እንደ ፆመ ሠው ለመፈሠክ ምንሯሯጠው ስ ነገር !
እንደው የፈጣሪ ይቅር ባይነት እንጂ የኛ የሁለት ወር ፆም ፀሎት አድኖን ነው ?
ምህረቱ የማያልቅ ሁኖ እንጂ እኛ ዝንት አለም ብንፆም ይቅር የምንባል ሠዎች ነን ግን ?
ከኣመት አመት የሀጢያት ስራችን አበል እንደሚከፈለው ፖለቲከኛ እየገነነ እንደምንኖረው ኑሮ እየናረ እንደ ዱር ቃጠሎ ጢሥ ሠማይ እየነካ እዚህ ደርሠናል ፤ የሚያልቁት ቢያልቁም የሚሠደዱት ቢሸሹም የሚረግፉት ቢረግፉም እኛ ደሞ ዛሬ ላይ ቆመን አለነው ። ለዛውም አማርጠን እየበላን እየጠጣን ለዛውም በልብስ ላይ ልብስ በጌጥ ላይ ጌጥ እየደራረብን ካዝናችንን የሞላው ገንዘብ አላዘጋ ቢለን ወጥተን በመዳራት በዳንኪራ በቅሚያ ገንዘባችንን በትነን ለስንቱ ሞት ምክንያት ሁነን ዛሬም አለን።
ከንግዱ አለም ከድሀው ሠርቀን ለሀብታም አጎብድደን ራሱኑ አጭበርብረን ርካሽ እቃ በውድ ሽጠን ያገኘነው ገንዘብ እውነት በርክቶልን ስራ ሠራንበት? ተለወጥንበትስ ? መልሱን ልባችንና ኪሳችን ይወቀው .
ስራ ለመቀጠር ተወዳድረን ለህክምና ትምህርት የኢንጂነሪንግ ምሩቅ በዘመድ ያስገባን የገባን እንዴት ነው ስራውና የተማርነው የትምህርት ዘርፍ ክላሽ አላረገም ?
ቤተ እምነት ብለን ወጥተን ቤተሠብ አስጨንቀን ገንዘብ ተቀብለን ሳይሆን (ፈልጠን ፣ነጥቀን) ቀኑን ስንዘል ርኩስ ነገር ስናደርግ በፈጣሪያችን ስም እየማልን አምልኮት ላይ ነው የቆየነው ስንል ያልተቀፀፍን ስንቶች አለን !
የቤት አከራይና ተከራይ ፣ በየመስሪያ ቤቱ በየተቋማቱ በአገልግሎት መስጫው በየትምህርት ቤቱ ሁሉ በቋንቋ ካልገጠመ ዘሩ ብሔሩ እያልን እየሠነጣጠቅን ስራ የማናስቀጥር ቤት የማናከራይ ሠብኣዊ እርዳታ እንኳን የማንሰጥ እኛ ርጉማን ስንሞት ምን ይውጠን ይሆን ?
ክልል ተብለን ሀገር ጎሳ ተሠጥቶን በመልክ በቀለም ተነጥለን ከአንድነት ምህተብ የተፈታን የኛን ቃል ያላወራ የራሱን መነሾ ያልመሠለ በመሀላችን ሲገኝ እንደመጤ የሠማይ ፍጥረት UFO ተቆጥረው በቀስትና በጎራዴ በቆጥራ በገጀራ በጥይት አሩር የቆላናቸው በራቸውን እየዘጋን ቤታቸውን በላያቸው ላይ ያነደድን ያቃጠልን እኛ ከዘላለም እሳትስ እንድን ይሆን ?
ቤተ እምነት እያወደምን እያቃጠልን የእምነት አባቶች እናቶች ወንድምና እህቶችን ህ ፃናቶችን በግፍ በአሠቃቂ ሁኔታ የምንገድል እኛ አንድ ቤት ሳይበቃን አንድ ሙሉ ከተማ የምናወድም እኛ ንፁሀንን ከሠላም ጉዟቸው ነጥለን በዱር በሜዳ እንደከብት የምናርድ የዳቢሎስ እኩያ ወንድሞች ማንነትን መሠረት እያደረገ አብሮን የኖረ ወንድማችንን ዘቅዝቀን እንደ ከብት ስጋ የምንሠቅል በሲኦሉ እሳት ለመንደድ እያማሟቅን ነውን ?
ከምንም በላይ ሀገር የተባለችው ክብርት መኖሪያ ዳር ድንበሯን መሀል ሀገሯን ታሪኳን የሚያዛባ ቅርሷን የሚሸጥ ባንዳ ተላላኪ ተራ ቅጥረኛ ወገኑን እንደይሁዳ ለማይረባ ዲናር የሚሸጥ አስመሳይ ምስጥ ሴረኛ ሁላ
ያሣደገውን የሚከዳ ያጠባውን ጡት የሚነክስ ልቡ በነውር የታፈነ የሠላም አየር መተንፈስን የተፀየፈ እርሱ አሟሟቱስ ያምርለት ይሆን ????
የኛ የሀጥያት ስራ ሠይጣን እንኳን ሊያደርገው የማይደፍረው ስለመሄኑ ጥርጥር የለኝም ።
እና ለዚህ ስራችን ዝንት አለም ፆም ፀሎት ስግደት ምፅዋት ብንታዘዝ ይከፋናል ? ክብር ለፈጠረን ይሁንና አለን የሚሉት በቀን 4 ግዜና ከዛ በላይ አማርጠው ቢበሉ
አልነሳንም የምንል በቀን 3 ግዜ ብንበላ
አጣሁ የሚለው በሁለት ቀን ወይ በሳምንት ጥቂት ፍርፋሪ ቀምሶ እንደሚያድር አስበን እናውቃለን ?
እናውቅ ይሆናል ግን ማካፈልን መለገስን ግን ፈፅመን አናውቅበትም !
ከማመስገን ማማረር ስለሚቀናን
ከፀሎት ከንቱ ውዳሴ ስለሚሻለን
ከመልካም ስራ ይልቅ ያልተነካ ሀጢያት ፍለጋ ስለምንባዝን
በየት በኩል ሠው ስለመሆን እናስብ እንጨነቅ ? ? ?
ልቦና ሠጥቶን ልባችን ከተደፈነ ፤
ወገብ ሠጥቶን ዝቅ ማለትን ከናቅን
እግርን ሠጥቶን ወደ ጥፋት መንገድ ብቻ ከሮጥን
እንዴት ሁኖ ነው ሰው የሚባለውን ፍጥረት የምሆነው ?
እንፀልይ እንፁም ፈጣሪን እንለምን
እንደዘንድሮው ሳይሆን እንደቀድሞው እንደአባቶቻችን ዘመን እንሁን
ፍቅር ይስጠን ሠላም ይስጠን የሚመጣውን ግዜ ያቅልልልን
እንባ የመገፋት የስቃይ እርጎ ነው !
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅ
አሜን !
ፀባዖት ሶልአኪያ
ሚያዝያ 2013
ግላዊ ሂስ
@misrakterefetobiya@tobiyamisrakterefe@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead