####እንዲህ ያደርገኛል####
:
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
ሰውነቴ ሁሉ ጆሮ ይሆንና የብናኝ ኮሽታ ገዝፎ ይሰማኛል፣
ኮቴ እንደመብረቅ እንደአንዳች ፍንዳታ የጆሮዬን ታንቡር
ደርሶ ይጠልዘኛል፡፡
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
ጥሞናዬ ረቆ፣
መንፈሴን አምጥቆ፤
የሷን ኮቴ ናፍቆ፣
የፍቅሬን አካሄድ ሰበር ሰካውን
ከርምጃዎች ሁሉ ከዳናዎች አውቆ፡፡
በናፍቆቷ ድጋን
በጉጉት ፍላፃ
ተወርዋሪው ልቤ
ተወጥሮ ከሮ፣
ጅስሜ እንደአሞራ
እንደብርቱ ንስር
ክንፍ አውጥቶ በሮ፡፡
ምድርና ሞላዋን
አለምን ይቃኛል፣
ከፍቅሬ በስተቀር
ሁሉም ከንቱ ከንቱ
ከንቱ ውቱ ይለኛል፡፡
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
በፍቅሯ ልዕልና በፍቅር ፅናቴ፣
ከመንደሬ ገዳም ከጎጆ በአቴ፣
ከመላዕክ ረቅቄ፤
ከፃድቅ ፀድቄ እጠብቃታለሁ፣
እመጣለሁ ብላኝ
መች ተኝቼ አውቃለሁ፡፡
አለም ግዜ ፀሀይ ሁሉም ቀጥ ብለው፣
የኪዳኔን ታቦት ፅላቴን አክብረው፣
ይማፀኑልኛል፤
ይማልዱልኛል፤
ይህ ምስኪን ፃዲቅ ሰው፣
ከአለም የመነነው
ባዕቱን የዘጋው፣
ፀሀይን አስቁሞ ጊዜን የገዘተው፣
እመጣለሁ ብለሽ እንዳትዘገዪ ነው፤
እንዳትቀሪበት ነው፡፡
ብለው ይሉልኛል
ጨረቃ ከዋክብት
ይማልዱልኛል፣
የፍቅር ብርታቴን ሁሉም ያውቁልኛል፣
ካይን ያውጣህ፤
ካይን ያውጣህ፤
ካይን ያውጣህ ይሉኛል፡፡
አንድ አንዴም ሽው ሲል
እንዲህ እሆናለሁ፣
ከቤቴ ቁጭ ብዬ
በሀሳብ እመጥቃለሁ፣
እሷን እየጠበኩ
እፈላሰማለሁ፤
እላላሁ፣
ይሄ ሁሉ ጥሞና
ይሄ ሁሉ ብቃት፣
ለሌላም ለሌላም
ቢሆን ምን አለበት፣
አዬ ግዜ ደጉ
አዬ ወጣትነት እላለሁ፡፡
እድሜ ለሷ ፍቅር
መንፈሴን ቀጥቅጦ
ልቤን ለሚገዛው፣
በሌላማ ግዜ
በጥልቅ ለመመሰጥ
አዕምሮዬን ባዘው፣
መች እሺ ይለኛል፤
መች እሺ እላለሁ፤
መች እሺ እለለሁ፡፡
@poems_Essay
🥀
:
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
ሰውነቴ ሁሉ ጆሮ ይሆንና የብናኝ ኮሽታ ገዝፎ ይሰማኛል፣
ኮቴ እንደመብረቅ እንደአንዳች ፍንዳታ የጆሮዬን ታንቡር
ደርሶ ይጠልዘኛል፡፡
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
ጥሞናዬ ረቆ፣
መንፈሴን አምጥቆ፤
የሷን ኮቴ ናፍቆ፣
የፍቅሬን አካሄድ ሰበር ሰካውን
ከርምጃዎች ሁሉ ከዳናዎች አውቆ፡፡
በናፍቆቷ ድጋን
በጉጉት ፍላፃ
ተወርዋሪው ልቤ
ተወጥሮ ከሮ፣
ጅስሜ እንደአሞራ
እንደብርቱ ንስር
ክንፍ አውጥቶ በሮ፡፡
ምድርና ሞላዋን
አለምን ይቃኛል፣
ከፍቅሬ በስተቀር
ሁሉም ከንቱ ከንቱ
ከንቱ ውቱ ይለኛል፡፡
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
በፍቅሯ ልዕልና በፍቅር ፅናቴ፣
ከመንደሬ ገዳም ከጎጆ በአቴ፣
ከመላዕክ ረቅቄ፤
ከፃድቅ ፀድቄ እጠብቃታለሁ፣
እመጣለሁ ብላኝ
መች ተኝቼ አውቃለሁ፡፡
አለም ግዜ ፀሀይ ሁሉም ቀጥ ብለው፣
የኪዳኔን ታቦት ፅላቴን አክብረው፣
ይማፀኑልኛል፤
ይማልዱልኛል፤
ይህ ምስኪን ፃዲቅ ሰው፣
ከአለም የመነነው
ባዕቱን የዘጋው፣
ፀሀይን አስቁሞ ጊዜን የገዘተው፣
እመጣለሁ ብለሽ እንዳትዘገዪ ነው፤
እንዳትቀሪበት ነው፡፡
ብለው ይሉልኛል
ጨረቃ ከዋክብት
ይማልዱልኛል፣
የፍቅር ብርታቴን ሁሉም ያውቁልኛል፣
ካይን ያውጣህ፤
ካይን ያውጣህ፤
ካይን ያውጣህ ይሉኛል፡፡
አንድ አንዴም ሽው ሲል
እንዲህ እሆናለሁ፣
ከቤቴ ቁጭ ብዬ
በሀሳብ እመጥቃለሁ፣
እሷን እየጠበኩ
እፈላሰማለሁ፤
እላላሁ፣
ይሄ ሁሉ ጥሞና
ይሄ ሁሉ ብቃት፣
ለሌላም ለሌላም
ቢሆን ምን አለበት፣
አዬ ግዜ ደጉ
አዬ ወጣትነት እላለሁ፡፡
እድሜ ለሷ ፍቅር
መንፈሴን ቀጥቅጦ
ልቤን ለሚገዛው፣
በሌላማ ግዜ
በጥልቅ ለመመሰጥ
አዕምሮዬን ባዘው፣
መች እሺ ይለኛል፤
መች እሺ እላለሁ፤
መች እሺ እለለሁ፡፡
@poems_Essay
🥀