የአዲስ ኪዳን መካከለኛ
@superchristiantube7@superchristiantube7@superchristiantube7#የአዲስ_ኪዳን_መካከለኛ
የአዲስ ኪዳን መካከለኛ እንደ እርሱ ሌላ የሌለ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነው ጌታ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው:: እርሱ ለእግዚአብሔርም ለሰውም ወገናዊነቱ እኩል ሹመቱም ዘላለማዊ የሆነ ነው::
#የአዲስ_ኪዳን_መካከለኛ_ወደሚሆን_ወደ_ኢየሱስ_ከአቤልም_ደም_ይልቅ_የሚሻለውን_ወደሚናገር_ወደ_መርጨት_ደም_ደርሳችኋል። ዕብ. 12÷24
#አሁን_ግን_በሚሻል_ተሰፋ_ቃል_በተመሠረተ_በሚሻል_ኪዳንም_ደግሞ_መካከለኛ_እንደሚሆን_በዚያ_ልክ_እጅግ_የሚሻል_አገልግሎት_አግኝቶአል። ዕብ. 8÷6
ሰውና ሰው ቢጣላ በመካከል የሚገቡት አስታራቂዎች ከአንድ በላይ ቢሆኑ ምንም አይደለም። ነገር ግን ጠቡ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሲሆን ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር በመካከል የሚገባና የሚያስታርቅ ሌላ መካከለኛ (አማላጅ) የለም። እግዚአብሔር አንድ ባይሆን ኖሮ ከምርጫው ብዛት የተነሳ የሰው ልጆች ግራ ሊጋቡ ይችሉ እንደነበረ፤ እንደዚሁ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ባይሆን ወደ እግዚአብሔር የመቅረቢያው መንገድ ዝብርቅርቁ ይወጣ ነበር።
ከኢየሱስ ሌላ አማላጆች ሰጥቶናል በሚሉት መካከል አማላጆቹ በመብዛታቸው ስለ የመካከለኛነት አገልግሎት የተቃወሰና ግራ የሚያጋባ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ አመለካከት አለ። የዚህን እውነት ለመረዳት ከአማላጆች አንዷ ክርስቶስ ሰምራ አደረገች የሚሉት ገድል መመልከት በቂ ነው። ክርስቶስ ሰምራ ሰውን ብቻ ሳይሆን ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ምልጃ አድርጋለች።
ገድለ ክርስቶስ ሰምራ
#ጌታም_ወዳጄ_ክርስቶስ_ሰምራ_ሆይ_እስኪ_የልብሽን_ሀሳብ_ወይም_ፍላጎትሽን_ንገሪኝ_አላት። #አቤቱ_ፈጣሪዬ_ፈቃድህስ_ቢሆን_የአዳም_ልጆች_ከስቃይ_ከኩነኔ_ይድኑ_ዘንድ_ዲያብሎስን_ይቅር_ትለው_ወይም_ትምረው_ዘንድ_እለምንሃለሁ። #የኃጥእን_መመለሱን_እንጂ_ጥፋቱን_አትወድምና_አለችው... >>
ሰይጣንንና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ መሞከር መጽሐፍን ካለማወቅና ስለ እግዚአብሔር ሆነ ስለ ሰይጣን ማንነት በትክክል ካለመረዳት የሚመጣ ችግር ነው። ገ.ክ.ሠ. ዘግንቦት 36-39
ሌላው አማላጅ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆነውን ሁሉ ጌታ እንዲምርለት ማልዶ በጅምላ እንዳስማረ በገድሉ ውስጥ ተተርኮለታል።
ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#አባታችንም_ጌታችንን_አቤቱ_የኢትዮጵያን_ሕዝብ_አንድ_ሳታስቀር_በሙሉ_ማራቸው_አለው። #ጌታችንም_አባታችንን_እነሆ_የኢትዮጵያን_ህዝብ_በሙሉ_ዓስራት_እንዲሆኑ_ሰጥቸሃለሁ_እንድወደድህ_ላንተ_ይሁኑህ_መታሰቢያህን_ያድርጉ_በጸሎትህ_ይታመኑ_ደስ_ብሎአቸው_ለዘላለም_ይኑሩ አለው። ገ.ገ.መ.ቅ.ክፍል 7 ምዕ. 27፥26-28
እንደዚህ ገድል አገላለጽ ደህንነት በጅምላ ለኢትዮጵያዊ ሁሉ ተሠጥቶአል። በዚህ ገድል መሠረት ለመዳን የሚያስፈልገው በክርስቶስ ማመን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻና በገብረ መንፈስ ቅዱስ አማላጅነት መታመን ነው። በኢትዮጵያ በክርስቶስ የሚያምኑ፣ ሌላ የተለያዩ ኃይማኖት ያሏቸው፥ ደግሞም ለጣዖት የሚሰግዱ ብዙ ወገኖች አሉ። ስለዚህ ስለገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲል እግዚአብሔር ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ በጅምላ ይመራል ብሎ ማስተማር ከፍተኛ ስህተት ነው።
እነዚህን ገድል፣ ታምር የተባሉትን መጽሐፎች ለሚያነብ ሰው የአማላጆቹን ቀጥር ያህል ብዙ አሳፋሪና ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳቦች እንዳሉ ግልጽ ነው።
የአንዱን የኢየሱስ ክርስቶስን አማላጅነት ብቻ መቀበል ማለት ይህን ሁሉ አሮጌ ተረት መተው ማለት ነው። ስለዚህ ነው ሰዎች ክርስቶስን ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም ማለት የሚቀላቸው።
በጥላው ዘመን የነበሩትን የመካከለኛነት አገልግሎቶች ሁሉ አጠቃሎ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ እንዲሆን የተመረቀውና የተሾመው አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ስለዚህ እርሱ፦
ሀ) ሙሴ አስቀድሞ እግዚአብሔር እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል ያለው ነቢይ ነው። (ዘዳ. 18፥15-17፣ የሐዋ. 3፥20-27፣ ሉቃ. 13፥33)
ለ) እንደመልከ ጸዴቅ የዘላለም ካህን ነው። (ዕብ. 5፥6፣ ዕብ. 3፥5፣ ዕብ. 3፥1 ዕብ. 7፥26፣ ዕብ. 4፥10)
ሐ) የዘላለም ንጉስ ነው። (ሚክ. 5፥2፣ መዝ. 2፥6፣ ኢሳ. 9፥6-7፣ ራዕ. 20፥4-6)
የሰብአዊ መጠሪያ ስሙ የሆነው #ኢየሱስ የሚለው ቃልና መለኮታዊ ስሙ #ክርስቶስ የሚለው ቃል ሁለቱም መካከለኛነቱን የሚያንጸባርቁ ናቸው።
መለኮታዊነቱን የሚገልጸው #ክርስቶስ የሚለው ቃል የመጣው #ክርስቶ ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን የቃሉ መሠረታዊ አመጣጥ ግን በብሉይ #መሲህ ከሚለው ከዕብራይስጥ ቃል ነው። #መሲህ ( #ክርስቶስ) ማለት #የተቀባ ማለት ነው። በብሉይ የሚቀቡት #ነቢያት፣ #ካህናትና #ነገሥታት እንደነበሩ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ሦስቱንም ማዕከላዊ አገልግሎት አጠቃሎ ለማሟላት #የተቀባ (የተመረቀ) በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ብቸኛው መካከለኛ ነው። #ኢየሱስ ማለት #መድኃኒት ማለት ነው። ኃጢያተኛን ከኃጢአት ዕዳና ፍርድ ነፃ የሚያደርገውና የሚያድነው ከእርሱ በቀር ሌላ ማንም የለም። (ሐዋ. 4፥12)
@superchristiantube7@superchristiantube7@superchristiantube7ቢያንስ ቢያንስ ይህን መልእክት ለ2 ሰዎች #ሼር በማድረግ ወንጌልን ከእኛ ጋር አብረው ይሥሩ።
#SHARE