Forward from: መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
ቅዱስነታቸው ዱባይ በሰላም ገብተዋል።
*******************************
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዱባይ በሰላም ገብተዋል። ዱባይ አየር መንገድ ሲደርሱ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር አማረ፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ፣ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎችና በዱባይ የሚገኙ ምዕመናን ተወካዮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ለሐዋርያዊ አገልግሎት ዛሬ ማለዳ ወደ ዱባይ መጓዛቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ፎቶ ግራፍ በመ/ሕ/አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ
ምንጭ: EOTCPR