"ከሰውነቱ ውስጥ 110 ብረታ ብረቶች በቀዶ ህክምና የወጡለት ታካሚ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል" - ሆስፒታሉ
******************
ከሰውነቱ ውስጥ 110 ብረታ ብረቶች በቀዶ ህክምና የወጡለት ታካሚ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡
በሆስፒታሉ ጠቅላላ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ዳግማዊ ዳኜ ለኢቢሲ ዶትስትሪም እንደገለፁት፤ ታካሚው በትናትናው ዕለት በተደረገለት የአንጀት ቀዶ ህክምና እንደ ቁልፍ፣ ሚስማር እና ብሎን ያሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች ተወግዶለታል፡፡
ታካሚው በተደረገለት የተሳካ የቀዶ ህክምናም በአሁኑ ወቅት በማገገሚያ ክፍል ውስጥ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከ46 እስከ 48 ዓመት የሚገመተው ይህ ታካሚ በሆስፒታሉ ለብዙ ጊዜ የአዕምሮ ታማሚ ሆኖ ሲመላለስ እንደነበርም ዶ/ር ዳግማዊ ተናግረዋል፡፡
ታካሚው በተደጋጋሚ ጊዜ እንደ ማስመለስ፣ ሰገራ አለመውጣት እና ሆድ መንፋት ያሉ የጤና እክሎች ሲያጋጥሙት እንደነበር የገለፁት ዶ/ር ዳግማዊ፤ በቅርቡም እነዚሁ ችግሮች አጋጥመዉት ወደ ሆስፒታሉ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡
https://web.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid02zVmWLRfj2skpeGiNYmzRsDWYSxC1idufbAz3iHNWBvXUmBpgqfJbiqXco8zD3feol&id=100063770933024