#በቃ_ምንም_ብታደርግ_ሰዎች ከማውራት አይመለሱም
➊.ደሀ ብትሆን→የመናጢ ልጅ፣
➋.ሀብታም ብትሆን→ዶላር ያሳበጠው፣
➌.ከሴት ጋር ብትሄድ→ሴሰኛ፣
➍.ብቻህን ብትሆን→ወፈፌ
➎.ብትፈጥን→ቀዥቃዣ፣
➏.ብትዘገይ→ዘገምተኛ፣
➐.ብታወራ→ለፍላፊ፣
➑.ዝም ብትል→ዝጋታም፣
➒.ብትራመድ→አርፎ አይቀመጥም፣
➓.አርፈህ ብትቀመጥ→ዝፍዝፍ፣
➊➊.ብትማር→አወቅሁ ባይ፣
➊➋.ባትማር→የአቡጊዳ ሽፍታ፣
➊➌.ብትወፍር→ጠብደል፣
➊➍.ብትከሳ→በልቶ ማይጠረቃ፣
➊➎.ብትይዝ→ቋጣሪ፣
➊➏.ብትለቅ→መንዛሪ ይሉሀል።
:
ስለዚህ ዝምታ የአዋቂዎች ጥሩ ምላሽ ናትና በዝምታ ማለፍን ልመድ።
፡
❀︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵❀
:
#ስማኝ ወዳጄ፥
፡
☞«ምቀኛና ሸረኛ ሰው የራሱን እንጀራ መጋገር ሲያቅተው የሌላውን ሰው ሊጥ ደፍቶ ያጨማልቃል» የሚባለው የሀገራችን አባባል እውነትነት አለው።
:
#ወዳጄ ልብ በል፥
:
➊.የሰው ልጅ እኮ አዝነህ ብታዝለው እግሬ ለምን ተንጠለጠለ? ብሎ ነገር የሚፈልግህ ፍጡር ነው።
፡
➋.ለጮኸ ውሻ ሁላ ድንጋይ መወርወር ጊዜን ማባከን ነው፡፡
:
➌.ስለዚህ ሰዎች ያሉትን ይበሉ አንተ አንተነትህን ሁንና ህሊናህ አውጥቶና አውርዶ ከተቀበለው ሀሳብ ጋር ተስማማ።....አበቃሁ
:
"በማስተዋል ያቆየን" 😍😍😍 ❀︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵❀
#share
Join
@Starmeznagnatm@Abreninisak