ሰበር መረጃ - ከባህር ዳር
በጎጃም ዕዝ የባህር ዳር ፋኖ ስር ሁለት ሻምበሎች ታሪካዊ ስያሜን ይዘው መመስረታቸው ታውቋል።
1. አንሻ ሰይድ ሻምበል - በጀግናዋ እህታችን ፋኖ ህይወት ጌራ የሚመራው ይሆናል። ይህ ሻምበል ስያሜውን በወለጋ ክልል ቤተሰቦቿን የኦነግ ታጣቂዎች በማጨፍጨፍ ላይ እያሉ እራሷን ለማትረፍ "ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም፤ አትግደሉኝ" በማለት በተማፀነችው ህጻን አንሻ ሰይድ የተሰየመ መሆኑ ታውቋል።
"አንሻ ሰይድ የትግላችን ቃል ኪዳን ሆና፣ ታናናሾቿ በማንነታቸው ኮርተውና ተከብረው የሚኖሩባትን ለሁሉም እኩል የሆነችን ሃገር ለመፍጠር እንታገላለን" ሲሉ የሻምበሏ አባላት ተናግረዋል።
2. ታዲዮስ ታንቱ ሻምበል - ይህም ሻምበል በጎጃም ዕዝ የባህር ዳር ፋኖ ስር የተመሰረተ ሲሆን በቅርቡ ወደ ሻለቃ እንደሚያድግም ተነግሯል። ይህ ሻምበሉ ስያሜውን የወሰደውም ለእውነት ታምነው በእርጅና እድሜያቸው መስዕዋትነት እየከፈሉ ካሉት የወላይታው አንጋፋ ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁር ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ስም እንደሆነ ታውቋል። ፋኖዎቻችን በአጋጣሚውም "ለጋሽ ታዲዮስ ታንቱ እጅግ እጅግ ታላቅ አክብሮት አለን" ሲሉ ለሚዲያዎች የላኩት መልዕክት ያስረዳል።
በዚሁ አጋጣሚ በሌሎች አካባቢዎች ያላችሁም ፋኖዎቻችን እነዚህንና መሰል ትልቅ ትርጉም ያላቸውን ስያሜዎች እንድትጠቀሙ ጥሪ እናቀርባለን። ዝቅ ያደረጓቸውን፣ በታሪክ ውስጥ ተገቢና ጉልህ ስፍራ ሰጥተን ከፍ አድርገን እናሳያቸው!
@hulumedia1