ስለ እውነት


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified



Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ክፍል 2

5. የልጆችዎን የትምህርት አቀባበል የሚመዝኑባቸው ቀላል ዘዴዎች ይኑርዎት

ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ለመርዳት በየዕለቱ ምን ተምረው እንደመጡ መፈተሸና መከታተል እንዲሁም ቀለል ባለ ዘዴ የምዘና ጥያቄ አዘጋጅተው መመዘን ይችላሉ፡፡ በተወሰነ የጊዜ ርቀት ይህን ተግባር በማከናወን ልጆችዎን ከተማሩት ምን ይህል በሚገባ እንደተረዱት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ግን ልጅዎን በሚያሳስብና በሚያስጨንቅ መልኩ መካሄድ የለበትም፡፡ ልጆችዎ እተዝናኑና እየተጫወቱ ሊሰሩ የሚችሉበትን ድባብ መፍጠር ይገባል፡፡ ልጆችን በዚህ መልኩ የተማሩትን በተለያየ ዘዴ እየገመገሙ ማነፅ በልጆቻችን ትምህርት በስፋት ተሳታፊ እንድንሆን፤ ልጆችንም የተማሩትን ትምህርት በጊዜ በሚገባ እንዲከልሱና በጥልቀት እንዲረዱ እንዲሁም በቀላሉ የተማሩትን አስታውሰው በምዘና መለኪያዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እና በክፍል ውስጥም በንቃት እንዲሳተፉ ጭምር ያበረታታቸዋል፡፡

6. ልጆችዎን በትምህርታዊ ጉዞ ያዝናኑዋቸዋል

“ካሉበት ቦታ መቀየር ከድካም ዕረፍት የመውሰድ ያህል አስደሳች ነው” ይባላል፡፡ እንግዲያው እርስዎ ልጆችዎን ቀኑን ሙሉ ከሚውሉበት ት/ቤት እንዲሁም ከቤትዎ በተወሰነ ጊዜም ቢሆን በማላቀቅ ለምን በሽርሽር አያዝናኗቸውም? ከተለመደ ቦታ መቀየር ለሁሉም ቢሆን ያዝናናል፡፡ በተለይ ደግሞ ትምህርት በመማር ከፍተኛ ውጣ ውረድ በት/ቤትም ሆነ በቤት ለሚጋፈጡ ልጆችዎ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እዚህ ጋር ግን አንዴ ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን አለ እሱም ልጆቻችን በሽርሽር/በጉብኝት ለማዝናናት ከመነሳታችን በፊት የምናዝናናበት/የምናስጎበኝበት ቦታ ለልጆቻችን የአካልም ሆነ የአዕምሮ ጤና እንዲሁም የሥነ ልቦና ደህንነታቸው ብሎም ሞራልና ግብረ-ገብነታቸው ላይ ምንም አይነት ጉዳት የማያስከትል (ዋጋ የማያስከፍለን) ስለመሆኑ ቅድሚያ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ አለያ ግን አተርፍ ባይ . . . ነው የምንሆነው፡፡

7. ልጆችዎ የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግቡ ዕውቅና ሰጥተው ያበረታቱ፤ ይሸልሙ

ልጆችዎን ለሚያስመዘግቧቸው የትምህርት ስኬቶች ዕውቅና ሰጥቶ ማበረታታትና መሸለም የተሻለ እንዲሰሩ በጣም ያግዛቸዋል፡፡ እርስዎ ታዲያ ልጆችዎ የላቀ ውጤት ይዘው ወደ ቤት ሲመጡ በማበረታታትና በሽልማት ሊቀበሏቸው ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ ግን የግድ ከፍተኛ የሆነ ወጪ ማውጣት አይጠበቅም፡፡ አቅም በፈቀደ ከወላጅ ለልጆች የሚደረግ ሽልማት ልጆች ደክመው ያመጡት ውጤት በወላጅ የላቀ ዋጋ እንደሚሰጠው መልዕክት ለማስተላለፍ መሆን ነው የሚገባው፡፡

8.ልጆችዎ እረፍት እንዲኖራቸው ያድርጉ! ለልጆችዎ ሰዓት ይኑርዎት! 

ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከጥናት ዕረፍት መውሰድ ለልጆች ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም ልጆችዎን በትምህርት ለማገዝ የሚረዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡ በቤት ውስጥም ቢሆን አንዳንዴ ልጆች ከትምህርት ተለይተው (አቋርጠው) ሊዝናኑ የሚችሉበት ጊዜ ያመቻቹላቸው፡፡ እርስዎም ካለዎት ሰዓት ምርጡን ከልጅዎ ጋር በመሆን ያሳልፉ፡፡ ግን ግን ስንቶቻችን ነን ካለን ሰዓት ምርጡን ነገ እኛን ይተኩናል ብለን ብዙ ከምንደክምላቸው ውድ ልጆቻችን ጋር የምናሳልፈው? ምን ያህል እርስዎ ለልጆችዎ ቅርብ ነዎት? ለልጅዎት ምርጡን ሰዓት ሰጥተው ያገኟቸዋል ወይስ . . . ? እኛ ለልጆቻችን ቅርብ ልንሆን ይገባል፡፡ ይህን የማናደርግ ከሆነ ግን ልጆቻችንን እኛ ሳንሆን የሚያንፃቸው ሌላ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክ፣ ቲቪ፣ እና የመሳሰሉት፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ነገ የምንመኘውን አይነት ትውልድ ማፍራት ባዶ ተስፋ ሆኖ ይቀራልና ለልጆቻችን ሰዓት መስጠታችን በሚገባ መፈተሽ ለነገ የማይባል ነው፡፡

9.ልጆችዎ በአግባቡ መመገባቸውንና በተገቢው ሰዓት ወደ መኝታቸው መሄዳቸውን ያረጋግጡ!

ት/ቤት እንደ ስያሜው እውቀት የሚቀሰምበት ቦታ ነው፡፡  ትምህርት ለመማር ደግሞ ተማሪ በአካልም ሆነ በአዕምሮ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ የምግብ ስርዓትና የመኝታ ሰዓት የተስተካከለ ሊሆን ይገባል፡፡ እንደ ወላጅ ለልጆች አሸክመን ለምንልከው ምግብ ምን ያህል ተገቢውን ጥንቃቄ እናደርጋለን? አንዳንዴ ልጆች እንደማይመቻቸው እየታወቀ የሚታሰርላቸውን ምግብ እንዲጨርሱ በት/ቤት የሚፈጠረው ግብ ግብ  ለጉድ ነው፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን ምግብ በዕርግጥ እየተመለከቱት ነውን? የሚል ጥያቄም ያስነሳል፡፡ በተመሳሳይ የልጆች የእንቅልፍ ሰዓትም ከፍተኛ ክትትል ያሻዋል፡፡ ልጆች መተኛት በሚገባቸው ሰዓት ስለመተኛታቸው እንደ ወላጅ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ልጆች ማረፍ በሚገባቸው የመኝታ ሰዓት ተገቢ ባልሆኑ ተግባራት የሚጠመዱ ከሆነ በአካልም ሆነ በአዕምሯቸው ላይ የሚፈጠረው ጫና በትምህርታቸው ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡

ውድ ወላጅ እንግዲህ ልጆቻችንን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚቻልባቸው ቀላል ዘዴዎች 9ኙን የጠቆምንበት  መልዕክት በዚሁ ተጠናቋል፡፡

እንደ ወላጅ ከጽሑፉ ልጅዎን በትምህርቱ/ቷ ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ነጥቦች እንዳገኙ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እባክዎ ልጆችዎን በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ ለመርዳት እንደወላጅ ሃላፊነትዎን በአግባቡ ይወጡ የዛሬው መልዕክታችን ነው፡፡ ሰላም!


ቦሌ የነበረው ተኩስ❓❓
ዛሬ ቦሌ ሚሊዮን አዲራሽ አካባቢ ተኩስ ነበር‼️
የተኩሱ መነሻ የጎንደር ፋኖ መሪ የነበረው ናሁሰናይ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች በመያዙ ምክንያት ነው ተብሏል።
ናሁሰናይን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲሞክር ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል ያሉ ሲሆን አብረውት የነበሩ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ እርሱ ቆስሎ ሳይያዝ እንዳልቀረ ተገልጿል። ከፀጥታ ኃይሎች በኩል አንዱ ሞቷል የቆሰሉም መኖራቸውን ነው የመረጃ ምንጮቹ የገለፁት።
ከቦሌ snap plaza እስከ ቦሌ መድሃኒያለም ያለው መንገድ ዝግ ተደርጓል ብለዋል።
ጥቆማ❗❗👇
👉ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት፣ከስር ባለው ሊንክ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial




Forward from: Alain Amharic
የእስራኤል 70 ሺህ ቶን ቦምብ በጋዛ ያደረሰው ውድመት

የአለም ባንክ በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ የደረሰው ውድመት 18 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ ገምቷል።

ጋዛን ማፈራረሱን የቀጠለው ጦርነት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ቤት አልባ አድርጓል ተብሏል።

እስራኤል ባለፉት ስድስት ወራት በጋዛ በፈጸመችው ድብደባ የደረሰውን ውድመት በዝርዝር ይመልከቱ፦https://bit.ly/43RJoAg


ሶማሊያ በኢትዮጵያ አምባሳደርና ዲፕሎማቶች ላይ ያሳለፈችው ትእዛዝ ምን ይዟል?

ኢትዮጵያ በሶማሊያ የውስጥ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ገብታለች ያለው የሶማያ መንግስት በሶማሊላንድ እና ፑንትላንድ ዋና ከተማ በሆኑት ሀርጌሳ እና ጋሮዌ ያሉ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፏል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫው የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሃመድ ዋሬ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ የ72 ሰዓት ግዜ መስጠቱን አስታውቋል።

በተጨማሪም ሶማሊያ በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን ለውይይት ወደ ሞቃዲሾ መጥራቷንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የሶማሊያ ካቢኔ ውሳኔ ዝርዝርን ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3xobVRC


Forward from: Alain Amharic
እስራኤል የኳታሩን አልጄዚራ ቴሌቪዥን እንደምታደርግ ኔታንያሁ ተናገሩ

ኔታንያሁ በቅርቡ ፓርላማው ተሰብስቦ እግዱን ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስችል ህግ ያወጣል ብለዋል
https://am.al-ain.com/article/neytanyahu-pushes-blocke-aljezeera-israel


Forward from: Alain Amharic
ከፍተኛ የአየር ብክለት ያለባቸው ዓለማችን ከተሞች

የባንግላዲሽ፣ ሕንድ እና ፓኪስታን ለመኖር አስቸጋሪ የተባሉ ቀዳሚ ሀገራት ናቸው

የእስያ ሀገራት የዓለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው አማካኝ የዓለም አየር ብክለት ደረጃ ከ10 እጥፍ በላይ ናቸው ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3J2iSue


Forward from: Alain Amharic
በእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁን የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

በእየሩሳሌም በተካሄደ ሰልፍ ላይ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሳትፈዋል። ተቃውሞ የወጡ እስራሌላውያን በጋዛ ታግተው የሚገኙ እስራኤላውያን እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4afN0yi


የራሳቸው ያለሆነን ገንዘብ ወስደው ወደቤቲንግ ተቋማት ያዛወሩ ግለሰቦች እንዲያመለክቱ ባንኩ አሳሰበ‼️

ያለአግባብ የራሳችሁ ያለሆነን ገንዘብ ከባንኩ ወስዳችሁ ወደ ቤቲንግ ተቋማት ገንዘቡን ያዘዋወራችሁ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንድታመለክቱ ባንኩ አሳስቧል። ባንኩ መጋቢት 7 ቀን 2016 ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ይታወቃል።

በዚህም በርካታ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብና በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የወሰዱትን የገንዘብ እየመለሱ ይገኛሉ።ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ወደ ቤቲንግ ተቋማት በማዛወራቸው መመለስ እንደተቸገሩ ገልጸዋል።

በመሆኑም ገንዘቡን ተመላሽ ለማድረግ እንዲቻል ወደ ቤቲንግ ተቋማት የራሳችሁ ያልሆነውን ገንዘብ ያዘዋወራችሁ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንድታመለክቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥሪ አቅርበዋል።

@Esat_tv1
@seleeewnet


ኢትዮጵያ የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በሁለተኝነት አጠናቀቀች!

45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በሰርቢያ ቤልግሬድ ተካሂዷል፡፡ኢትዮጵያም በተለያዩ  ኪሎ ሜትር ውድድሮች የተሳተፈች ሲሆን 2 ወርቅ፣6 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት  ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡

በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች  ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት አሸንፈዋል፤በተመሳሳይ በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ውድድር የብር ሜዳልያ  አግኝታለች፡፡

እንዲሁም በድብልቅ ሪሌ 8 ኪሎ ሜትር ውድድር  የብር ሜዳሊያ ስታገኝ በአዋቂ ሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ግን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም፡፡በውድድሩ ከ51 ሀገራት የተውጣጡ አትሌቶች÷ በወጣቶች እና በአዋቂ በአምስት የውድድር ዘርፎች ተሳትፈዋል፡፡

@seleeewnet


Forward from: Hasen Injamo
ብር ማተም ቴፒ ደርሷል

ባለ ሁለት መቶ ብር ሲያትም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ:: መጋቢት 10 ቀን 2016 በቴፒ ከተማ ህብረት ቀበሌ ከረፋዱ 5:30 ሰዓት በአንድ ማተሚያ ቤት ዉስጥ ሐሰተኛ የ200 ኖቶችን ሲያሳትምና ኮፒ ሲያደርጉ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ ኮፒ የተደረገ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ብር እና አንድ ተጠርጣሪ፣ ፎቶ ኮፒ ፣ኮምፕተር ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ገልጿል።
____
ብዙ ሀገራት ላይ ፎቆች ድንገት የሚያድጉት በተመሳሳይ ድርጊት ሲሆን ድሆች ግን ድህነታቸውን አስፋፍተው ይቀጥላሉ::


#Update #ራይ

" ግጭቱ ከ20 ደቂቃ በላይ አልፈጀም፤ በግጭቱ የሞተ ሰውም የለም  " - በትግራይ ደቡባዊ ዞን የራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ግደይ ካልኣዩ

" የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ግዛት ውስጥ የፈፀሙት ትንኮሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት  እንዲያስቆመው ተደርጓል " - የትግራይ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም

የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባናል ጥያቄ በሚያነሱበት የራያ አላማጣ አካባቢ ግጭት መነሳቱን አንድ የራያ አላማጣ እና አካባቢው አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለፃቸው ይታወሳል።

አመራሩ ፥ " ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በመጣስ ጦርነት ከፍቷል፤ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ የተኩሱ መነሻ በራያ እና ወልቃይት በትምህርት ስርዓቱ ካርታ ላይ ተካተዋል የሚል ነው " ብለው ነበር።

በትግራይ በኩል ምን ምላሽ ተሰጠ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በትግራይ ደቡባዊ ዞን የራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ካልኣዩ ግደይና የክልሉን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም ጠይቋል።  

አቶ ካልኣዩ ግደይ በፅሁፍ በሰጡት ምላሽ ፥ " ግጭቱ የተከሰተው መጋቢት 17 /2016 ዓ.ም ቀን ነው። በር ተኽላይና ዶዶታ በተባለ አከባቢ ነው። ቶክሱን የጀመሩት የአማራ ታጣቃዎች ሲሆኑ በትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ላይ ቶክስ የከፈቱት በአለማጣ ከንቲባ አቶ አበራ ሃይሉ ጥሪ የተደረገላቸው የአማራ ክልል ታጣቂዎች ናቸው " ብለዋል።

ግጭቱ 20 ደቂቃ በላይ አልፈጀም ያሉት አስተዳዳሪው በግጭቱ የሞተ ሰው የለም ብለዋል።

" ግጭቱ ሆን ተብሎ  ፦
- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለማደናቀፍ
- የትግራይ ማህበረሰብ ተወካዮች ከጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ያደረጉት ውይይትና የአማራና የትግራይ  ፕሬዚዳንቶች በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ዙሪያ የፈጠሩት መድረክን ተከትሎ 'ውሉ ተግባራዊ ይሆናል' የሚል ስጋት  ስለፈጠረባቸው ነው " ብለዋል።

አቶ ካልኣዩ አክለው " የአማራ ክልል ታጣቂዎች ለቀጣይ ትንኮሳ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ደርሰንበታል " ብለዋል።

የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የራያ ጨርጨር ወረዳ አስተዳዳሪ በፅሁፍ የሰጡት መረጃ እንዲያረጋግጡለት ፤ የትግራይ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም አግኝቶዋቸዋል። 

አቶ ረዳኢ ሓለፎም ፥ የራያ ጨርጨር ወረዳ አስተዳዳሪ መረጃ ' ልክ ነው ' ብለዋል።

ከዚህ ባሻገር ፤ " የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ግዛት ውስጥ የፈፀሙት ትንኮሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንዲያስቆመው ተደርጓል " ሲሉ ተናግረዋል።

" የፌደራል መንግስት በትግራይ ግዛት ውስጥ በመግባት ተደጋጋሚ ግጭት በመፍጠር ላይ የሚገኙ የአማራ ክልል ታጣቃዊች በዘላቂነት እንዲያስታግስ እና በሃይል ከያዙት ግዛት ለቀው እንዲወጡ የሚያስገደደው የፕሪቶሪያ የሰላም ውል እንዲተገብር ደግመን ደጋግመን እንጠይቃለን " ብለዋል። 

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
                                             
@tikvahethiopia         
@seleeewnet


✍️የዓለማችን አጭሩ ዶክተር ✍️

👉ዓለም ላይ ምንም የማይቻል ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው ይሉታል፡፡ በቁመቱ ማጠር ያጋጠሙት መድሎዎች ዶክተር ከመሆን ህልሙ አሰናክለው አላስቀሩትም፡፡ ፈተናዎችን በጽናት ማለፉ የብርቱ ሰብእና ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ የህይወት መርሁ በተስፋ መትጋት ነው፡፡

👉በማይድን ህመም የመጠቃቱ የሀኪሞች መርዶ ለወላጆቹ የደረሰው ገና የ4 ዓመት ህጻን እያለ ነበር፡፡በትምህርት ቤት ቆይታው በቁመቱ ማጠር እና በጭንቅላቱ መግዘፍ በርካቶች ቢሳለቁበትም የሚያበረቱ ጥቂት አብሮ አደጎቸን ነበሩት፡፡

👉አንድ ቀን ወላጅ አባቱ በቀን 200 ሩፒ የሚያስገኝ የስራ እድል ቀረበላቸው፡፡ ስራው ልጃቸውን ለአስቂኝ ትዕይንት የቡድናቸው አባል ለማድረግ ከወጠኑ የሰርከስ ቡድን ባልደረቦች የመጣ ነበር፡፡ ወላጅ አባቱ ቆፍጠን ያለ መልስ ሰጡ፤ "ልጄ ተምሮ ሀኪም ይሆናል…"

👉በህንድ ጉጃራት ግዛት ተወልዶ ያደገው የ23 ዓመቱ የዓለማችን አጭሩ ዶክተር ጋነሽ ባርያ የወላጅ አባቱን ውለታ ተናግሮ አይጠግብም፡፡ ልጃቸውን ሰርቀው ለስራ እንዳይወስዱባቸው ሰግተው ስራቸውን ጥለው ከእርሱ ጋር ትምህርት ቤት እስከዋል ደርሰው ነበር፡፡

👉ጋነሽ ባለበት አካላዊ የአቅም ውስንነት ሳይበገር በጥሩ ውጤት እስከ ዩኒቨርሲቲ ደርሶ ህክምና ለማጥናት "ብሃቭናጋር" ወደ ተባለ የመንግስት ኮሌጅ ማመልከቻ አስገባ፡፡ ኮሌጁ ግን ተቀብሎ ሊያስተምረው ፈቃደኛ አልነበረም፡፡

👉ጉዳዩን ወደ ሕንድ የሕክምና ምክር ቤት ወሰደው፡፡ የምክር ቤቱ መልስም "በ91 ሳ.ሜ ቁመት በአስቸኳይ ሁኔታዎች ውስጥ የህክምና ተግባር መፈጸም አይቻልም" የሚል ነበር፡፡ የሀገሪቱን የትምህርት ሚኒስቴር እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠንቶ መፍትሄ ሲያጣ የፍትሕ ተስፋ ባለመቁረጥ ጉዳዩን ወደ ሕንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አደረሰው፡፡

👉በመጨረሻም እ.አ.አ በ2018 ፍርድ ቤቱ ለጋነሽ በቀዶ ጥገና ትምህርት ክፍል ውስጥ የመመዝገብ መብት ሰጠው፡፡ በብሃቫናጋር በሰር-ቲ ሆስፒታል ውስጥ በተለማማጅ ዶክተርነት እየሰራ የሚገኘው እጩ ዶ/ር ጋነሽ ባሪያ በቅርቡ ትምህርቱን ያጠናቅቃል፡፡

👉"ከሦስት ዓመታት በፊት በጣም ተከፍቼ ነበር፣ አትችልምን ለመቀበል ባለመፍቀዴ ግን እዘህ ደርሻለሁ"ይለል እንደማንኛውም ሰው  ጥሩ ኑሮ መኖር እና ወላጆቹ ማኮራት እንደሚፈልግም መናገሩን የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ያመላክታል፡፡

Via 👉EBC
@seleeewnet


ራሺያ #ግብረሰዶምን በሸብር ዝርዝር ውስጥ አስገባች‼️
ሩሲያ የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴን በአክራሪነት እና ሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ ማከተቷ ተሰምቷል፡፡

የተመሳሳይ ጾታ እንቅስቃሴ አራማጆች በአክራሪነትና በአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ  የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሩሲያ ሚዲያዎች ዘገባ ያመላክታል፡፡ ውሳኔው የግብረ ሰዶማዊያን እና ትራንስጀንደር ተወካዮችን ለእስር እና ለሽብርተኝነት ቅጣት የሚዳርግ ነው ተብሏል፡፡
የሩሲያ ውሳኔ ዓለም አቀፍ የግብረ ሰዶም ማኅበራት እንቅስቃሴ እና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን ጭምር ይመለከታል ተብሏል፡፡ በሩሲያ ምድር የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴ ማድረግ ከዚህ በኋላ በሸባሪነት አስከስሶ ዘብጥያ የሚያስወርድ ከባደ ወንጀል ሆኗል፡፡

በአገሪቱ የግብረሰዶማዊ እንቅስቃሴን የሚደግፉና የሚያስፋፉ አካላት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ይነገራል፡፡

የእንቅስቃሴው አራማጆች መሰረት ሩሲያ ባላንጣ ካደረገቻ ቸው ከእነ አሜሪካና አውሮፓ ምድር የሚነሳ መሆኑ ደግሞ የቭላድሚር ፑቲንን አስተዳደር አስቆጥቷል፡፡

እንደ አሜሪካ ያሉ አገራት የግብረ ሶዶማዊያን እንቅስቃሴን እንደ መብት ቆጥረው እያስፋፋት ነው፡፡ ግብረ ሶዶማዊያነት ከምዕራቡ አለም አልፎ እስከ አፍሪካ የዘለቀ ሲሆን፣ አንዳንድ አገራት እንስቅቃሴውን በሕግ እያገዱ ነው(አዩዘሀበሻ)።
ጥቆማ❗❗👇
👉 ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያግኙ፣ከስር ባለው ሊንክ join አድርጉ❗👇👇👇👇


" ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው "‼️

🗣ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከትላንትና የሽብር ጥቃት በኃላ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ነገ መጋቢት 15 በመላው ሩሲያ የሀዘን ቀን እንደሚሆን ተናግረዋል። " የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ዜጎቻችን ይዘከሩበታል " ብለዋል።

አሁን ላይ በጥቃቱ ላይ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጠር ስር መዋላቸውን ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ፤ ሌላ የጅምላ ግድያ እንዳይፈጸም የጸጥታ ኃሎች ሰፊ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።

" በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፈ እና ያገዛቸው የትኛውም አካል ለህግ ይቅርባል " ሲሉ ዝተዋል።

ፕሬዜዳንቱ በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ 4 ወንጀለኞች ወደ ዩክሬን ሊያመልጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

" አሁን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያመላክተው በዩክሬን በኩል ሽብርተኞች ለማስመለጥ የሚያስችል መንገድ በድንበር በኩል ተዘጋጅቶ እንደነበረ ነው "  ብለዋል።

" ሩሲያ በዚህ የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሁሉንም አካላት ለይታ ትቀጣለች " ያሉት ፑቲን፤ " ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው፤ ከዚህ ውጪ ምንም አማራጭ እና ተስፋ የላቸውም " ሲሉ ዝተዋል::
@seleewnet


Forward from: Alain Amharic
ፑቲን የሞስኮውን ጥቃት ተከትሎ ዛቻና ቁጣ በተቀላቀለበት ንግግራቸው ምን አሉ?

ፑቲን “ሩሲያ በጥቃቱ ላይ የተሳተፉትን ሁሉንም ለይታ ትቀጣለች” ብለዋል። በጥቃቱ ላይ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸው አራት ሰዎች ወደ ዩክሬን በመሸሽ ላይ እያሉ ነው የተያዙት ብለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3TM8A7J


#Update

ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል።

4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈፀመውን ድርጊት " #የሽብር_ጥቃት_ነው " ሲል ጠርቶ አውግዟል።

ለጥቃቱ #IS ኃላፊነቱን መውሰዱን በበይነ መረብ የወጣ አንድ ያልተረጋገጠ መግለጫ አመልክቷል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ፤ IS ሩሲያን ለማጥቃት እንደሚፈልግ የሚያሳይ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

አሜሪካ በሞስኮ ከተማ " ሕዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች " ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሩሲያን አስጠንቅቃ ነበር።

ከ2 ሳምንታት በፊት በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ በርካታ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ሕዝባዊ ስፍራዎች እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር።

በማስጠንቀቂያው ላይ " ጽንፈኞች በሞስኮ ሕዝብ በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎችን (የሙዚቃ ኮንሰርትን ጨምሮ) የጥቃት ዒላማ ለማድረግ ዕቅድ አላቸው " የሚል ሪፖርትን እየተከታተልኩ ነው ሲል ገልጾ ነበር።

ኤምባሲው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ወደደረሰበት ስፍራ ዜጎቹ ዝር እንዳይሉ ምክር ማስተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia


Forward from: Alain Amharic
ኢትዮጵያ ሩሲያ አሸባሪዎችን ለመዋጋት ለምታደርገው ጥረት ሙሉ ድጋፍ እንደምተሰጥ ገለጸች

ኢትዮጵያ በሩሲያ ሞስኮ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት አውግዛለች። በሩሲያ ሞስኮ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 115 ደርሷል።

ኢትዮጵያ ስለ ጥቃቱ ምን አለች? በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/497KpVx


#Update

ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል።

4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈፀመውን ድርጊት " #የሽብር_ጥቃት_ነው " ሲል ጠርቶ አውግዟል።

ለጥቃቱ #IS ኃላፊነቱን መውሰዱን በበይነ መረብ የወጣ አንድ ያልተረጋገጠ መግለጫ አመልክቷል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ፤ IS ሩሲያን ለማጥቃት እንደሚፈልግ የሚያሳይ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

አሜሪካ በሞስኮ ከተማ " ሕዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች " ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሩሲያን አስጠንቅቃ ነበር።

ከ2 ሳምንታት በፊት በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ በርካታ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ሕዝባዊ ስፍራዎች እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር።

በማስጠንቀቂያው ላይ " ጽንፈኞች በሞስኮ ሕዝብ በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎችን (የሙዚቃ ኮንሰርትን ጨምሮ) የጥቃት ዒላማ ለማድረግ ዕቅድ አላቸው " የሚል ሪፖርትን እየተከታተልኩ ነው ሲል ገልጾ ነበር።

ኤምባሲው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ወደደረሰበት ስፍራ ዜጎቹ ዝር እንዳይሉ ምክር ማስተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia


በትግራይ ጦርነት “ምርኮኞች ነበሩ” የተባሉ 112 የመከላከያ ሰራዊት አባላት “በምህረት” ተለቀቁ ‼️
በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት “ተማርከው ነበር” የተባሉ 112 የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት፤ በትናንትናው ዕለት “በምህረት” መፈታታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ። በዛሬው ፍቺ ያልተካተቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጉዳይም “በአጭር ጊዜ ውስጥ” መፍትሔ እንደሚያገኝም አስተዳደሩ ገልጿል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ፤ የፌደራል መንግስት እና የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በጥቅምት 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ከመፈራረማቸው በፊት የተማረኩ መሆናቸውን የትግራይ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ከ16 ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መለቀቃቸውን ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አስታውሷል።

ትናንት አርብ መጋቢት 13፤ 2016 የተለቀቁት የመከላከያ ሰራዊት አባላት፤ “በከባድ ወንጀል” ተጠርጥረው “በቁጥጥር ስር የቆዩ” መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለእነዚህ የሰራዊት አባላት “ምህረት” ያደረገው፤ የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተደረገ ውይይት ላይ “በተደረሰው መግግባት” መሆኑንም አክሏል።
ጥቆማ❗❗👇
👉በዚህ የቴሌግራም ቻናል ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያግኙ፣ከስር ባለው ሊንክ join አድርጉ❗👇👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

20 last posts shown.