FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ይህ ትክክለኛ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቴሌግራም ቻናል ነው

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter




የጣዕም ልኬት የራዲዮ ፕሮግራም

አዘጋጆች ሰርፀ ፍሬ ስብሐት እና ምዕራፍ ተክሌ


Forward from: EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
"አዲስ ቀን"
ሰኞ ይጀምራል!!
ከጠዋቱ ከ1፡00 እስከ 3፡00 ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ
በኢቲቪ ዜና ቻናል ይጠብቁን!
#etv #EBC #ebcdotstream #አዲስቀን #newday


Forward from: EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
አዲስ ቀን
ሰኞ ጠዋት ከ 1፡00 እስከ 3፡00 ይጠብቁን!
#etv #EBC #ebcdotstream #አዲስቀን #newday


Forward from: EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
ታህሳስ 14 ይጠናቀቃል
**************
ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር ምዝገባ የሚካሄደው እስከ ታህሳስ 14 ብቻ ነው።
የንግድ ፈጠራ ሀሳብ ያላችሁና የመነሻ ካፒታል ለሚያሳስባችሁ ሁሉ ነጋድራስ ለናንተ ነው።
1.8 ሚሊዮን ብር በየምእራፉ ይሸልማል፤ ለአሽናፊዎች አሽናፊ ደግሞ 5 ሚሊዮን ብር አዘጋጅቷል።
በተጨማሪም የፕሮግራሙ ታይትል ስፖንሰር የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለማስያዣ የብድር እድል ያመቻችልዎታል፤ እንዳያመልጥዎ!!
ይመዝገቡ፣ ይወዳደሩ፣ ያሸንፉ
ለመመዝገብ ኪው አር ኮድኑን ስካን ያድርጉ አልያም ዌብ ሳይቱን ይጠቀሙ
www.ebc.et


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አዲስ ቀን
ከሰኞ - አርብ ጠዋት 1፡00 - 3፡00




አዲስ ቀን


Forward from: EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ የነበራቸውን ስብሰባዎች አገባደው ዛሬ ጠዋት አትዮጵያ ገብተዋል::
#PMOEthiopia


"ከሰውነቱ ውስጥ 110 ብረታ ብረቶች በቀዶ ህክምና የወጡለት ታካሚ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል" - ሆስፒታሉ
******************

ከሰውነቱ ውስጥ 110 ብረታ ብረቶች በቀዶ ህክምና የወጡለት ታካሚ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡

በሆስፒታሉ ጠቅላላ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ዳግማዊ ዳኜ ለኢቢሲ ዶትስትሪም እንደገለፁት፤ ታካሚው በትናትናው ዕለት በተደረገለት የአንጀት ቀዶ ህክምና እንደ ቁልፍ፣ ሚስማር እና ብሎን ያሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች ተወግዶለታል፡፡

ታካሚው በተደረገለት የተሳካ የቀዶ ህክምናም በአሁኑ ወቅት በማገገሚያ ክፍል ውስጥ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ከ46 እስከ 48 ዓመት የሚገመተው ይህ ታካሚ በሆስፒታሉ ለብዙ ጊዜ የአዕምሮ ታማሚ ሆኖ ሲመላለስ እንደነበርም ዶ/ር ዳግማዊ ተናግረዋል፡፡

ታካሚው በተደጋጋሚ ጊዜ እንደ ማስመለስ፣ ሰገራ አለመውጣት እና ሆድ መንፋት ያሉ የጤና እክሎች ሲያጋጥሙት እንደነበር የገለፁት ዶ/ር ዳግማዊ፤ በቅርቡም እነዚሁ ችግሮች አጋጥመዉት ወደ ሆስፒታሉ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡

https://web.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid02zVmWLRfj2skpeGiNYmzRsDWYSxC1idufbAz3iHNWBvXUmBpgqfJbiqXco8zD3feol&id=100063770933024


Forward from: EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
ለነጋድራስ ተመዝግበዋል?
*************

ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ፈጠራ ዉድድር ምዝገባ ታህሳስ 15 ይጠናቀቃል፡፡

በየዙሩ 1.8 ሚልዮን ብር ሽልማት ፤ ምርጥ አምስት ዉስጥ ለሚገቡ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ያለማስያዣ የብድር እድል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያገኙበት የምእራፍ አራት ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንት ብቻ ይቀራል፡፡

የስራ ሀሳብዎን ወደ ነጋድራስ በማምጣትዎ ስራዎን ያስተዋዉቃሉ፤ ከአንጋፋ ዳኞች ጠቃሚ ምክር ያገኛሉ ፤ ያለማስያዣ የብድር እድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ፡፡

ለመመዝገብ ኪዉአር ኮዱን ስካን ያድርጉ፤ አለያም ሊንኩን ይጠቀሙ፡፡
ይመዝገገቡ ፡ ይወዳደሩ፡ ይሸለሙ

https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx


Forward from: ETV መዝናኛ
በኢትዮጵያ አይዶል ለመወዳደር ባሉበት ከተማ አሁኑኑ ይመዝገቡ!!
********************

የኢትዮጵያ አይዶል ምዝገባ የሚካሄድባቸው 21 የክልል ከተሞች
የሻሸመኔ፣ ቦንጋ፣ ጋምቤላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ደብረብርሀን፣ አርባምንጭ፣ ደሴ፣ ሰመራ፣ ነቀምት፣ ጎንደር፣ አዲግራት፣ አዳማ፣ መቐሌ፣ ባህርዳር፣ አሶሳ፣ ጅማ፣ ሐዋሳ፣ ሐረር እና ሆሳዕና ከተሞች የኢትዮጵያ አይዶል ተወዳዳሪዎች የመመዝገቢያ ቦታዎች አድራሻ።

የኢትዮጵያ አይዶልን ካሉበት ቦታ ሆነው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የቴሌግራም ቦት በነፃ ይመዝገቡ።

የቴሌግራም ቦቱ ሊንክ ከዚህ በታች የተጠቀመጠው ብቻ ነው።

https://t.me/EtvEthiopianidolbot

#የኢትዮጵያአ ይዶል #ኢትዮጵያ #አይዶል #etv #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #musica #IDOL #ethiopianidol


Forward from: ETV መዝናኛ
የኢትዮጵያ አይዶልን በነፃ!!!
***************

የኢትዮጵያ አይዶልን ካሉበት ቦታ ሆነው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የቴሌግራም ቦት በነፃ ይመዝገቡ።

የቴሌግራም ቦቱ ሊንክ ከዚህ በታች👇 የተጠቀመጠው ብቻ ነው።

https://t.me/EtvEthiopianidolbot

ከቴሌግራሙ በተጨማሪ ምዝገባ የሚካሄድባቸው 21 የክልል ከተሞች የሻሸመኔ፣ ቦንጋ፣ ጋምቤላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ደብረብርሀን፣ አርባምንጭ፣ ደሴ፣ ሰመራ፣ ነቀምት፣ ጎንደር፣ አዲግራት፣ አዳማ፣ መቐሌ፣ ባህርዳር፣ አሶሳ፣ ጅማ፣ ሐዋሳ፣ ሐረር እና ሆሳዕና ከተሞች የኢትዮጵያ አይዶል ተወዳዳሪዎች በኢቢሲ ቅርንጫፎች በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ።

#የኢትዮጵያአይዶል #ኢትዮጵያ #አይዶል #etv #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #musica #IDOL #ethiopianidol


Forward from: EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የ20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን አዘጋጅ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆኗል
*******************

በቀጣይ ዓመት የሚከበረው የ20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን አዘጋጅ ክልል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሆኑ ታውቋል።

#etv #ብሔርብሔረሰቦች #ኢቢሲ #DOTSTREAM


Forward from: EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ ከሶማሌ ክልል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተላለፈ
*******************

የኢትዮጵያውያን የወል እውነት የሆነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ በሱማሌ ክልል ላለፈው አንድ አመት ያደረገውን ቆይታ አጠናቅቆ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርክክብ ተደርጓል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫውን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የርክክብ ስነ-ስርአቱን አካሂደዋል።

#etv #ብሔርብሔረሰቦች #ኢቢሲ #DOTSTREAM


Forward from: EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን እየተከበረ ነው
*************

19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በክብረ በዓሉ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እንዲሁም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

#etv #ብሔርብሔረሰቦች #ኢቢሲ #DOTSTREAM



17 last posts shown.