ተውሒድ እና ሽርክ
ክፍል አስራ ስምንት
12.5 የሺርክ አደጋ አስከፊነት
የሺርክ አደጋው እጅግ ዘግናኝ ስለሆነ ነው ነብዩላህ ኢብራሂም እኔንም ልጆቼንም ጣኦትን ከማምለክ ጠብቀኝ ማለታቸው።
የሺርክን አስከፊነት ለመረዳት ከሚረዱ ዋና ዋና ነጥቦች ውስጥ አንዱ አላህን ፍፁም ወዳጅ አድርጎ የያዛቸው፣ የነብያት አባት፣ነብዩላህ ኢብራሂም እኔንም ልጆቼንም ከሺርክ(ከጣኦት አምልኮ) አርቀን ማለታቸው ብቻ ይበቃል ። ነብዩላህ ኢብራሂም (አለይሂ ሠላም) ጌታቸውን ከሺርክ እንዲጠብቃቸው እንደለመኑት አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል ፦
وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِيمُ رَبِّ ٱجْعَلْ هَٰذَا ٱلْبَلَدَ ءَامِنًۭا وَٱجْنُبْنِى وَبَنِىَّ أَن نَّعْبُدَ ٱلْأَصْنَامَ
ኢብራሂምም ባለ ጊዜ (አስታውስ) «ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን፡፡
رَبِّ إِنَّهُنَّ أَضْلَلْنَ كَثِيرًۭا مِّنَ ٱلنَّاسِ ۖ فَمَن تَبِعَنِى فَإِنَّهُۥ مِنِّى ۖ وَمَنْ عَصَانِى فَإِنَّكَ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ
«ጌታዬ ሆይ! እነርሱ (ጣዖታት) ከሰዎች ብዙዎችን አሳስተዋልና፡፡ የተከተለኝም ሰው እርሱ ከኔ ነው፡፡ ትእዛዜንም የጣሰ ሰው አንተ መሓሪ አዛኝ ነህ፡፡[ኢብራሂም 35-36]
ዛሬ አንዳንድ “ዘመናዊ ነን፣ሰልጥነናል፣የዱንያ ትምህርት አለን፣የከተማ ሰዎች ነን”የሚሉ ሸይጧን እና ነፍስያ የተጫወቱባቸው ግለሰቦች “ዘመን ሰልጥኗል፣“እንደኔ የተማሩት ን ሽርክ አያሰጋንም ወይንም የዚህን ቃል ፅንሰ ሀሳብ የመሰለ የሚናገሩ ”፣ “ሽርክ እኮ ገጠር ያሉ ሰዎች ላይ ነው ያለው ”እና የመሳሰለውን ምክንያት በመደርደር የሽርክን ነገር አቅልለው ሲያዩ ይታያሉ።ለነዚህ የዲን እውቀት አልባ ለሆኑ ሰዎች የምንላቸው መጀመሪያ ዲንን ጠንቅቃችሁ እወቁ።አላህ ፍፁም ወዳጅ አድርጎ የያዘው ነብዩላህ ኢብራሂም “እኔንም ልጆቼንም ጣኦትን ከመገዛት አርቀን” ካለ እኛ ማን ነንና ሽርክን ለነፍሳችን እና ለቤተሰባችን ማንሰጋው ?አለ ማወቅ ከባድ አደጋ ነው።እጥፍ ድርብ የሆነው ከባድ አደጋ ደሞ እውቀትም እንደሌለንም አለማወቃችን ነው።
12.6 ሺርክ ዘላለማዊ የጀነም ማገዶ ያደርጋል
ለዚህም ማስረጃው አጋሪያን ጀነት እንደማይገቡና ዘላለማዊ መኖርያቸው ጀሐነም እንደሆነ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል፦
إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ
እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ይሉናል “ከአላህ ሌላ ያለን አካል (አጋርን) እየጠራ (እያመለከ) የሞተ እሳት ገባ ።” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
12.7 ሺርክ ከእስልምና ውጭ ያደርጋል
ለዚህም ማስረጃው የሚከተለውን የአላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ንግግር ነው።
وَلَا تَدْعُ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَ ۖ فَإِن فَعَلْتَ فَإِنَّكَ إِذًۭا مِّنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
«ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)፡፡ (ዩኑስ:106)
ታላቁ የተፍሲር ሊቅ ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጦበሪይ እና ሌሎችም እንዳብራሩት “ከበደለኞች” የሚለው ቃል ከአጋሪዎች ማለት እንደሆነ ጠቁመዋል።በዚህም የተነሳ ነው የኢስላም ሊቃውንቶች ሺርክ ከእስልምና ያስወጣል የሚሉት ።
✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
(ተውሒድ እና ሽርክ ገፅ 36-38)
“ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide