በሶማሊላንድ እና ሶማሊያ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት እና ዛቻ እየተፈጸመ መሆኑን ዜጎች ተናገሩ!
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባሕር ጠረፍ ያስገኛል የተባለውን የመግባቢያ ሠነድ መፈራረማቸውን ተከትሎ በሶማሊያ እና ሶማሊላንድ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ አካላዊ ጥቃት እና የንብረት ዝርፊያዎች እየተፈጸሙ መሆኑን እንዲሁም ማስፈራሪያዎች እየደረሱ እንደሆነ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ተናገሩ።
በተለይ በሶማሊላንድ በኢትዮጵያውያን ላይ አካላዊ ጥቃት መፈጸሙን፣ ንብረታቸው መዘረፉን እና መኖሪያ ቤታቸውን ለማቃጠል ሙከራ መደረጉን የስደተኞች ተወካይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።በሶማሊያም በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የሚጠይቁ ቅስቀሳዎች መኖራቸውን ኢትዮጵያውያኑ በተለይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ራስ ገዝነትን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ማግኘት የሚያስችላትን የመግባቢያ ሠነድ ታኅሣሥ 22/2016 ዓ.ም. መፈራረሟ ይታወሳል።ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ለወደብ እና ለጦር ሠፈር ልማት የሚውል 20 ኪሎ ሜትር የባሕር ጠረፍ እንድታገኝ ያስችላታል የተባለ ሲሆን፣ በምላሹ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ እንዲሁም እንደ አገር ከአዲስ አበባ እውቅና እንደምታገኝ ተዘግቧል።
ታዲይ ይህን ስምምነት የአዲስ አበባ እና ሐርጌሳ መንግሥታት ታሪካዊ ብለው ቢያወድሱትም በሐርጌሳ እና ሞቃዲሹ የተለያዩ ስሜቶችን አስተናግዷል።ስምምነቱ ከሶማሊያ በኩል በአገሪቱ አስተዳደር ጠንካራ ትችት የቀረበበት ሲሆን፤ በአንዳንድ የሶማሊያ ከተሞችም ስምምነቱን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፎች በስፋት ተካሂዷል።
@hulumedia1