➡️✅ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ካንሰርን ለማከም የሚያስችል ሳሙና ፈጠረ ።
✅ካንሰርን ለማከም የሚጠቅም ሳሙና የፈጠረው የ14 አመቱ ተመራማሪ ሄማን በቀለ ፡ ሰሞኑን ትላልቅ የአለም ሚዲያዎችን ትኩረት እየሳበ ይገኛል ።
በየአመቱ በሚካሄደውን 3M Young Scientist Challenge ላይ ይህንን ፈጠራውን ይዞ የቀረበው ታዳጊ ሄማን ፡ ውድድሩን በማሸነፍ የ25 ሺህ ዶላር አሸናፊ የሆነ ሲሆን ፡ America's Top Young Scientist የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደውና ፡ በአራት አመቱ ወደ አሜሪካ የተጓዘው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪው ሄማን በቀለ ለዚህ ሽልማት የበቃው ፡ በተለይ በታዳጊ ሀገራት የሚኖሩ ሰወችን የሚያጠቃውንና ፡ ህክምናውን ለማግኘት እስከ አርባ ሺህ ዶላር የሚያስፈልገውን የቆዳ ካንሰር በሽታን ማከም የሚያስችል ሳሙና በመፍጠሩ ነው ።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ሄማን በቀለ ፡ ይህንን አዲስ ፈጠራውን በተመለከተ እንደተናገረው ፡ ይህ ከአንድ ዶላር ባነሰ ዋጋ ፡ ለገበያ የሚቀርበው ሳሙና በበሽታው የተጠቁ ሰወች ለህክምና የሚከፍሉት ገንዘብ በማጣታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ስቃይ እንደሚቀንስ ገልጾ ፡ በቀጣይ ምርቱን በስፋት ለማድረስ እንደሚሰራ ገልጿል ።