Yezid Ahimed🕌🌙


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Set your goal in life and try to make it success by starting from very little to enough huge!!!

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: Yasin nuru's hadis
አላህ አያረፍድም :-

📌 ዩሱፍ ላይ እንዳላረፈደው
📌 ያዕቆብን እንዲሁ እንዳልተወው
📌ዩኑስ ላይ እንዳልጨከነው.....

እኛም ላይ አያረፍድም🫶

@yasin_nuru_hadis


Forward from: Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የዳዕዋ ቲቪ አዲስ የዩቲዩብ ቻናል!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

ውድ የዳዕዋ ቲቪ ቤተሰቦች ከ2ሺ በላይ የሚሆኑ የኪታብ ደርሶች፣ፈትዋዎች እንዲሁም የሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን የቁርአን ተፍሲርና የተለያዩ ኢስላማዊ እውቀትን የሚያስጨብጡ ትምህርቶችን ስንናስተላልፍበት የነበረው የዩቲዩብ ገፃችን ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በመጠለፉ ጥልቅ ሀዘናችንን እየገለፅን በምትኩ አዲስ ቻናል ከፍተናል።

ስለሆነም እርሶም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን አዲሱን የዩቲዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ እንዲያደርጉና ለሌሎችም እንዲያስተላልፉ እንጠይቃለን!!!

👉 https://ytbe.one/rzYHUrtM8QU
👉 https://ytbe.one/rzYHUrtM8QU
👉 https://ytbe.one/rzYHUrtM8QU


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
ገንዘብ ደስታን አይፈጥርም ብላችሁ ካሰባችሁ



ብሩን ወደ አካውንቴ ላኩልኝ አለ አንዱ😁

ኧረ አልሃምዱሊላህ እንበል

@yasin_nuru @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
ፍቅር

በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቢላል ኢብኑ ረባህን ከኃላው በፍቅር ስሜት እቅፍ አድርገው ይይዙትና ድምፃቸውን ቀይረው...

❤️ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- "እኔ ማን ነኝ"?

ቢላል (ረ.ዐ) :- ዑመር (ረ.ዐ) ነህ?

❤️ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አይደለሁም

ቢላል (ረ.ዐ) :- አቡብክር (ረ.ዐ) መሆን አለብህ?

❤️ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አሁንም ተሳስተሃል

ቢላል (ረ.ዐ) :- በቃ ዑስማን (ረ.ዐ) ነህ?

❤️ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አላወቅከኝም

ቢላል (ረ.ዐ) :- ዓሊ (ረ.ዐ) ነህ ማለት ነው...
እያለ ያቀፈውን ሰው ማንነት ሲጠይቅ ይቆያል።

ከዚያም ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለቀቅ አደረጉትና ከፊት ለፊቱ በመምጣት

"ቢላል ሆይ! እውነት እኔ መሆኔን አላወቅክም ነበር እንዴ"? ሲሉ ጠየቁት

ቢላልም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" በደንብ አውቄዎታለሁኝ ነገር ግን ለረጂም ጊዜ እንድታቅፉኝ ስለፈለኩኝ እንጂ ሲል መለሰላቸው።

❤️ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይከ ያ ረሱሊላህ❤️

@yasin_nuru @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
የሰው   ዘር   መጀመሪያ  የሆኑት  #አደም።

ልዩ  የክብር  ቦታ  የተሰጣቸው  #እንድሪስ።

950   ዓመታት  በማስተማር  የቆዩት  #ኑህ

ወደዓድ  ህዝቦች  የተላኩት    #ሑድ።

ድንጋይ  ተፈልቅቆ  ግመል  የወጣችላቸው  #የሰሙዱ ሳሊህ።

የኑምሩድን  እሳት ድል  በማድረግ  የወጡት  #ኢብራሒም።

መላእክት በእንግድነት  ወደቤቱ  የገቡት  #ሉጥ።

በካዕባ ግንባታ የተሳተፉት  #ኢስማኢል።

የአባታቸው  የኢብርሂም ልድ #ኢስሐቅ።

የ12  ወንድ  ልጆች  አባት የሆኑት  #ያዕቆብ።

እጅግ ታጋሹና  ጥበበኛው    #ዩሡፍ።

መከራን  ቻዩና  ጸሎተኛው      #አዩብ።

የሁለት  ሴቶች አባት  የሆኑት  የመደኑ #ሹዓይብ።

ባህር  የተሰነጠቀላቸው  የኢምራን  ልጅ #ሙሳና  ወንድማቸው #ሐሩን

በዓሣ  ሆድ  ውስጥ  ዚክር  ያደረጉት  የነይነዋው #ዩኑስ።

ብረት እንደጭቃ  የሚለዝብላቸው ድምጻዊው  #ዳውድ።

ንፋስን  እንደፈለጉ  የሚያዙት  ንጉሱ  #ሱለይማን።

ቁርኣን  ስማቸውን  እንጅ  ያላስዋወቀን አልየሰእ፤ #ኢሊያስና  #ዙልኪፍል።

አናጺውና  የመሪየም  አሳዳጊ  #ዘከርያ።

በልጅነታቸው  ነብይነትን የተሰጡት #ያህያ።

ያለአባት  የተወለዱት  ተአምረኛው  የመሪየም  ልጅ  #ዒሣ።

ለተልእኳቸው  የቦታና  የዘመን  ግርዶሽ        የተነሳላቸው  #ሙሐመድ ናቸው።

እንግዲህ  ከአላህ  ጋር  ያለንን  ግንኙነት ለማስተካከል  በተላኩት  ነቢያት  በሙሉ  ያለምንም  ልዩነት ማመን  ይኖርብናል።

@yasin_nuru     @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
❤️የኛ ነብይ ﷺ
ዝምታቸው ብዙ ሳቃቸው ትንሽ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ በህፃናት ጎን ሲያልፉ ሰላም ይሏቸው ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ለሰው ልጆች ለእንስሳት ሳይቀር ያዝኑ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ሰዎችን አክባሪና ተናናሽ ኩራት የሚባል ነገር አያውቁም ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ይቅር ባይና ይቅር ማለትን የሚወዱ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ የቅርቧ አለም ብልጭልጭ ይልቅ የመጨረሻውን አለም የሚናፍቁ
ዛሂድ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ጌታቸውን አመስጋኝ ሰዎችንም አመስጋኝ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ሷላትን የልቤ እርጋታ እያሉ ለጌታቸው ባጣምም ይሰግዱ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ በፈተናዎች እና በችግሮች ላይ ታጋሽ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ውሸትን በጣም ይጠሉ የነበሩ «ታመኙ-እውነተኛ» ነበሩ።

❤️የኛ ነብይﷺ ስድብንም ሆነ እርግማንን ይጠሉ ነበር።

የኔ ዉድ ነብይ ፤ ሩሔም፣ ገንዘቤም እናቴም፣ አባቴም ለአንቱ ፊዳ ይሁኑሎት..
ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም።

@yasin_nuru    @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
ቲክቶክ ላይ ዩትዩብ ላይ አንዳንድ ወንድሞች

አንድ ሰው የተሳሳተ መንገድ ላይ ሆኖ ስታዩት
እሱን ለማተካከል ከፈለጋችሁ አደብ ባለው መልኩ ለብቻው ምከሩት።

እኛ ወንጀላችን አጠገባችን ሰው የማያስቀርብ ሆኖ ሳለ ሌላ ሰውን ግን አጥረግርገን የምንሰድብበት፤ተውበት እንዲያረግ ሳይሆን በወንጀሉ እንዲገፋ በሚያረግ በቁጣ የምንናገራቸው እኛ ማን ሆነን ነው?

ስንመክር በአደብ ለብቻ ይሁን አልመለስም ካሉ እንግዲህ ምንም ማረግ አንችልም በማስገደድ አይሆንም። ነብዩ ሙሳ እንኳ ፊርዓውንን እንኳ እንዴት ነው አናግር የተባሉት እኔ ጌታ ነኝ ያለውን።

ስለዚህ እኛ ከሙሳ በልጠን ነው በአደባባይ ክብራቸውን ዝቅ እያደረግን የምንናገረው🤔 በግድ እንዲ ካልሆናቹ የምንለው? ከልባችሁ ዱዓ አድርጉላቸው

የባሳ ለመበላሸታቸው ሰበብ አትሁኑ ዱአ አድርጉላቸው በየኮሜንቱም እየገባችሁ መጥፎ ነገር የምትፅፉ አላህ እንዲመልሳቸው ዱዓ አድርጉላቸው። ይሄን ማድረግ #ካልቻላችሁ_ዝም_በሉ።

ቲክቶክ ላይ ከእስልምናችሁ ጋር የማይሄድ ነገር የምትሰሩ ይቅርባችሁ ሞት ቢመጣ ዋጋ ያስከፍላቹሃል። የእስልምና እምነት ተከታይ ስለሆናችሁ የእስልምና ወገኖቻችሁ የናንተን ቪድዮ ሲያዩ ይረበሻሉ እና እንተም የዚች አለም ነገር ሳያሳስባችሁ ወደ እስልምናችሁ ተመለሱ አላህ አያሳፍራችሁም የምትፈልጉትን ይሰጣቹሃል ተመለሱ ወደ አላህ።

አላህ ሁላችንንም ወደ እሱ ይመልሰን።

@yasin_nuru    @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
//ማነው ድሀ ጨዋ አይደለም ያለህ?//

♨አንድ ሀብታም ሰውዬ ወደ አንዲት ሊስትሮ ወደ ምትሳራ ብላቴና ሄደው ጫማ ማስጠረግ ጀመረ

🌻በመጀመሪያ ቀን በንቀት አይኑ እያየ አስጠርጎ ሄደ

🌻በሁለተኛ ቀንም ተመሳሳይ ፈት አሳይቶ ሄደ

🌻ሦስተኛ ቀን ልጅቷ ጫማውን እየጠረገች  በስህተት ትንሽ ቀለም ካልሲ ላይ አደረገች በዚህ የተናደደው ሰውዬ በጣም ተሳድቦ  ይቅርታ እያለችው ጥሏት ሄደ

ከትንሽ ደቂቃ ቡኋላ ተመልሶ መጣ ለካ ስልኩን ጥሎ ሂዶ ነበረ ከዛም ከትህትና ስልክ ጠፍቶብኝ ነው እዚህ ጥዬ ይሆን እንዴ ብሎ ይጠይቃል

ልጅቷ አዎ ስልኩ እዚህ አለ መጥቼ ልሰጥህ ፈልጌ ነበረ ግን የት እንደሄክ አላወኩም ትላለች

ሰውዬውም በልጅቷ ታማኝነት ተገርሞ ሀምሳ ብር ከኪሱ አውጥቶ ይሰጣታል

ልጅቷም እባክህ ጌታዬ አምስት ብር ጨምረህ ስጠኝ ትላለች

ሰውዬውም ያለ ምንም መቅመማት አውጥቶ ሰጣት

ልጅቷም ሀምሳ ብሩን መልሳ ሰጠች ምነው ላንቺ እኮ ነው ለታማኝነትሽ ብዬ ነው ይላታል

የታማኝነት ዋጋ ስንት ነው ትላለች

ሰውዬውም እኔ'ጃ ብሎ መለሰ

ልጅቷም አንተም ታማኝ ለመሆን ሞክር መርዳት ካለብህ ሰው መጀመሪያውኑ እርዳ አምስት ብሩ የሰራውት ብር ነው እኔ ታማኝነትን አልሸጥም ብላ ጥላው ሄደች

ሌላ ቀን መጥቶ ልጅቷን ቤት ብዙ ጫማዎች አሉኝ እቤት እንሂድ ብሏት ይዟት ሄደ

ከዛም እሷ ስራ እየሰራች እሱ ቤት ጥሏት ይሄደል። ቤት ውስጥ ጠረጴዛ ላይ ብዙ ብር አስቀምጦ እመጣለሁ ብሎ ይሄደል

ልጅቷም ብሩን ከጠረጼዛ አንስታ ጥሩ ቦታ ላይ አስቀመጠች

ሰውዬው ከሄደበት ቦታ መጥቶ ብሩን ጠረጴዛ ላይ ተመለከተ ብሩ እዛ አልነበረም ሰውዬውም ልጅቷን ጠርቶ እናንተ ድሆች መቼም ብር አይታችሁ ማለፍ አትችሉም አይደለም ባለፈው ታማኝ ነኝ ብለሽ ነበረ እኮ ብሎ ሰደባት

ልጅቷም አትሳሳት እኔ የድሀ ልጅ ድሀ ነኝ ድሀ የሆነ ሁሉ ሌባ ባለጌ አይደለም ሀብታም የሆነ ሁሉ ደግሞ ጨዋ አይደለም ስለዚህ ሰውን ሰው በመሆኑ ብቻ ቅረብ😡

አንድ ሰው መሆን የሚችለው ራሱን ብቻ ነው
አንድ ሰው ብዙ ሰው መሆን አይችልም
ስለዚህ በአንድ ሰው ስህተት  ብዙ ሰዎችን አትሳደብ ስለ ሁሉም ነገር አመሰግናለሁ።

ብሩን እዚህ መጥፎ ቦታ ላይ አይቼ እዛ ጥሩ ቦታ አስቀምጨልሀለው ብላ ጥለው ሊትሄድ ስትል ሰውዬው መጥቶ ተንበርክኮ ይቅርታ ጠየቀ

ከዛም አብራው እንድትኖር ተማፀነ

ሰውን በልብሱ ወይንም በአቋሙ አይታችሁ አትፍረዱ ልብና ልብስ የተላያዩ ነገሮች ናቸዉ
ልብ የፈጣሪ ስጦታ ሲሆን ልብስ በብር የሚገዛ እቃ ነው ስለዚህ የፈጣሪን ስጦታ በብር ከሚገዛው እቃ ጋር አታወደድሩ

ቅንነት  ለራስ  ነው
ቅንነት  መልሶ  ይከፍላል 

@yasin_nuru @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
ጀግንነትን ከታላቁ መሪ እንማር!

የበረሐው አንበሳ ኡመር ሙክታር ከጣልያኑ መርማሪ ጋር የነበራቸው ቆይታ…

መርማሪ፦የጣልያን ጠላት ሆነህ ተዋግተሀል?

ኡመር ፦አዎን

መርማሪ፦የሊብያን ህዝብ ጣልያንን እንዲዋጉ አሳምፀሀል?

ኡመር፦አዎን

መርማሪ፦የወንጀልህን ቅጣት ታውቀዋለህ?

ኡመር፦አዎን

መርማሪ፦የምትናገረውን ነገር ታምንልኛለህ?

ኡመር፦በሚገባ

መርማሪ፦ከመቼ ጀምረህ ነው ጣልያንን መዋጋት የጀመርከው?

ኡመር ፦ከ20 አመት ይሆነኛል!

መርማሪ፦በሰራሀው ነገር ተፀፅተሀል?!

ኡመር ፦በጭራሽ!

መርማሪ፦ስቅላት እንደሚጠብቅህ ታውቃለህን?!

ኡመር፦አዎን

የፍርድ ቤት ዳኛው፦መጨረሻህ በዚህ መልኩ ስለሆነ በጣም አዝናለሁ

ኡመር፦እንዲያውም ህይወቴን የምቋጭበት ምርጥ መንገድ ብዬ የማስበው በዚህ መንገድ ስጨርሰው ነው

ዳኛ፦ኡመርን በሂወት ለማጎጎት እየሞከረ…ለሙጃሂዶቹ ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ አድርግ እኛ በነፃ እንለቅሀልን…

ኡመር፦በጣም በግርምት ካዩት በኃላ…እንዲህ በማለት ታዎቂ ንግግራቸውን ተናገሩ " በሁሉም ሰላቶቼ ውስጥ ለ ላኢላሀኢለሏህ ሙሀመዱ ረሱሉላህ የምትመሰክር ጣቴ ባጢል ነገር አትፅፍም"

@yasin_nuru @yasin_nuru


ኡስታዝ ያሲን ኑሩ - "የቀልብ (የልብ) ድርቀትን የሚያጠፋ እና ልብን በኑር የሚሞሉ ዚክሮች

@yasin_nuru_hadis


Forward from: Yasin nuru's hadis
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አሁን በዚህ ዘመን🥺

@yasin_nuru_hadis


Forward from: Yasin nuru's hadis
የኑህን ዕድሜ፣

የሙሳን አዕምሮ፣

የኢብራሂምን ዕውቀት፣

የአዩብን ትዕግስት፣

የዩሱፍን ተቅዋ፣

የሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ትዕግስትና ፍቅር

አላህ ይወፍቀን🤲🏽🤲🏽


@yasin_nuru_hadis


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
🔰 ሙርተድ(ከእስልምና የወጣ ይገደላል??ለምን ይገደላል?🔰

አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ሰዎችንና ጂኖችን የፈጠረበት ዐላማ እሱን ብቻ እንዲያመልኩ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል👇
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
(📗ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

በእስልምና አንድ ሙስሊም ያልሆነ ግለሰብን አስገድዶ ወደ እስልምና ማስገባት የሚባል ነገር የለም።
አላህ እንዲህ ይላል👇

በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ "(📘ሱራ በቀራ፥ 2:256)

➤ ተገዶ እስልምና መቀበሉ ራሱ ትርጉም የለውም። ጥቅም የለውም። ምክንያቱም እስልምናን የተቀበለው በውጩ እንጂ ልቡ ላይ ሌላ እምነት ካለው ሙናፊቅ ይሆናል። በጣም ትልቅ ቅጣት ይጠብቀዋል።
አላህ እንዲህ ይላል👇.

إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا
*መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡
📚 አልኒሳእ 4፥145
➤ አላህ የሚፈልገው ጥርት ያለን አመልኮ እንጂ ሳይፈልጉ በግድ የሚፈፅሙትን አይደለም።
👇ማስረጃ
«وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ ۚ وَذَٰلِكَ دِينُ الْقَيِّمَةِ»
«አላህን፣ ኃይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፣ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)። ይህም የቀጥተኛዪቱ (ኃይማኖት) ድንጋጌ ነው።»
📚 [አል-በዪይናህ: 5]

ተገደው አላህን የሚያመልኩ ሰዎች አምልኳቸው ጥራት ስለሌለው ጥቅም የለውም። ስለዚህ በእስልምና ሌላን ሰው አስገድዶ ወደ እስልምና ማስገባት የሚባል ነገር የለም ጥቅምም የለውም።

➤ በእስልምና ሌላን ሰው ወደ እስልምና አስገድዶ ማስገባት እንደሌለ ካየን
ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች ያስገድዳል ብለው የሚያነሱትን ሀዲስ እንመልከትና መልስ እንስጥበት
ሀዲሱ👇👇👇👇
عنْ اِبْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اَللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: قَالَ رَسُولُ اَللَّهِ ‏- صلى الله عليه وسلم ‏-{ مَنْ بَدَّلَ دِينَهُ فَاقْتُلُوهُ }
ኢብኑ ዐባስ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል" ሀይማኖቱን የቀየረን ግደሉት"

➤➤ በመጀመሪያ ሰዎች  በአላህ የማምንና የመካድ ምረጫ ተሰጥቷቸዋል። ነፃ ፈቃድ ተሰጥተዋል።
አላህ እንዲህ ይላል👇
وقلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ ۚ إِنَّا أَعْتَدْنَا لِلظَّالِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمْ سُرَادِقُهَا ۚ وَإِن يَسْتَغِيثُوا يُغَاثُوا بِمَاءٍ كَالْمُهْلِ يَشْوِي الْوُجُوهَ ۚ بِئْسَ الشَّرَابُ وَسَاءَتْ مُرْتَفَقًا
ሱረቱ አል ከህፍ፥ - 29 ]
«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፡፡ (ከጥም) እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ! መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች!

☝️ አላህ እዚህ አንቀፅ ላይ ሰዎች የማመንና የመካድ ነፃ ፈቃድ እንዳላቸው ከጠቀሰ በኃላ እነዚያ የካዱ ሰዎች ቅጣት እንደሚያገኙ ይጠቅስልናል።
ይህ ማለት ሰዎች የማመንና የመካድ ምርጫ እንዳላቸውየመካድ መብት ግን እንደሌላቸው እንረዳለን። የመካድ መብት ቢኖራቸው በክህደታቸው ባልተቀጡ ነበር።
ይህንን ካየን ከእስልምና የወጣ ሰው ለምን ይገደላል። የመካድ ምርጫ ካለው ለምን ይገደላል ለሚለው መልሱ👇👇

➤➤1. በእስልምና حد ሐድ ( የወንጀል መቅጫ ህግ፣ውሳኔ) የሚባል ነገር አለ። ይህም አንድ ሙስሊም ለሚተገብራቸው ወንጀሎች የተቀመጠ ቅጣት ነው።
ለምሳሌ  "حد الزاني " አግብቶ ዝሙት የሰራ ቅጣት(መግደል)፣حد السرقة የስርቆት ህግ(እጁን መቁረጥ), حد القتل የግድያ ቅጣት(መገደል) ወዘተ  የሚባሉ ህግጋቶች አሉ። እነዚህን ወንጀሎች የተዳፈረ ከላይ የተጠቀሰውን ቅጣት ያገኛል ምክንያቱም ከላይ እንደተጠቀሰው ሰዎች የመካድ፣ወንጀል የመስራት ምርጫ እንጂ መብት ስለሌላቸው ይቀጣሉ ይጠየቃሉ።  ለምሳሌ አግብቶ ዝሙት የሰራ ሰው ዝሙት የሚባል ወንጀል ስለሰራ ይገደላል። ዝሙት መስራት መብቱ ነው አይባልም ልክንደዚሁ አንድ ሙስሊም ከከፈረ ከዝሙት የባሰ የተለቀ  ኩፍር(አምላክን መካድ) የሚባል ትልቅ ወንጀል ስለሰራ ይገደላል። አምላኩን መካድ መብቱ ነው አይባልም
ሰዎች በፈጠሯቸው በተለያዩ ሀገሮች ህግ ላይ ራሱ " ሀገሩን የካደ ሰው ይገደላል" የሚል ህግ አላቸው። ሀገርን መካድ መብቱ ነው እንደማይባለው ሁሉ አምላክን መካድም መብቱ አይደለም።

ሀገርን የካደ ሰው ከተገደለ ሀገርን የፈጠረ አምላክን ሲክድ ይገደል ቢባል ምኑ ነው ሚገርመው።
በአጭሩ ከእስልምና የወጣ ሰው የሚገደለው አምላኩን ስለካደ ክህደት ስለፈፀመ ይገደላል እንጂ አስገድደን እንዲሰልም አይደለም።

➤➤2. ሙርተድ የሚገደልበት ሁለተኛው ምክንያት ለሙስሊሞች ፊትና ስለሚሆን ነው። ከድሮ ጀምሮ "ከእስልምና ወጥቻለሁ፣መስሊም ነበርኩ ወዘተ እያሉ እስልምና ላይ እየቀጠፉ የእስልምና ስም እንደሚያጠፉት ለሙስሊሞች ፊትና ስለሚሆኑ ሙስሊሞችን ከንደዚህ አይነት ፈታኝ ከሆኑ ሰዎች ነፃ ለማድረግ(ሰዎች በነሱ ቅጥፈት እንዳይፈተኑ) ተብሎ ይገደላሉ።
አላህ እንዲህ ይላል
  ۚ وَالْفِتْنَةُ أَكْبَرُ مِنَ الْقَتْلِ ۗ وَلَا يَزَالُونَ يُقَاتِلُونَكُمْ حَتَّىٰ يَرُدُّوكُمْ عَن دِينِكُمْ إِنِ اسْتَطَاعُوا ۚ وَمَن يَرْتَدِدْ مِنكُمْ عَن دِينِهِ فَيَمُتْ وَهُوَ كَافِرٌ فَأُولَٰئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۖ وَأُولَٰئِك أَصْحابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدون
  ፈተናም (ማጋራት) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው፡፡ (ከሐዲዎች) ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስከሚመልሳችሁ ድረስ የሚዋጉዋችሁ ከመሆን አይቦዝኑም፡፡ ከእናንተ ውስጥም ከሃይማኖቱ የሚመለስና እርሱም ከሐዲ ሆኖ የሚሞት ሰው እነዚያ (በጎ) ሥራቸው በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም አገር ተበላሸች፡፡ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡»(📚አልበቀራህ 2:217)

ይቀጥላል......👇 ሙሉውን አንብቡት👇👇👇👇👇👇
https://t.me/iwnetlehullu1/376


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
ዝሙት አደጋዎቹ እና መጠበቂያ መንገዶች

① ዝሙት የአላህን ቁጣ ያስከትላል።


② ዝሙት እጅግ ሰቅጣጭ ዱንያዊ ቅጣት የተወሰነበት ወንጀል ነው። አላህ እንዲህ ይላል:–
﴿الزَّانِيَةُ وَالزَّانِي فَاجْلِدُوا كُلَّ وَاحِدٍ مِنْهُمَا مِائَةَ جَلْدَةٍ وَلا تَأْخُذْكُمْ بِهِمَا رَأْفَةٌ فِي دِينِ اللهِ إِنْ كُنْتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَلْيَشْهَدْ عَذَابَهُمَا طَائِفَةٌ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ﴾
"ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን (ያላገቡ ከሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፉዋቸው፤ በእነርሱም በአላህ ፍርድ ርህራሄ አትያዛችሁ፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆናችሁ (አትራሩ)፡፡ ቅጣታቸውንም ከምእምናን ጭፍሮች ይገኙበት፡፡" [አንኑር: 2]

የርህራሄ ተምሳሌት ከሆነችው ከእናትም በላይ አዛኝ የሆነው ጌታ ከባድ ቅጣት ከማስተላለፉም በላይ ቅጣቱን የሚፈፅሙት ርህራሄ እንዳይዛቸው ማሳሰቡ የወንጀሉን ከባድነት ነው አጉልቶ የሚያሳየን። በዚያ ላይ ቅጣቱ ለሌሎች መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ከፊል ህዝብ እንዲመለከተው እያስታወሰ ነው።
ይሄ መቶ ግርፋት እንግዲህ ዝሙተኛው አግብቶ የማያውቅ ከሆነ ነው። አግብቶ የሚያውቅ ከሆነ ግን በድንጋይ ተወግሮ ነው የሚገደለው።
እነዚህ ዱንያዊ ቅጣቶች ናቸው። ጥፋቱን ፈፅሞ ሳይቶብት የሞተ ሰው የሚኖረው አኺራዊ ቅጣቱ ደግሞ የከፋ ነው የሚሆነው።

③ ዝሙት በቀብር (የበርዘኽ ህይወት) አስፈሪ ቅጣት ያለበት ጥፋት ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
«رأيتُ الليلةَ رجلين أتياني فأخرَجاني، فانطلقتُ معهما فإذا أنا ببناءٍ على مثلِ التنُّورِ، أعلاه ضيِّقٌ وأسفله واسعٌ، يوقد تحتَه نارٌ، فيه رجالٌ ونساءٌ عراةٌ، فإذا أُوقدت النارُ ارتفعوا حتى يكادوا يخرجون، وإذا خمَدَت رجعوا، فقلتُ للرَّجُلينِ: من هؤلاء؟ قالا: هم الزناةُ»
"ዛሬ ሌሊት ሁለት ሰዎች ወደኔ መጥተው አየሁኝ። ይዘውኝ ወጡ። ከነሱ ጋር ተጓዝኩ። እንደ ምድጃ ባለ ግንብ ዘንድ ደረስኩ። ላዩ ጠባብ ታቹ ሰፊ ነው። ከስሩ እሳት ይቀጣጠላል። በውስጡ እርቃን የሆኑ ወንዶችና ሴቶች አሉ። እሳቱ ሲቀጣጠል ሊወጡ እስከሚቀርቡ ወደላይ ይወጣሉ። ሲከስም ይመለሳሉ። ‘እነማን ናቸው እነዚህ?’ ብየ ሁለቱን ሰዎች ስጠይቅ ‘ዝመተኞች ናቸው’ ይላሉ።" [ቡኻሪ: 7047]

④ ዝሙት በአኺራ ድርብርብ ቅጣት ከተዛተባቸው ሺርክና ሰው መግደል ጋር አብሮ የተጠቀሰ የወንጀል አይነቶች ነው። አላህ እንዲህ ይላል:–
(وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا * يُضَاعَفْ لَهُ الْعَذَابُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَيَخْلُدْ فِيهِ مُهَانًا)
"እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡ በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል፡፡ በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ኾኖ ይኖራል፡፡" [አልፉርቃን: 68–69]
ኢማሙ አሕመድ "ከግድያ ቀጥሎ ከዝሙት የከፋ ወንጀል አላውቅም" ይላሉ።

⑤ ዝሙት ከባድ ማስጠንቀቂያ የመጣበት የባለጌዎች መንገድ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:–
﴿وَلا تَقْرَبُوا الزِّنَى إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلاً﴾
"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ ብልግና ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!" [ኢስራእ: 32]

⑥ ዝሙት ኢማንን የሚያራቁት አደገኛ ወንጀል ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
«لا يزني الزاني حين يزني وهو مؤمنٌ»
"ዝሙት በሚፈፅመው ጊዜ ሙእሚን ሆኖ አይፈፅመውም።" [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይሄ እጅግ እጅግ አስፈሪ ሐዲሥ ነው።

⑦ በዱንያም የአላህን ቁጣና ቅጣት ያስከትላል። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
إذا ظهر الزنا و الربا في قرية فقد أحلوا بأنفسهم عذاب الله
"ዝሙትና ወለድ በአንዲት መንደር ላይ ከተንሰራፋ በራሳቸው ላይ የአላህን ቅጣት አስወስነዋል።"

⑧ ዝሙት ሲበዛ በሐዲሥ እንደተገለፀው ቀድሞ የማይታወቅ በሽታና ወረርሺኝ ይመጣል። ለምሳሌ ኤድስን አስታውሱ።
…………

…ከዝሙት መራቂያ መንገዶች…

① በመጀመሪያ አንተ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ ድረስ። ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም።

② እይታን መገደብ። "አይኖች ይዘሙታሉ። ዝሙታቸው ያልተፈቀደ እይታ ነው" ተብሏል በሐዲሥ።

③ ከአጅነቢ ጋር ከመቀላቀል፣ ከአጅነቢ ጋር ተገልሎ ከመቀመጥ መራቅ። አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ለብቻ መሆኑ ብልግና የመፈፀሙን እድል በጣም ከፍ ያደርገዋል።
"አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር አይገለል። ይህ ሲሆን ሶስተኛቸው ሸይጧን ነውና" ተብሏል በሐዲሥ። ሰው በሌለበት የባልሽ ወንድም እንዲገባ አታድርጊ። "ዋርሳ (የባል ወንድም) ሞት ነው" ብለዋል ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለመወ።

④ ከመጥፎ ጓደኞች መራቅ
"እግሮች ይዘሙታሉ። ዝሙታቸው (ወዳልባሌ ቦታ) መሄድ ነው" ተብሏል በሐዲሥ።

⑤ አጅነቢ ከመጨበጥ መቆጠብ
"እጆች ይዘሙታሉ። ዝሙታቸው መንካት/ መጨበጥ ነው" ተብሏል በሐዲሥ።

⑥ ምላሳችንን ዝሙትን ከሚያስታወሱ ነገሮች ማራቅ። በሐዲሥ "ምላስም ይዘሙታል" እንደተባለ እናስታውስ።

⑦ እንደ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ልቦለድ፣ እርቃን ምስሎችና የብልግና ቪዲዮዎች በከባዱ ወደ ዝሙት የሚጣሩና የዝሙት ፍላጎትን የሚቀሰቅሱ ስራዎች ናቸው። አብዛኞቹ ዘፈኖች ስለ አጅነቢ ገላ፣ ከአጅነቢ ጋር ስለመጫወትና መዋል ነው የሚያወሩት። ዘፈን የዝሙት መሰላል፣ የንፍቅና መብቀያ ነው። አብዛኞቹ ፊልሞች የዝሙት ሙቀዲማዎች ይገኙባቸዋል።

⑧ አኺራን ማሰብ፣ ነገ ከአላህ ፊት መቆምና ከባድ ምርመራ እንዳለ ማሰብ። አላህ እንዲህ ይላል:–
(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ)
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡" [አንኑር: 24].

⑨ እራስን በሐላል ማብቃቃት (ማግባት)። ለቻለ ሰው እንደ ትዳር ከዝሙት መጥጠበቂያ ሰበብ የለም።

(10) ማግባት ያልሆነለት ደግሞ እስከዚያ ፆም ማብዛት። አመጋገብን ማስተካከል። እራስን ከቦዘኔነት አርቆ በስራ መጥመድ።

(11) ስለዝሙት አደገኝነት፣ ከዝሙት መራቅ አላህ ዘንድ ስላለው ደረጃ ማንበብ፣ ማድመጥ፣ ማስታወስ።

@yasin_nuru @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
ተዉሂድ / ላኢላሃ ኢለላህ ማለት

* አላህን ብቻ መገዛት

* እሱን እንጂ አለመፍራት

* አምልኮ ለሱ ብቻ ማድረግ

* ከሱ ብቻ እንጂ አለመከጀል

* ወደሱ ብቻ እንጂ የድረስልን ጥሪ አለማሰማት

* በሱ እንጂ አለመመካት

* ለሱ ብቻ እንጅ ያለ መስገድ ያለ ማጎብደድ

* በስሙ ብቻ እንጂ ያለማረድ ያለመሰዋት

* በስሙ እንጂ ያለመማል

* ሥራን ለሱ ብቻ ጥርት አድርጎ መሥራት

* ከሱ አስበልጦ ሌላን አካል አለመውደድ

* ወደሱ ብቻ ተውባ ማድረግ

* ለሱ ብቻ እንጂ ስለት አለማድረግ

* በደነገገው ሕግ መዳኘት

* ባወረደው ቁርአን መሥራት

* በላከው መልዕክተኛ ማመን

#ይሄንን_የማያቁ_ብዙ_ወዳጆች_አሉን_እና_እናጋራቸው።

@yasin_nuru @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
😄 ሰኞን በፈገግታ 😄

ባል እና ሚስት ተጣልተው ለፍቺ ፍርድ ቤት ይቆማሉ

ዳኛው፦ 3 ልጆች አሏችሁ እንዴት ነው የምትካፈሉት? አላቸው

ባል እና ሚስት ለብዙ ግዜ ከተማከሩ በዃላ፤

'የተከበረው ፍርድ ቤት ፤ አንድ ልጅ ጨምረን ቀጣይ አመት ለመመለስ ተስማምተናል።'
*
*
*
*
*
*
የሚገርመው ከ 9ወር በዃላ መንታ ተገላግላ አረፈችው።😆😆

መቼ ይፋቱ ይሆን።፨፨፨፨

@yasin_nuru    @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
ተዉሂድ / ላኢላሃ ኢለላህ ማለት

* አላህን ብቻ መገዛት

* እሱን እንጂ አለመፍራት

* አምልኮ ለሱ ብቻ ማድረግ

* ከሱ ብቻ እንጂ አለመከጀል

* ወደሱ ብቻ እንጂ የድረስልን ጥሪ አለማሰማት

* በሱ እንጂ አለመመካት

* ለሱ ብቻ እንጅ ያለ መስገድ ያለ ማጎብደድ

* በስሙ ብቻ እንጂ ያለማረድ ያለመሰዋት

* በስሙ እንጂ ያለመማል

* ሥራን ለሱ ብቻ ጥርት አድርጎ መሥራት

* ከሱ አስበልጦ ሌላን አካል አለመውደድ

* ወደሱ ብቻ ተውባ ማድረግ

* ለሱ ብቻ እንጂ ስለት አለማድረግ

* በደነገገው ሕግ መዳኘት

* ባወረደው ቁርአን መሥራት

* በላከው መልዕክተኛ ማመን

#ይሄንን_የማያቁ_ብዙ_ወዳጆች_አሉን_እና_እናጋራቸው።

@yasin_nuru @yasin_nuru


Forward from: ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
ተዉሂድ / ላኢላሃ ኢለላህ ማለት

* አላህን ብቻ መገዛት

* እሱን እንጂ አለመፍራት

* አምልኮ ለሱ ብቻ ማድረግ

* ከሱ ብቻ እንጂ አለመከጀል

* ወደሱ ብቻ እንጂ የድረስልን ጥሪ አለማሰማት

* በሱ እንጂ አለመመካት

* ለሱ ብቻ እንጅ ያለ መስገድ ያለ ማጎብደድ

* በስሙ ብቻ እንጂ ያለማረድ ያለመሰዋት

* በስሙ እንጂ ያለመማል

* ሥራን ለሱ ብቻ ጥርት አድርጎ መሥራት

* ከሱ አስበልጦ ሌላን አካል አለመውደድ

* ወደሱ ብቻ ተውባ ማድረግ

* ለሱ ብቻ እንጂ ስለት አለማድረግ

* በደነገገው ሕግ መዳኘት

* ባወረደው ቁርአን መሥራት

* በላከው መልዕክተኛ ማመን

#ይሄንን_የማያቁ_ብዙ_ወዳጆች_አሉን_እና_እናጋራቸው።

@yasin_nuru @yasin_nuru


Forward from: Alain Amharic
በስልካችን ላይ ሊኖሩ የማይገቡ አደገኛ መተግበሪያዎች የትኞቹ ናቸው?

በውስጣቸው አጥፊ ቫይረሶችን የያዙ ነገር ግን አገልግሎት የሚሰጡ በመመስል የተሰሩ መተግበሪያዎች አሉ የሚለን ፎን አሬና ድረ ገጽ፤ እንዚህን መተግበሪያዎች (አፕሊክሽኖች) ውለን ሳናድር ዛሬውኑ ከስልካችን ላይ እናጥፋቸው ሲልም ምክር አክሏል።

የካሜራዎች፣ የኪቦርዶች፣ የጂ.ፒ.ኤሶች፣ የፎቶ ማስተካከያ እና ሌሎች መሰል መተግበሪያዎች በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል።

የመተግበሪዎቹን መጠሪያ በተከታዩ ሊንክ ያገኛሉ፤ https://bit.ly/3xJtPyU



20 last posts shown.