ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን በምን አይነት መንገድ ነው ማሳረፍ የሚኖርብን?
--------------
ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ
መንቀራፈፍ ይጀምራል።
በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም
ማሳረፍ ያስፈልጋል።
ኮምፒውተራችን “ተርን ኦፍ”፣ “ስሊፕ” አልያም “ሀይበርኔት” በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ
ማድረግ እንችላለን።
ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው።
እናም ከዚህ በታች ስለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች እና ጉዳቶች
በዝርዝር እንመለከታለን።
“ስሊፕ”
በቀደሙ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ “ስታንድ ባይ”
የሚል ስያሜ የነበረው “ስሊፕ” የኮምፒውተራችን የሀይል ፍጆታ የሚቀንስ ነው።
ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል።
የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ
ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ስራ በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል።
ይሁን እንጂ ስሊፕ ማድረግ ከሸት ዳውን እና ሃይበርኔት የበለጠ ሀይል ይወስዳል። በመሀል
የሀይል መቋረጥ ከተከሰተም ሴቭ ሳናደርግ የተውናቸው ስራዎች ሊጠፉ ይችላሉ።
በመሆኑም ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ከማድረጋችን በፊት የተጀመሩ ስራዎችን ሴቭ
ማድረግ ተገቢ ነው።
“ሸት ዳውን”
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው “ሸት ዳውን” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም
ነው።
በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል፤ የራም (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል፤
በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም።
በ”ሸት ዳውን” የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም።
ይሁንና ኮምፒውተራችን በድጋሚ ስንከፍት ዘለግ ያለ ጊዜ (ከ“ስሊፕ” አንፃር) ይወስዳል።
“ሀይበርኔት”
ይህ አማራጭ ደግሞ በ”ስሊፕ” እና በ”ሸት ዳውን” መሀል የሚገኝ ነው።
“ሀይበርኔት” ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን
ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ።
ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን፥
ከ“ስሊፕ” አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ነገር ግን ስሊፕ ያደረግነውን ኮምፒውተር
ስንከፍት ከሚወስደው ጊዜ ዘግየት የማለት ባህሪ አለው።
በሀይበርኔትም ሆነ “ሸት ዳውን” ኮምፒውተራችን ስናጠፋ እና ስንከፍት የምንጠቀመው
ሀይል ተመሳሳይ ነው።
ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ “ሀይበርኔት” ተመራጭ ነው።
መቼ ነው “ስሊፕ”፣ “ሸት ዳውን” ወይም “ሀይበርኔት ማድረግ የሚኖርብን?
በቀን ውስጥ ለተከታታይ ስአታት ኮምፒውተራችንን የምንጠቀምበት ከሆነ ሙሉ በሙሉ
ማጥፋት (ሸት ዳውን) አይጠበቅብንም።
ይሁን እንጂ በቀን ውስጥ ለአንድ ስአት አልያም ለሁለት ስአት የምንጠቀም ከሆነ ሙሉ
በሙሉ ቢጠፋ መልካም ነው።
“ስሊፕ”
ካቆምንበት በአጭር ጊዜ ተመልሰን ስራችንን ለመቀጠል “ስሊፕ” ተመራጭ ነው።
“ስሊፕ” ስናደርግ ኮምፒውተራችን በፈለግነው ቅፅበት ዝግጁ ይሆናል።
“ሸት ዳውን”
ለስአታት አልያም ለቀናት ኮምፒውተራችን እንዲያርፍ ስንፈልግ ደግሞ “ሸት ዳውን”
ማድረጋችን መዘንጋት የለብንም።
በርካታ ሰዎች የዘጉት ኮምፒውተር በፍጥነት እንዲከፈት በማሰብ “ሸት ዳውን” ከማድረግ
ይልቅ “ሀይበርኔት”ን ይመርጣሉ።
ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች ከ”ሀይበርኔት” መልስ ተግባራቸውን
በአግባቡ ማከናወን ሊሳናቸው ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም “ሸት ዳውን”
ማድረጉ ተመራጭ ነው።
“ሀይበርኔት”
ከ“ስሊፕ” ይልቅ “ሀይበርኔት” ሀይል በመቆጠብ ረገድ የተሻለ ነው።
ረዘም ላለ ስአታት የጀመርነውን ስራ ማቋረጥ ከፈለግን “ሀይበርኔት” ማድረግ ይመከራል። ለምሳሌ ለእንቅፍል ወደ መኝታ ክፍላችን ስናመራ።
“ሀይበርኔት” የኤሌክትሪክ ሀይልን እና የኮምፒውተር ባትሪን ሀይል ለመቆጠብ ይረዳል።
ነገር ግን ሀይበርኔት ያደረግነውን ኮምፒውተር ስንከፍት ጥቂት ጊዜ ይወስዳል።
በአጠቃላይ ኮምፒውተራችን እንደምንጠቀምበት አግባብ የእረፍት ጊዜ እነዲኖረው ከላይ
የጠቀስናቸውን ማሳረፊያዎች መጠቀም ይገባል።