ደርሶ እየጠቆረ
ደርሶ እየዳመነ ይህ የክረምት ሰማይ
ናፍቆት እያዘነበ በምስኪን ነፍሱ ላይ፤
በሴቃ እየሞላ
በአሳር እያሰቃየ ትዝታ ግምግምታው፤
ብትት የሚያደርገው
ድንግጥ የሚያሰኘው ምስሉ እና ብልጭታው፤
ቦግ እልም እያለ
ሽው ጥፍት እያለ ፍቅሩን ቀስቅሶበት፤
ሌት ቀን የሚያስነባው ሚሞላው በጭንቀት፤
ይህ የእግዚየር ሰማይ
ጠላቱ የሆነ አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ማለዳም ምሽትም
ፀሀይም ጨረቃ ኮኮብም ቢወጣ፤
በተስፋ ብርሀኖች
በምኞት መንገዶች ትዝታ እየመጣ፤
ወደፊት እንዳይሄድ
ወደ ኃላ ስቦ ወደ ኃላ ወስዶ፤
ዛሬውን እንዳይኖር
አሁንን እንዳያይ በትናንት ቀፍድዶ፥
አሳሩን ሚያበላው!
ስቃዩን ሚያሳየው!
ይህ የእግዚየር ሰማይ
ጠላቱ የሆነ አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ዛፉ ሳር ቅጠሉ ድምፅ እየፈጠረ፤
ተፈጥሮው በሙሉ ስንኝ እየቋጠረ፤
ከአእዋፍ የሚዋሀድ ዜማ እየቀመረ፤
በሄደበት ሁሉ እየተከተለ
በትዝታ ቅኝት እያንጎራጐረ
ትዝ ወደ'ሚለው ድምፅ
ነፍስያውን ወስዶ ስላም እየነሳ፣
በሀሳብ እየዋዠቀ በአካል እንዲሳሳ፤
ሰማዩ መሬቱ፣
ሁሉ ዘፍጥረቱ፣
የሆነ ጠላቱ!
አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
በዛች ጠባብ ቤቱ
ብቸኝት ሰፍቶት ውቂያኖስ ሁኖበት፤
ምስኪን ጀልባ ልቡን
ናፍቆት ማእበሉ ትዝታ አናውጦበት፤
ላለመውደቅ ሚቀዝፍ፣
ላለመስመጥ ሚጥር ፤
በነፍስ ግቢ ውጪ በጭንቀት ሚጣጥር፤
የገዛ ንብረቱ፣
የሆነ ጠላቱ!
አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ምናልባት ምናልባት
በህልም አለም ውስጥ
ተከስቶ ካየሽው
ወይ በእብደት ዓለም ውስጥ
ዙሪያ ካገኘሽው
ያ ወንድኮ እኔ ነኝ !
ያ ወንድ "አዳምሽ" የፍጥረትሽ ፍንጩ
አንቺን ሲጠብቅ የደረቀ ምንጩ።
ጸሃፊ Abu
ከተመቻችሁ እስኪ ጆይን በሉልኝ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥
ደርሶ እየዳመነ ይህ የክረምት ሰማይ
ናፍቆት እያዘነበ በምስኪን ነፍሱ ላይ፤
በሴቃ እየሞላ
በአሳር እያሰቃየ ትዝታ ግምግምታው፤
ብትት የሚያደርገው
ድንግጥ የሚያሰኘው ምስሉ እና ብልጭታው፤
ቦግ እልም እያለ
ሽው ጥፍት እያለ ፍቅሩን ቀስቅሶበት፤
ሌት ቀን የሚያስነባው ሚሞላው በጭንቀት፤
ይህ የእግዚየር ሰማይ
ጠላቱ የሆነ አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ማለዳም ምሽትም
ፀሀይም ጨረቃ ኮኮብም ቢወጣ፤
በተስፋ ብርሀኖች
በምኞት መንገዶች ትዝታ እየመጣ፤
ወደፊት እንዳይሄድ
ወደ ኃላ ስቦ ወደ ኃላ ወስዶ፤
ዛሬውን እንዳይኖር
አሁንን እንዳያይ በትናንት ቀፍድዶ፥
አሳሩን ሚያበላው!
ስቃዩን ሚያሳየው!
ይህ የእግዚየር ሰማይ
ጠላቱ የሆነ አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ዛፉ ሳር ቅጠሉ ድምፅ እየፈጠረ፤
ተፈጥሮው በሙሉ ስንኝ እየቋጠረ፤
ከአእዋፍ የሚዋሀድ ዜማ እየቀመረ፤
በሄደበት ሁሉ እየተከተለ
በትዝታ ቅኝት እያንጎራጐረ
ትዝ ወደ'ሚለው ድምፅ
ነፍስያውን ወስዶ ስላም እየነሳ፣
በሀሳብ እየዋዠቀ በአካል እንዲሳሳ፤
ሰማዩ መሬቱ፣
ሁሉ ዘፍጥረቱ፣
የሆነ ጠላቱ!
አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
በዛች ጠባብ ቤቱ
ብቸኝት ሰፍቶት ውቂያኖስ ሁኖበት፤
ምስኪን ጀልባ ልቡን
ናፍቆት ማእበሉ ትዝታ አናውጦበት፤
ላለመውደቅ ሚቀዝፍ፣
ላለመስመጥ ሚጥር ፤
በነፍስ ግቢ ውጪ በጭንቀት ሚጣጥር፤
የገዛ ንብረቱ፣
የሆነ ጠላቱ!
አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ምናልባት ምናልባት
በህልም አለም ውስጥ
ተከስቶ ካየሽው
ወይ በእብደት ዓለም ውስጥ
ዙሪያ ካገኘሽው
ያ ወንድኮ እኔ ነኝ !
ያ ወንድ "አዳምሽ" የፍጥረትሽ ፍንጩ
አንቺን ሲጠብቅ የደረቀ ምንጩ።
ጸሃፊ Abu
ከተመቻችሁ እስኪ ጆይን በሉልኝ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥