የአረብያው ባህረሰላጤ በ1930ዎቹ ገደማ ከበረሀው በታች ለዘመናት ቢቀዱት የማያልቅ የነዳጅ ክምችት እንዳቆረ ከመታወቁ በፊት አካባቢው ለምንም ነገር የማይጋብዝ ከባድ ሀሩር ነበር
በተለይም ደግሞ በቅድመ ኢስላም ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሮም እና ፋርስን የመሰሉ ግዙፍ ኢምፓየሮች ልክ በሌሎች ግዛቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ በመካ ዙሪያ ያለውን ህዝብ ለማስገበር እምብዛም ጦር አልሰበቁም።
የረባ አልነበረምና ነው፥ እንዲያውም ጦር ለማዘጋጀትና በረሀው ላይ ቋሚ ሰራዊት ለማኖር የሚወጣው ወጪ በኢምፓየሩ ላይ ከባድ የኢኮኖሚ ጠባሳ በጣለ ነበር።
በመሆኑም የአረብያ ህዝብ በራሱ በሆነ ብልሀትና ጥንካሬ ሳይሆን ተፈጥሮ በቸረችው ለኑሮ የማይመች በረሀ ምክንያት ከቀኝ ወራሪዎች ተጽእኖ ለዘመናት ተጠብቆ ኖሯል። ለንግድ ልውውጥም ቢሆን ያን ያህል አጓጊ መድረክ ስላልነበረ በበረሀው ወበቅ ለመጠበስ ፍቃደኛ ሆኖ የሚመላለስ ነጋዴ አልነበረም። በሌሎች ክፍላተ አለማት ከሚስተዋለው የገበያና የገበያተኛ ቅይጥ አንጻርም የአረብያው በረሀ አንድ አይነት ህዝብ ብቻ የተከማቸበት ድፍን ከባቢ ነበር። ይህ ህዝብ በሌሎች ተጽእኖ ለመጠቃት የማይመች፥ በራሱ ለማጥቃት ደግሞ ጉልበት የሌለው፥ የተነጠለ ህዝብ ነው።
@alqalamarabic