🤣🤣ከተጠነሰሰ 3 ወሩ ነው😂😂
አልኮል ፋብሪካ ውስጥ የነበረ አልኮል ቀማሽ ይሞትና ማናጀሩ አዲስ ቀማሽ ለመቅጠር ክፍት የስራ ማስታወቂያ ያወጣል::
አንድ በጣም የሰከረና ድሪቶ የለበሰ ሰው ማስታወቂያውን አይቶ ሊፈተን ይመጣል:: ማናጀሩ ገና እንዳየው የሰውዬው ሁኔታ ይደብረውና ላለመቅጠር ወስኖ በከባድ ጥያቄ ሊያባርረው ይወስናል::
በብርጭቆ የተሰጠውን አልኮል ምንነት በመቅመስ እንዲለይ የመጀመሪያው መጠጥ ተሰጠው::
ሰውየው መጠጡን ቀመሠና :-
*ቀይ ወይን ነው::•
የተሰራው ከነጭ የወይን ፍሬ ነው::
*ከተጠነሰሰ 3 ዓመቱ ነው:: *በደቡብ ሸለቆ ውስጥ በብረት በርሜል የተጠመቀ ነው ሲል መለሰ::
ማናጀሩ በመልሱ ፍፁም ትክክለኛነት ተደንቆ ሌላ ብርጭቆ ሰጠው::
ይህንንም ቀመሠና:-
* ከደረቅ ቀይ ወይን የተሰራ ነው::* ከተጠነሰሰ 8 ዓመቱ ነው:: * በደቡባዊ ፈረንሳይ *በእንጨት በርሜል የተጠመቀ ቀይ ወይን ነው" አለ::
ማናጀሩ ገርሞት ቢሮ ውስጥ የሚያሽኮረምማትን ፀሐፊ ጠርቶ ያንሾካሹክላታል:: እሷም ወጣ ብላ ሽንቱዋን በብርጭቆ ይዛ ትመጣና ትሰጠዋለች:: ተፈታኙም ይቀምሰውና:-
* ብሎንዲ /ቢጫ ነገር/ ነው:: * ከተጠነሰሰ 3 ወሩ ነው:: *የተሠራው ቢሮ ውስጥ ነው:: ካልቀጠርከኝ ደግሞ አባትዬውንም /የፅንሱንም አባት/እናገራለሁ ብሎ ቁጭ.. . 🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣
🤣ዝገት ከኔጋር😂