅ የመነጠቀበት ቀን ነበር። ይች ቦታ እስትራቴጂካዊ ሚና ስለነበራትም ሌሎች የአካባቢው ቦታዎች ከእጁ ወድ
ቀዋል።


የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 2️⃣0️⃣
⏳ሻዕባን 20፣ 852 (ሒጅራ) ወይም ኦክቶበር 19፣ 1448 (እ.አ.አ.) የዑስማኒያው ሱልጣን ሙራድ ሁለተኛው ክርስቲያናዊውን የአውሮፓ ሠራዊት አሸንፏል። አውሮፓዎቹ መቶ ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችን በዚህ ጦርነት ላይ አሰልፈዋል። ውጊያው የተካሄደውም ኮሶቮ ውስጥ ነበር። ሦስት ቀን ከፈጀ ውጊያ በኋላ 17 ሺህ የሚሆኑ አውሮፓዊያን ተገድለውበት ጦርነቱ ተጠናቋል። ይህ ውጊያ አውሮፓዎች ዑስማኒዮችን ከአውሮፓ ለማስወጣት ካደረጓቸው ዘመቻዎች መካከል ስድስተኛው ነበር። ነገር ግን አልተ
ሳካም።


እድሜው የገፋ ባለፀጋ ህይወት ምን እንዳስተማራቸው ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ ነበር ምላሽ የሰጡት

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ ተበዳይ ጊዜው ቢዘገይም ድል እንደሚያደርግ ነው

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ በሌሊት የተደረገች ፀሎት ማረፊያዋ ቅርብ እንደሆነ ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ በየትኛውም አጋጣሚ እንደተዘናጋን ህይወታችን ልትጠናቀቅ እንደምትችል ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ ገራገር ልቦና ፣ ለዘብተኛ ንግግር እና ቸርነት የስነምግባር ካፒታል መሆኑን ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ የአለማችን ሀብታም ጤና እና ሰላም የሰፈነበት ኑሮ ያለው ሰው እንደሆነ ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ መርዝ ዘርቶ መድሀኒት ማጨድ እንደማይቻል ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ የህይወት ውጣውረድ ሳይጠናቀቅ እድሜ እንደሚቋጭ ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ ሰዎች እንዲሰሙት የፈለገ ሰዎችን መስማት እንዳለበት ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ ከሰዎች ጋር መንገድ መጓዝ የተደበቀ ማንነታቸውን ለመረዳት አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ እኔ እና እኔ የሚል ፍልስፍና የሚያበዛ ሰው ውስጡ ባዶ መሆኑን ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ ውስጥ በወርቃማ ስብእና የተገነባ በየጊዜው እያንፀባረቀ ሲጎላ ውስጡ እንደብረት የጠጠረ እየዛገ እንደሚሄድ ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ የሞቱ ሰዎች ሁሉ ምኞታቸውን ያልጨረሱና ቀጠሮ የነበረባቸው እንደሆኑ ነው።

ህይወት ያስተማረችኝ ፦ ለትንሿ ሞታችን እንቅልፍ እንኳ አልጋ ማነጠፍ እና ብርድልብስ ማጠብ እንደሚያስፈልገን ነው።

ሰዎች ሆይ! ስለትልቁ ሞት ግን ምን ያክል ዝግጅት አድርገን ይሆን?

ከደጋግ አባቶቻችን አንዱ እንዲህ ይሉ ነበር
«ሰዎች በሽታን ፍራቻ የተወሰኑ ምግቦችን ሲጠነቀቁ እሳትን ፍራቻ ከወንጀል አለመጠንቀቃቸው ያስገርመኛል!!»


የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 1️⃣9️⃣
⏳ሻዕባን 19፣ 1413 እንደ ሒጅራ ወይም እ.አ.አ ፌብራሪ 12፣ 1993 ታላቁ የሐዲስ ምሁር ዐብዱላህ ቢን ሙሐመድ አል-ጉማሪይ አረፉ። እኚህ ሰው የዘመናቸው ትልቅ የሐዲስ ሐፊዝና የብዙ መፅሐፍት ባለቤት
ናቸው።


የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 1️⃣8️⃣
⏳ሻዕባን 18፣ 967 (ሒጅራ) ወይም ሜይ 14፣ 1560 (እ.አ.አ.) ባለልዩ ተልእኮ፣ በጠርገድ ባሻ የሚመራው የዑስማኒያዎች ሠራዊት ልዩ ወታደራዊ ተልእኮ ያለው መስቀለኛው የእስፔን ሠራዊት ላይ ቱኒዚያ አካባቢ በምትገኘው “ጂርባ” በምትሠኘው ሥፍራ ላይ ድል ተቀዳጅቷል። በዓለማችን ልዩና በታላቅነቱ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዝ የባህር ጦርነት ነበር። በጦርነቱ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑ የእስፔን የባህር ተዋጊዎች ተገድለዋል። ከዑስማኒዮች በኩል ግን አንድ ሺህ የሚሆኑ ሸሂዶች ብቻ ነበር የተ
ገኙት።


ብን ዑመር እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ·ዐ·ወ) እንዲህ ብለዋል ፦ «በመዲና ውስጥ መሞት የቻለ ሰው በርሷ ውስጥ ይሙት። እኔ በርሷ ውስጥ ለሚሞቱት አማላጅ ነኝና» ቲርሚዚ ዘግበውታል


ጌታህ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ከሚሰጡት ጎደሎ ባህሪት የፀዳ ነው፡፡ የአላህ ሰላም በመልእክተኞች ሁሉ ላይ ይሁን፡፡ ምስጋና ሁሉ ለአለማቱ ጌታ አላህ ብቻ ነው፡፡


የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 1️⃣6️⃣
⏳የዑስማኒያው ሱልጣን ዓብዱልሐሚድ ሁለተኛው ሻዕባን 16፣ 1258 ላይ ተወለዱ። ይህ ቀን ከሴፕቴምበር 22፣ 1842 ጋር ይጋጠማል። ኸሊፋነታቸው ሳይወድም እና ፀሐያቸው ከመጥለቋ በፊት ካለፉት የዑስማኒያ ነገስታት ዝርዝር ውስጥ ከታላላቆቹ ጋር የሚመደቡ ሰው ናቸው። ለሠላሳ አንድ አመታት የቆየው ስልጣናቸው በታላላቅ ክስተቶችና ድሎች የተሞላ ነበር። ኢምፓየሩን ከመበታተን በማዳናቸው ይታወቃሉ።


አልላሁምመ ሰሊ ዐላ ሰይዪዲና ሙሀመዲን ዐብዲከ ወረሱሊከ ንነቢይዪል ኡሚዪ ወዐላ ኣሊሂ ወሰህቢሂ ወሰልሊም ተስሊመን ዐደደ ማ አሃጠ ቢሂ ዒልሙከ ወኸጥጠ ቢሂ ቀለሙከ ወአህሳሁ ኪታቡከ፣ ወርደልላሁምመ ዐን ሳዳቲና አቡ በክር፣ ወዑመር፣ ወዑስማን፣ ወዐሊይይ፣ ወዐኒስሰሃበቲ አጅመዒን፣ ወዐኒ ትታቢዒነ ወትታቢዒሂም ቢኢህሳኒን ኢላ የውሚድዲን ፡፡

አላህ ሆይ በባሪያህ፣ በመልክተኛህ፣ በኚያ መፃፍና ማንበብ በማይችሉት መሪያችን ሙሀመድ ላይ እዝነትህን አውርድ፡፡ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸውም ላይ እንዲሁ እዝነትህን አውርድ፡፡ እውቀትህ ያካበበውን ያህል፣ ቀለምህ የከተበውን ያህል፣ መፅሀፍህ ያሰፈረውን ያክል ሰላምም አውርድ፡፡ የመሪዎቻችንን የአቡበክር፣ የዑመር፣ የኡስማንን፣ የሰሃቦችን በሙሉ እንዲሁም እስከ ትንሳኤ በመልካም ስራ የተከተሏቸውን ሁሉ መልካም ስራ ተቀበል፡፡


የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) የስንብት ቃል


የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 1️⃣5️⃣
⏳ሻዕባን 15፣ 1294 (ሒጅራ) ወይም ኦገስት 25፣ 1877 (እ.አ.አ.) የዑስማኒያው የጦር መሪ አሕመድ ሙኽታር ባሻ የሩሲያውን ጦር “ኩድክለር” በተሠኘው የጦር አውድማ አሸንፎታል። በዚህ ድል የተነሳ “ጋዚ” ወይም “ዘማቹ” የሚል ማእረግ ከዑስማኒያው ሱልጣን “ዐብዱልሐሚድ ሁለተኛው” ተበርክቶለታል። አሕመድ ሙኽታር ባሻ ሩሲያዎችን ከዚህ ውጭም በተለያዩ የጦር አውድማዎች ላይ ተደጋጋሚ ድሎችን ተጎናጽፏል።
⏳ሻዕባን 15፣ 476 ሒጅሪያ ወይም እ.አ.አ. ዲሴምበር 28፣ 1083 ላይ ታላቁ ዓሊም አቢል ፈድል ዒያድ ኢብኑ ሙሳ አል-የሕሶቢይ አል-ሲብቲይ ተወለዱ። ቃዲ ዒያድ የሚታወቁበት ሥማቸው ነው። የምዕራቡ (ሞሮኮ) ሐፊዝ ናቸው። ከአምስተኛውና ስድስተኛው ምእተአመት (እንደ ሒጅራ) ታላላቅ የዒልም ሠዎች ይመደባሉ። ፊቅህ፣ ሐዲስ፣ ታሪክ እና ሌሎችም የእውቀት ዘርፎች ላይ የፃፏቸው መጽሐፍት ታላቅነታቸውን ይመሰክራሉ። ከእነዚህ መሐል “መሻሪቁል አንዋር” እና “ኢልማዕ” ምርጦቹና የታወቁት ናቸው።
⏳ሻዕባን 15፣ 1217 እንደ ሒጅራ ወይም እ.አ.አ. ዲሴምበር 11፣ 1803 ታላቁ ኢማም አቢስ-ሰናእ ሺሀቡድ-ዲን መሕሙድ አል-አሉሲይ ተወለዱ። አስራ ሶስተኛው ምእተአመት ሒጅሪያ ላይ ከነበሩት ታላላቅ ኢማሞች ይቆጠራሉ። “ሩሑልመዓኒ” የተሰኘው የቁርአን ማብራሪያ (ተፍሲር) ከመጽሐፍቶቻቸው መሀል የአሉሲይን ታላቅነት ይጠቁማል።


አላህ ሆይ ከጉድለት የጠራህና ምስጉን ነህ፡፡ ከአንተ ውጭ ለአምልኮ ተገቢ የሆነ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፡፡ ምህረትህን እሻለሁ ወደ አንተም እመለሳለሁ፡፡


👰‍♀የተዘነጉ የትዳር መደጋገፎች🤵

ለመሆኑ በነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ሱና የትዳር ግንኙነት ምን ይመስላል?
🎁 ለባለትዳር አጋር ፈገግታ መለገስ
የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል «በወንድምህ ፊት የምታቀርበው ፈገግታ😃 ሰደቃ ነው።» (ሰሂህ አቲርሚዚ 1956)
ለትዳር አጋር በበለጠ ፈገግታ የሚገባው አካል አለን?
🎁 ፍቅርን በጉርሻ መግለፅ
የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል «አንድንም ወጪ (ለአላህ ብለህ) አታወጣም የምትመነዳበት ቢሆን እንጂ። በሚስትህ አፍ የምታሳርፋት ጉርሻም🥘 ብትሆን።» (ቡኻሪ እና ሙስሊም)
🎁 ከኩባያ የተረፈውን በመጎንጨት
እሜት አኢሻ እንዲህ ይላሉ «የወርአበባ በሆንኩበት ጊዜ (እንኳ) ጠጥቼ ስጨርስ ለነቢዩ (ሰ ዐ ወ) አቀብላቸዋለሁ። ከናፍሮቼ 💋 ያረፉበት ቦታ ላይ አፋቸውን አድርገው ይጎነጫሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)
🎁 እጉያ ላይ መንተራስ
እሜት አኢሻ እንዲህ ብለዋል «እኔ የወር አበባ ሆኜ (እንኳ) ጉያዬ ተሸጉጠው (ታፋዬን ተንተርሰው) ቁርአን ያነበንቡ ነበር።» (ቡኻሪ እና ሙስሊም)
🎁 በአንድ እቃ ላይ ገላ 🛁 መታጠብ🚿
ከእሜት አኢሻ ፣ ከእሜት መይሙና እና ከኢብን ዑመር በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ከባለቤታቸው ጋር በአንድ ሳፋ 🛁 ይታጠቡ ነበር። (እንዲያውም ውሀውን) አትጨርሺብኝ ሲሏት ሂይ አንተም ውሀዬን አትጨርስብኝ ትላቸው እንደነበር ተዘግቧል። (ቡኻሪ እና ሙስሊም)
🎁 መጫወት እና መቀላለድ
የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ «የምታጫውታት እና የምታጫውትህን ድንግል ሴት አታገባም ነበርን?» 💏
እሜት አኢሻ አንዳስተላለፉት ከአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) ጋር መንገድ ወጥተው ሲመለሱ ሶሀቦቻቸውን «ተቀደሙ» ብለው ከአኢሻ ጋር የሩጫ ውድድር እንደተጫወቱ ተዘግቧል። (ሲልሲለቱ ሰሂሀ 1/25)
🎁 በቤት ስራዎች ላይ ማገዝ
እሜት አኢሻ የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) ቤት ውስጥ ምን እንደሚሰሩ ተጠይቃ «እንደማንኛውም ግለሰብ ነበሩ። ልብሳቸውን እየሰፋ ፤ ፍየሎችን እያለቡ እራሳቸውን ይኸድሙ ነበር።» ብላለች። (ሰሂህ አዳቡል ሙፍረድ 4996)
🎁 አፍን ለትዳር አጋር ሲባል ማፅዳት😁
እሜት አኢሻ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ቤታቸው እንደገቡ የሚያስቀድሙት መፋቂያን ነበር። (ሙስሊም)
🎁 ውበትን መጠበቅ እና መኳኳል
ኢብን ዓባስ እንዲህ ይሉ ነበር «እርሷ እንድትዋብለኝ😍 የምወደወን ያክል እኔም እዋብላታለሁ።» (ሙሰነፍ አቢ ሸይባ)
🎁 በትዳር አጋር በሚወደድ ስም መጠራራት እና መንቆለጳጰስ
የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) «አኢሹ ያ ጅብሪል ነው። ሰላምታ እያቀረበልሽ ነው።» ይሏት ነበር። (ቡኻሪ እና ሙስሊም)
አንዳንድ ግዜም «ቀዩቲ» ብለው ያንቆለጳጰሷት ነበር።❤️ (ሲልሲለቱ ሰሂሀ 7/818)
አንድ ቀን እሜት አኢሻ «እኔ ብቻ ስቀር ሁሉም ሚስቶችህ ተቀፅላ ስም አላቸው።» በማለቷ «ኡሙ ዓብደላህ» ብለው ተቀፅላ ስም አውጥተውላታል። (ሲልሲለቱ ሰሂሀ 1/255)
🎁 ከፊል ጉድለትን እንዳላየ ማለፍ
የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል ፦ «አንድ አማኝ አማኚትን አይጥላ። አንድ ባህሪዋን ቢጠላ (በእርግጠኝነት) ሌላኛውን ይወድላታልና።» (ሙስሊም)
🎁 እንባን ማበስ እና ማፅናናት
አነስ በዘገቡት ሀዲስ እሜት ሰፊያ ከነቢዩ ጋራ መንገድ ወጥታ በጉዞ ወደ ኋላ በመዘግየቷ እያነባች😭 «በቀርፋፋ ግመል ነው ያመጣኸኝ» ስትላቸው  በእጃቸው አይኖቿን እያባበሱ ያባብሏት ጀመር… (ነሳኢ ሶሂህ ብለውታል)
🎁 ንጭንጭን😤 በታጋሽነት ማሳለፍ
ኡመር ኢብን ኸጧብ እንድህ ይላሉ «ባለቤቴን ስቆጣት መልስ ሰጠችኝ። ለኔ መልስ መስጠቷን ሳግዝባት «ለአንተ መልስ መስጠቴን ለምን ትኮንናለህ? በአላህ ይሁንብኝ የአላህ መልእክተኛ ባለቤቶች እንኳ ለርሷቸው ምላሽ ይሰጡ ነበር!» አለችኝ…» (ቡኻሪ)
🎁 ምግብን አለማነወር🤫
አቢ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) ምግብን አነውረው አያውቅም።ከወደዱት ይመገቡታል። ከጠሉት ደግሞ ይተውታል።
🎁 ስለውለታ 👍ምስጋና ማቅረብ
የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል «ሰዎችን የማያመሰግን አላህንም አያመሰግንም።»
🎁 የትዳር አጋር ቤተሰብ እና ጓደኛን ማክበር
እሜት አኢሻ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ በግ ያረዱ ጊዜ ለኸዲጃ ጓደኞችን ተከታትለው ስጦታ ይልኩላቸው ነበር። (ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል)
🎁 ፍቅርን መናገር
እሜት አኢሻ ስለ አቡ ዘር ባለቤትን ጥሩ አያያዝ መያዝ ተናግራ እንደተፋቱ ለነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ስታሳውቃቸው «እኔ ለአንቺ (በአያያዜ) እንደ አቡ ዘር ነኝ። እርሱ ቢፈታትም እኔ ግን አልፈታሽም።» ብለዋታል። (ቡኻሪ)
🎁 ለችግር🤕 እና ህመም🤒 ደራሽ መሆን
እሜት አኢሻ ስለ ሀዲሱል ኢፍክ ስትናገር የአላህ መልእክተኛ (ወሬው ከመነዛቱ አስቀድሞ) ስታመም የሚያዝኑልኝ እና የሚራሩልኝ ነበሩ። ያኔ ግን «እሷስ እንዴት ናት» ከሚል ውጪ አይጨምሩም ነበር። (ቡኻሪ)
🎁 አላህን በመታዘዝ ላይ መተጋገዝ
የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል «ባለቤቱን ለሌሊት ሰላት የሚቀሰቅስ እና እምቢ ስትለው ፊቷን ውሀ የሚረጫት ሰው አላህ ይዘንለት። (እሷም) ባለቤቷን ለሌሊት ሰላት የምትቀሰቅሰው እና እምቢ ሲላት ውሀ የምትረጨው እንደሆነ አላህ ይዘንላት።» (አቡዳውድ ሶሂህ ብለውታል)
🎁 ቃል ኪዳንን መፈፀም
የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) «ሰውየው (ከመንገድ) በሌሊት ቤቱ እንዳይዘልቅ ፣ እንዳይክዳችው(ቃሉን እንዳያፈርስ) እና ነውራቸውን እንዳያነፈንፍ ከልክለዋል።» (ሙስሊም)
🎁 ከቤት መውጣት ሲሹ አስቀድሞ መሳም😘
እሜት አኢሻ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) አንዷን ባለቤታቸውን ስመው ውድ ሳያደርጉ ሰግደዋል። (አቡዳውድ ዘገባውን ጠንካራ ነው ብለዋል)


የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 1️⃣4️⃣
⏳ልክ ሻዕባን 14፣ 1402 ወይም ጁን 6፣ 1982 የኢስራኤል ሀይሎች በመከላከያ ሚኒስትራቸው ኤሪያል ሻሮን መሪነት ወደ ሊባኖስ ምድር ዘመቱ። ከዚያም መጠነ ሰፊ የዘር ጭፍጨፋ በሊባኖስ ምድር ሰብራና ሻቲላ የተሰኙ ስፍራዎች ላይ አደረጉ። ፊሊስጤማዊያን ነበር በግፍ የታረዱት። የጭፍጨፋው አጸፋም ሒዝቡላህ በሙሐመድ ሐሠን ፈድሉላህ እጅ ተመሠረተ። ትግሉንም ጀመረ። ከዚያም ብዙውን የደቡብ ሊባኖስ ምድር አስለቀቀ። በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ኢስራኤል ከፍተኛ ኪሳራ ገጥሟታል። ዘጠኝ መቶ ወታደሮቿን አጥታለች። ደም አይለቅም እና ደም ለማፍሰስ እንደወጡ ቀሩ።

20 last posts shown.

374

subscribers
Channel statistics