በረመዳን ምን ይጠበቅብናል ?
ክፍል ❼
5. ከተከበሩ ወቅቶች መጠቀም
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ፡-
“አላህ ለአንዳንድ ወራት የተለየ ክብር ሰጥቷል። አንዳንድ የለሊትና የቀን ክፍሎችን ልዩ ክብር እንደቸረ ማለት ነው። ለይለቱልቀድርን ከአንድ ሺህ ወራት በላይ እንድትሆን አድርጓል።…
እያንዳንዱ ልዩ አጋጣሚ ወደ አላህ የምንቃረብበት የራሱ የሆነን ተግባር አካቷል። በእነዚሁ አጋጣሚዎች አላህም ለባሮቹ የሚቸረው ልዩ ስጦታ አለው።
እድለኛ ማለት እነዚህን አጋጣሚዎች ጌታውን ለማገልገል በመንቀሳቀስ የተጠመደና በተከበሩት ወራትና ሰዓቶች ውስጥ ያለውን የጌታ ስጦታ የዘረፈ ሰው ነው። እነዚህን ስጦታዎች ማግኘት ማለት ከእሳት እራስን መጠበቅ ማለት ነው።
የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-“ጌታችሁ በአመቱ ቀናት ውስጥ ታላላቅ ስጦታዎች (ነፈሓት) አሉት። እራሳችሁን ለነርሱ አቅርቡ። ምናልባት አንዱን ስጦታ ያገኘ ሰው ለዘላለም እድለቢስ አይሆንም።”
እራሱን ለነዚህ ነፈሓት ያቀረበ ያለጥርጥር ትርፎችን ያገኛል። ዝንጉ የሆነና እራሱን ለስጦታዎቹ ያላቀረበ የተነፈገ ሰው ነው!!
በሀያ አራት ሠዓት ውስጥ ወደ አላህ ይበልጥ የምንቀርብባቸው ሦስት ወቅቶች አሉ። እነርሱም የለሊቱ መባቻ፣ የቀኑ መጀመሪያ እና የቀኑ መጨረሻ ናቸው።
የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-
إن هذا الدين يسر ولن يشاد الدين أحد إلا غلبه فسددوا وقاربوا وابشروا واستعينوا بالغدوة والروحة وشيء من الدلجة
“ይህ ዲን ገር ነው። ዲንን የሚያካብድ ሰው የለም የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ። (በአላህ ትእዛዝ ላይ) ቀጥ በሉ። መሀለኛ ሁኑ። አይዟችሁ። በጧትና በከሰዓት እንዲሁም በለሊቱ ጥቂት ሠዐት ታገዙ።”
የጧትና የምሽት ውዳሴን የዘገቡ ብዙ ሐዲሶች ላይ ጧትና ማታ አላህን ማወደስ ልዩ ትርፍ እንዳለው ተጠቅሶ እናገኛለን። ሰለፎች በበኩላቸው የከሰዓት በኋላውን ጊዜ ከመጀመሪያው ይበልጥ ያልቁት ነበር።
ኢማም ሐሰን አል-በና እንዲህ ይላሉ፡-
أيها الأخ العزيز أمامك كل يوم لحظة بالغداة ولحظة بالعشى ولحظة بالسحر تستطيع أن تسمو فيها كلها بروحك الطهور إلى الملأ الأعلى، فتظفر بخير الدنيا والأخرة.. وأمامك مواسم الطاعات وأيام العبادات وليالي القروبات التي وجهك إليها كتابك الكريم ورسولك العظيم صلى الله عليه وسلم، فأحرص أن تكون فيها من الذاكرين لا من الغافلين، ومن العاملين لا من الخاملين.. واغتنم الوقت فالوقت كالسيف، ودع التسويف فلا أضر منه
“የተከበርክ ወንድሜ ሆይ! በጧት፣ ከሰዓት በኋላና ዶሮ ጩኸት አካባቢ ንፁህ መንፈስህን ወደ ላይኞቹ ባለሟሎች ማሳደግ ትችላለህ።
ከዚያም የዱንያና የአኼራን ኸይሮች ታገኛለህ።… ከፊትህ ወደ አላህ የምትቃረብባቸው፣ ለአላህ ይበልጥ ታዛዥ መሆንህን የምትገልፅባቸው፣ አምልኮ ላይ የምትበረታባቸው ጊዜያት አሉ።
እነዚህን ቀናቶች እንድትጠቀምባቸው ቁርአንና መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) አስተምረውሀል። ስለዚህ በነዚህ ጊዜያት አላህን ከሚያወሱ እንጂ ከሚዘናጉ እንዳትሆን። ከሠራተኞች እንጂ ከሥራ ፈቶች እንዳትደመር።…
ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም። ጊዜ ሰይፍ ነው። ነገ-ዛሬ ማለትን ተው። ከርሱ የበለጠ ጎጂ ነገር የለምና።”
በየሳምንቱ የሚከሠቱ ልዩ ወቅቶችም አሉ። ከቀናት ውስጥ የጁሙዓ ቀን ታላቅ ክብር አለው።
ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ልዩ ሠዓትን በውስጡ አካቷል። ስለዚህ ለዚህ ቀን ስጦታ ራሳችንን እናቅርብ። ኢማም አን-ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፡-
“የጁሙዐህ ቀን ውስጥ ከፈጅር ጀምሮ ፀሐይ እስከሚጠልቅ ድረስ በሙሉ ዱዓ ማብዛት ይወደዳል።
ምክንያቱም የኢጃባው (ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት) ሠዓት መች እንደሆነ ስለማይታወቅ እንዳያመልጠን ለማድረግ ነው። ይህ ቀን ላይ ለዒባዳ መታገል አለብን።
ልዩ የዒባዳ ፕሮግራምም ልናወጣለት ይገባል። የጁሙዐህ ሶላታችንን ለማሳመር ጧት በጊዜ ወደ መስጂድ እንሂድ።…”
ረመዳን ከወራት መሀል ልዩ እንደመሆኑ ለይለቱል-ቀድር ደግሞ ከረመዳን ቀናቶች መሀል ልዩ ስፍራ አለው።
የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
من قام ليلة القدر إيمانا واحتسابا غُفر له ما تقدم من ذنبه
“ለይለቱል-ቀድርን በኢማንና ከአላህ አጅር አገኛለሁ ብሎ በማሰብ የቆመ ሠው ያስቀደመውን ኃጢያት ሁሉ ይማራል።”
ለይለቱል-ቀድርን መፈለግ የሚገባው አስሩ የመጨረሻ የረመዳን ቀናት ላይ ነው። ስለዚህ እጅግ በጣም መጠንከር ያስፈልጋል።
ለዚህ ነው“የአላህ መልእክተኛ የረመዳን ወር የመጨረሻው አስር ቀን ሲገባ ሽርጣቸውን ያጠብቃሉ። ለሊታቸውን ህያው ያደርጋሉ። ቤተሰቦቻቸውን ያነቃሉ።”
ከእነዚህ ምርጥ የስጦታ አጋጣሚዎች መሀል ሌላኛው የዑምራ አጋጣሚ ነው። ሁላችንም ይህን ስጦታ ለማግኘት እንመኝ።ሁሉ ነገራችንን ለእነዚህ ስጦታዎች ለመጣድ እናሰናዳ። አንዱ አጋጣሚ ቢያመልጠን ሌላኛውን ለማግኘት እንታገል።
6. ኢዕቲካፍ
ኢዕቲካፍ መስጂድ ውስጥ መቆየት ማለት ነው። ረመዳን ውስጥም ይሁን ከረመዳን በኋላ የሚወደድ ዒባዳ ነው። በተለይ የረመዳን አስሩ ቀናት ውስጥ ይበልጥ ይወደዳል።
ምክንያቱም እነዚህ ቀናት ውስጥ ከአንድ ሺህ ወራት በላይ የሚሆነው ለይለቱል-ቀድር ይገኛል። ኢማም አህመድ ኢዕቲካፍ የሚያደርግ ሰው ከሠዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ባይኖረው ይመርጣሉ።
ቁርአን ለማስቀራት ወይም ዒልም ለማስተማርም ቢሆን ከሠዎች ጋር ባይገናኝ ጥሩ ነው። ኢዕቲካፍ ያደረገ ሰው መገለል ይወደድለታል። ከጌታው ጋር በመዋየትና በዱዓ ቢጠመድ መልካም ነው።
ይህ መገለል (ኸልዋ) የጀመዓና የጁሙዓ ሶላት የማይተውበት ሸሪዓዊ ተግባር ነው። በረመዳን ቀናት ውስጥ ምንም ቢያጥር የተወሰነ ሰዓት ኢዕቲካፍ ነይተን የምንቀመጥበት ሠዓት ያስፈልገናል።
በተለይም በአስሩ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ አብዝሀኛ ጊዜያችንን በመስጂድ ውስጥ ማሳለፍ አለብን። ቀን ሥራ ላይ የሚያሳልፍ ወይም በቀን ኢዕቲካፍ ማድረግ የማይችል ሠው ለሊቱን ይጠቀም።
መስጂድ ኢዕቲካፍ ብለን ከገባን ደግሞ ከአላስፈላጊ ቅልቅልና ከማይጠቅም ወሬ መገለል ያስፈልጋል። ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ፡-“የኢዕቲካፍ ዓላማ ለፈጣሪ ኺድማ ሲባል ከፍጡራን ጋር ያለንን ግንኙነት ማቋረጥ ነው።”
ሙስሊም እህቶቻችንም በቤታቸው መስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ ይችላሉ፤ እንደ ሐነፊያዎች አስተያየት።
ስለዚህ ከቀን ውስጥ የተወሰኑ ሠዓታትን ወደ አላህ ለመዞር የቤቷ መስጊድ ውስጥ ብትቀመጥ ይበቃታል።
..........ይቀጥላል
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂
🍀 ዲነል ኢስላም Tube
🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"
http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube