Ibn Munewor
ከአመታት በፊት በአሕባሽ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በተቀጣጠለበት ወቅት ነው። የሆነ ታዋቂ ሸይኽ አሕባሾችን አጥብቆ ሲኮንን ሰማሁትና
"ግን ለምንድን ነው አሕባሽን የምትቃወሙት?" አልኩት።
"እንዴ ሙሐመድ አሕባሽኮ የጀህምያና የሙርጂ ዐቂዳ አለባቸው። በዚያ ላይ ዑለማዎችን ያከፍራሉ፣ ሶሐባ ይሳደባሉ…" አለኝ።
"እና ለዚህ ነው የምትቃወሟቸው?" አልኩት።
"አዎ!" አለኝ ጫን አርጎ።
"አይመስለኝም" አልኩት።
"እንዴት እንደዚያ ትላለህ?" አለ በግርምት።
"ተመሳሳይ ጥፋት ያለበት ሌላ ሰው ቢኖር ታወግዛላችሁ?" አልኩት።
"አዎ! ጥፋቱ ካለ ከሰውየው ምን አለን?" አለኝ።
"ጥሩ! እንግዲያው ቅድም የተዘረዘሩት የአሕባሽ ጥፋቶች ሰይድ ቁጥብ ላይ ይገኛሉ። ከሱ ታስጠነቅቃላችሁ?" አልኩት።
"አይ" አለና ይቺን አንቀፅ አነበበልኝ:
(تِلْكَ أُمَّةٌ قَدْ خَلَتْ ۖ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَلَكُمْ مَا كَسَبْتُمْ ۖ وَلَا تُسْأَلُونَ عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ)
"ይህች በእርግጥ ያለፈች ሕዝብ ናት፡፡ ለርሷ የሠራችው አላት፡፡ ለናንተም የሠራችሁት አላችሁ፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት አትጠየቁም፡፡"
"እንዴ! ዐብደላህ አልሀረሪስ በህይወት አለንዴ? ታዲያ ለምን ዝም አንልም?" አልኩት።
"አይ ሰይድ ቁጥብ ብዙ ለኡማው ያበረከተው ነገር አለ" አለኝ።
"ዐብደላህ አልሀረሪንም ተከታዮቹ እንደዚያ ይሉታል" አልኩት።
ከዚህ በሁዋላ ውይይቱን አልቀጠለም። "እስኪ ሌላ ጊዜ እናወራለን" ብሎኝ ተነስቶ ሄደ። ከዚያ በሁዋላ ተገናኝተን አናውቅም። በየሄደበት "መድኸልዮች" እያለ እንደሚያጠለሽ እሰማለሁ። ዛሬ ደግሞ ነፋሱን ተከትሎ አሕባሽን ከመቃወም እንደሚታቀብ እገምታለሁ። ከኖርን እናያለን፣ ኢንሻአላህ። የዥዋዥዌ ጀማዐ አባላት አብይ ባህሪ!!
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 08/2010)
🌐
t.me/AbumuslimAlarsi