ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ወይስ ተመላጅ?
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7
#ኢየሱስ_ክርስቶስ_አማላጅ_ነው_ወይስ_ተመላጅ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ከመስጠታችን በፊት #ማለደ የሚለውን ቃል ትርጉም እንመልከት።
ትርጉም
#ማለደ ለሚለው ቃል የሚከተሉት ሁለት ትርጉሞች ሊሰጡት ይችላል።
1⃣ #ማለደ ማለት አንድ ሰው ጉዞ ለመጀመር ወይም በሥራ መስክ ለመሰማራት ጎህ ሳይቀድ (በማለዳ) መነሳቱን ያመለክታል። (ምሳሌ #በማለዳ_ተነስቶ_ገሰገሠ፤ #ማልዶ_ተነሳ. . . . .ወዘተ)
2⃣ #ማለደ ስንል አንድ ሰው በደንብ የሚያውቀውን ሰው ስለሌላ ሦስተኛ ሰው ጉዳይ ለመነው፤ ይቅር እንዲለው፤ ዕዳው እንዲሰረዝለት ለመነለት (ማለደለት) ማለት ነው።
በተራ ቀጥር ሁለት ትርጉም መሰረት የአማላጅነት ሥራ ሦስት ሰዎችን ያካትታል። እነርሱም ሀ) #አማላጁ ለ) #ተማላጁ ሐ) #የሚማለድለት_ሰው ናቸው።
አማላጅ ተማላጁን በመለመን ዕዳን ያስምራል፤ በደልን ያሰርዛል፤ ይቅር ያስብላል። #አማላጅ ወይም #ተማላጅ የሚለውን ጥያቄ የምንመልሰው ከዚህ ትርጉም አኳያ ነው።
የተባለው የእግሊዘኛ መዝገበ ቃላትም #ማለደ Intercede የሚለውን ቃል #ከመካከል_መግባት go_between ሲል ይፈታዋል።
#መማለድ ሁለት ሰዎችን ወይም ወገኖችን ለማስማማትና ለማስታረቅ በሁለቱ መካከል የመግባት ተግባር ነው። ይህ በሁለት ሰዎች መካከል የመግባት ሥራ በእንግሊዘኛ to mediate (ማስማማት) ይባላል። የሚያስማማው ሰው ደግሞ Intercessor (አስማሚ ወይም አስታራቂ) ይባላል። አስታራቂ አማስታረቅ በሁሉት ሰዎች መካከል የሚገባ ሰው mediator ነው።
የመካከለኛነት አገልግሎት
መማለድና ምልጃ በክርስቶስ የመካከለኛነት ሥራ ውስጥ የሚካተት ሀሳብ ነው። ጊዜያዊና ሊመጣ ላለው ጥላ በነበረው ሥርዓት (ብሉይ ኪዳን) የመካከለኛነት አገልግሎት እንዲሰጡ ሦስት ዓይነት ሰዎች ይቀቡ ነበር። እነርሱም፦
1) #ነቢያት (1ኛ ነገ. 19፥15-16)
2) #ካህናት (ዘፀ. 28 እና 29)
3) #ነገሥታት (1ኛ ሳሙ. 10፥1) ናቸው።
በጥላው ዘመን የነበረው የእነዚህ ሁሉ የመካከለኛነት አገልግሎት ዘላለማዊነት አልነበረውም። ምክንያቱም በሚሞቱበት ጊዜ ማዕከላዊ አገልግሎታቸው ያበቃ ነበር እንጂ ወደ ሰማይ ፈጽሞም አልተላለፈም። የሚተላለፍ ቢሆን ኖሮ ከሰማይ ሆነው ማዕከላዊ አገልግሎት መስጠት ስለሚችሉ በሌሎች መተካት አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን የእነርሱ አገልግሎት ወደ ሰማይ መተላለፍ ስላልቻለ በምትካቸው ሌሎችን መሾምና መተካት ግዴታ ነበር። በጥላው ዘመን ማዕከላዊ አገልግሎት የሰጡት ሰዎች ቁጥር ብዙ የሆነበት ምክንያት ለዚህ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚህ ነገር ሲጽፍ፤ #እነርሱም_እንዳይኖሩ_ሞት_ስለከለከላቸው_ካህናት_የሆኑት_ብዙ_ናቸው። ይላል። ዕብ. 7፥23
የአዲስ ኪዳን መካከለኛ #ኢየሱስ #ክርስቶስ ግን ሹመቱ እንደ አሮን የክህነት ሥርዓት ሳይሆን እንደ መልከ ጸዴቅ የክህነት ሥርዓት በመሆኑና በሞት ባለመሸነፉ የዘላለም ካህን ነው። ስለሆነም የእርሱ የመካከለኛነት አገልግሎቱ ወደ ሰማይ ለመተላለፍ ችሏል።
ዕብ. 7፥24-25
ከላይ በተመለከትነው ጥቅስ መሰረት የክርስቶስ የመካከለኝነት አገልግሎት እንደ ጥላው ዘመን አገልጋዮች አይለዋውጥም። በምድር በነበረበት ጊዜ ሆነ አሁን በሰማይ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ሳለ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ዘላለማዊ ካህን የለም።
#ሐዋርያው_ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍ 1ኛ ቆሮ. 8፥5-7
አህዛብ ሰፈር ቁጥር የሌላቸው አማልክቶች አሏቸው። የአማልክቶቻቸው ቁጥር የሚያንስ ከሆነም አማልክቶቹን የሚፈጥሩ እነርሱ በመሆናቸው የፈለጋቸውን ያህል መጨመር ይችላሉ። ነገር ግን ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው የክርስቲያም አምላክ አንድ ብቻ ነው። በአብና በሰው መካከል ያለው መካከለኛም አንድ ብቻ ነው። #አንድ_ፀሐይ_ብቻ_በሰማይ_ላይ_እንዳለች_እሷም_ለዓለም_ሁሉ! _ስለምትበቃ_እግዚአብሔር_ሌላ_ጸሐይ_መፍጠር_እንዳላስፈለገው_ሁሉ፤ ለሰዎችም መካከለኛ ሲሰጥ ከመረቀው ከአንዱ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ መካከለኛ ለሰዎች መስጠት አላስፈለገውም፤ አልሰጠምም።
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7
ይህን መልእክት ቢያንስ ለአንድ ሰው #ሼር አድርጉት።
#Share