በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?
ክፍል ❾
“ዓቅል ያላቸው ሰዎች ዚክርን ከፊክር ጋር ፊክርንም ከዚክር ጋር ከማቆራኘት አልቦዘኑም። ከዚያም ልባቸውን አናገሩት ጥበብ ተናገረ።” ብለዋል፤ ሐሰኑል በስሪይ።
የዚክር መጀመሪያው ተፈኩር ነው። አንድን ጉዳይ አስታውሶ ከማስተንተን ዚክር ይወለዳል። ለምሳሌ አንድ ሰው ወንጀሉን ካስታወሰ እና ከአላህ መብት ያጓደለውን ካስተነተነ ኢስቲግፋርን ያስከትላል።
የአላህን ጥበብና ኃያልነት የሚጠቁሙ ፍጥረታትንና ተአምራትን ሲመለከትና ሲያስተነትን ተስቢሕና ተሕሚድ (ምስጋናና አላህን ከጉድለት ማጥራት) ይከተላል።
ከባድ ችግር ሲገጥመውና ወደ አላህ ያለውን ክጃሎት ሲያስብና ሲያስተነትን “ላሐውለ ወላቁው-ወተ ኢል-ላ ቢል-ላሂል-ዓሊዪል ዓዚም” ይላል፤ ከአላህ በቀር ኃይልና ብልሀት የለም ማለት። ሌሎችም ዚክሮች ላይ እንዲሁ፤ ከፊክር ዚክር ይወለዳል።
ለነፍሳችን የዚክርና የፊክር ፕሮግራም እናድርግ። ከዚያም የዚክር ፋይዳ ወደ ልብ እንዲደርስ የሚያስፈልገውን እናድርግ። የሥራችን ምንዳ የሚሟላው በሠራነው ሥራ ምሉዕነት ተመዝኖ ነው። ሥራዎች በቅርፃቸውና በቁጥራቸው አይለያዩም። የሚለያዩት ልብ ውስጥ ባለው የተመስጥኦ ልዩነት ብቻ ነው። ስለዚህ የሁለት ሥራዎች ቅርፅ አንድ ሆኖ የሠማይና የምድር ያህል ልዩነት ሊኖራቸው ይችላል።
የጧትና የማታ ዚክር ውስጥና የአንዳንድ ሁኔታዎች (አዝካሩል አህዋል) ዚክር ላይ መንፈስን የሚያነቁ ታላላቅ ጉዳዮች ተወስተዋል። ስለዚህ እነዚህን ዚክሮች በወቅታቸው ስንላቸው ውስጣቸው ያቀፈውን ትርጓሜ መዘንጋት የለብንም። ማስተንተን አለብን።
10. ነፍስን መተሳሰብ
ከጥቂት የረመዳን ቀናት በኋላ ነፍስ ለጌታዋ መመሪያ ታዛዥ ትሆናለች። ስለዚህ ባሳለፈችው ጊዜ ስለሠራችው ሥራ መተሳሰብ ብንጀምር አታስቸግረንም። ነፍሳችንን የምንተሳሰብባቸው የተለያዩ ጉዳዮች አሉ።
እነዚህ ጉዳዮች የሙስሊምን ህይወት በሙሉ የከበቡ ናቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰው እያንዳንዱን የህይወቱን ክፍል መገምገም እና ማስተዋል ይጠበቅበታል። ከዚያም እያንዳንዱ ጉዳይ ላይ እግሩ ያረፈበትን ደረጃ መመልከት ይችላል።
በተለይም ኃጢያታችንን ብንቆጥርና ያጓደልናቸውን ሐቆች ብንዘረዝር መልካም ተውበት እንድናደርግና አካሄዳችንን እንድናሳምር ጠቃሚ ጉልበት ይሰጠናል።
የሙሐሰባ (ራስን የመተሳሰብ) ፈኖች
የአካል ዒባዳዎች፡- አምስት ወቅት ሶላቶችን በመጀመሪያ ወቅታቸው ላይ መስጂድ ውስጥ መስገድ፣ ፈርድ ሶላቶችን ተከትለው የሚመጡትን ሱናዎች መስገድ፣ የሶላት ዚክሮችን ማሟላት፣ የረመዳን ፆምና ሱና ፆሞች፣ በአላህ መንገድ አዘውትሮ መለገስ፣ የጧትና የምሽት ዚክር፣ ንግግርና ተግባር ላይ ሱናን መጠበቅ….
የአካል ኃጢያቶች:- ሐሜት፣ ነገር ማዋሰድ፣ ሰው ላይ ማሾፍ፣ ስላቅ፣ ክርክር፣ የሠውን ምስጢር ማጋለጥ፣ ዘለፋ፣ ውሸት፣ ውድቅ ንግግር፣ የማያውቁትን ማውራት (ሰርሰራ)፣ ዓይንን ከክልክል እይታ አለመጨፈን፣ ብላሽ ነገር ውስጥ መዘፈቅ፣ ቸኩሎ መቆጣት፣ ቃል ኪዳንን ማፍረስ….
የልብ አምልኮዎች:- ሶላት ውስጥ ኹሹዕ (ተመስጥዖ)፣ አላህን መፍራትና እርሱን መጠባበቅ (ሙራቀባህ)፣ የአላህን ውሳኔና ፍርድን መውደድ፣ በአላህ መመካት፣ በአደጋ ጊዜ መታገስ፣ በፀጋ ጊዜ ማመስገን…
የልብ ኃጢያቶች:- በራስ ሥራ መደነቅ፣ መልካም ሥራው እንዲሠማለት መፈለግ፣ ትችትን መስጋት፣ ምቀኝነት፣ ራስን ማታለል፣ ፉክክር፣ በሥጦታ መመፃደቅ፣ ሌሎችን መናቅ፣ ስሜትን መከተል፣ ቂም…
ሐቆች:- የሚስት/የባል ሐቅ፣ የልጆች ሐቅ፣ የወላጆች ሐቅ፣ የዝምድና ሐቅ፣ የጎረቤት ሐቅ፣ የመንገድ ሐቅ፣ የዳዕዋ ሐቅ፣ የወንድማማችነት ሐቅ….
መልካም ሥራዎች፡- የሙስሊሞችን ጉዳይ ለመፈፀም መሯሯጥ፣ ጎንን ማቅለል፣ መተናነስ፣ ህመምተኛን መጠየቅ፣ አስክሬን መሸኘት፣ መልካምን ነገር ለሌሎች መዋል፣ አደራን መወጣት፣ ደስታንና ፈገግታን ማሳየት፣ ሥራን አሳምሮ መሥራት…
ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት እራሳችንን የምንገመግምባቸው ነጥቦች ናቸው። ከእያንዳንዱ ግምገማ በኋላ የአላህን ምህረት መለመን አለብን።
ከተቻለንም በውስጧ ኢስቲግፋር የምናበዛባት ሶላት (ሶላቱት-ተውባ) ብንሰግድ መልካም ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ
“ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ። (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች)።” (አሊ ዒምራን 3፤ 135)
የዘጠነኛው ክፍል ማጠቃለያ
እዚህ ክፍል ውስጥ የተጠቀሱት የረመዳንን ፍሬዎች የምንጠቀምባቸው አስር ነገሮች ናቸው። እነዚህን ጥቆማዎች አስታከን ወሩን በሙሉ የምንገለገልበት ፕሮግራም ብናወጣ መልካም ነው።
ለእያንዳንዱ ቀንም የማንለውጣቸው ቋሚ ሥራዎች እንያዝ። መስጂድ ውስጥ ለምናደርገው ኢዕቲካፍ ቋሚ ጊዜ እንወስን።
ከፈጅር ሶላት በኋላ ፀሐይ እስከሚወጣ ድረስ ብናደርገው፤ ይህን ካልቻልን ደግሞ ከዐስር ሶላት በኋላ እስከ መቅሪብ ሶላት ድረስ ብንወስን፤ ይህንን የኢዕቲካፍ ጊዜያችንን ከዚህ በፊት በተናገርነው መልኩ ቁርአን በመቅራት ብናሳልፍ ጥሩ ሠርተናል።
ቤታችን ውስጥ አንድ ሳጥን ብናዘጋጅና የየቀን ሶደቃችንን እዚያ ውስጥ ማጠራቀም ብንለምድ። ከፈጅር በፊት ሰላሳ ደቂቃም ቢሆን ከሶላቱ-ት-ተራዊሕ ውጭ ለተሀጁድ የተወሰነ ጊዜ ብናደርገው…
ከዚክሮች መሀል በቀን ቢያንስ መቶ ጊዜ “ሱብሐነል-ላሂ ወቢሐምዲሒ” ብንል፣ መቶ ጊዜ ኢስቲግፋር ብናደርግ፣ “አል-ላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወአሊሂ” እያልን መቶ ጊዜ በነብዩ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ሶለዋት (እዝነት) ብናወርድ፣ መቶ ጊዜ “ላሓውለ ወላ ቁው-ወተ ኢል-ላ ቢል-ላሂል-ዓሊዪል ዓዚም” ብለን ኃይልም ሆነ ብልሀት እንደሌለን ብናውጅ….
ከዚያም እነዚህን ዚክሮች ለቀንና ለሌት ብንመድባቸው ዚክራችንን አሳምረን ሰራን ማለት ነው።
ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝባቸውን ወቅቶች ጠብቀን አብዝተን ዱዓ ብናደርግ፣ ባህር ውስጥ ሊሰምጥ እንደቀረበ ችግረኛ ጌታችንን ብንለማመን፣ ለወንድሞቻችን እና ለሙስሊሞች ባጠቃላይ ዱዓ ብናደርግ ዱዓንም አሳምረን አደረግን ማለት ነው።
አንዳንድ ወቅቶች ላይ ደግሞ ከሠዎች ተነጥለን ያሳለፍነውን ሁሉ እያሰብን ምህረት ብንለምን ስራችንን በግምገማ ጠበቅነው።
ያለንበትን የኢማን ደረጃም አወቅን ማለት ነው። ከዚያም ስህተታችንን ለማረምና ይበልጥ ለማደግ በኢስቲግፋር አዲስ መዝገብ መጀመር ነው።…
.........ይቀጥላል
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂
🍀 ዲነል ኢስላም Tube
🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"
http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube