ጋብቻን ማፍረስ …
☄️ بسم الله الرحمن الرحيم
እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።
📘 السؤال السادس عشر:
(المجموعة الثالثة)
ما الفرق بين الطلاق الرجعي والطلاق البائن؟ وهل في الطلاق البائن عدة، وهل فيه مراجعة؟
ጥያቄ ፦
" አጠላቁ አል– ረጂዒ " (የመመለስ ፍቺና) " አጠላቁ አል–ባኢን " (ሙሉ በሙሉ ግንኙነት እንዳይኖራቸው በሚያደርገው ፍቺ) መሀል ያለው ልዩነት ምንድነው ?
አጠላቁ አል–ባኢን "ዒዳ" (መቁጠርና) መመለስስ አለውን ?
📘 الجواب:
الطلاق الرجعي هو: أن يطلق الزوج زوجته التي قد دخل بها طلقة واحدة أو طلقتين ولا تزال في العدة، فإذا طلق زوجته التي قد دخل بها، طلقة واحدة أو طلقتين، وهي لا تزال في العدة، فهو طلاق رجعي.
መልስ ፦
" አጠላቁ አል–ረጂዒ " (የመመለስ ፍቺ) ማለት ፦
ወንድዬው (ባል) ያገባት በሆነችው ባለቤቱ ላይ ከገባ (አብሮ መኖር ከጀመረና) ከዚያም አንድ ወይም ሁለት
ጊዜ የፈታት እንደሆነ በርሷ ላይ "ዒዳን"
የምትቆጥር ከመሆን ቅሮት የለውም።
ይህም " አጠላቁ አል–ረጂዒ"
(የመመለስ ፍቺ) ይባላል።
والطلاق البائن نوعان: منه ما هو بائن بينونة صغرى، ومنه ما هو بائن بينونة كبرى.
" አጠላቁ አል–ባኢን " (ሙሉ በሙሉ ግንኙነት እንዳይኖራቸው የሚያደርገው ፍቺ) ሁለት ዓይነት ነው።
1ኛው· " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ "በይኑነተ ሱግራ" የሚባለው ሲሆን
2ኛው· " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ "በይኑነተ ኩብራ" የሚባለው ነው።
فالبينونة الصغرى: أن يطلق زوجته التي دخل بها طلقة واحدة، أو طلقتين، ويتركها فلا يراجعها حتى تنتهي عدتها، فهذا طلاق بائن ولكن بينونة صغرى، فله أن يُعيدها بعد ذلك إذا أحب بنكاح جديد.
ومثله أن يطلق زوجته التي لم يدخل بها، طلقة واحدة، فإذا طلق زوجته التي عقد عليها ولم يدخل بها طلقة واحدة فإنها تصير بائنا بينونة صغرى، يستطيع ردها بنكاح جديد.
👉 "በይኑነተ ሱግራ" (የሚባለው ፍቺ) ፦
1· አንድ ወንድ ያገባትን ባለቤቱን
(አብሯት ገብቶ እየኖረ …) አንዴ ወይም ሁለቴ ይፈታትና "ዒዳዋን" ቆጥራ እስክትጨርስ ድረስ ሳይመልሳት ይተዋታል።
ይህ ዓይነቱ ፍቺ " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ ነገር ግን "በይኑነተ ሱግራ" የሚባለው ነው። ለርሱ (ለባልዬው) ከዚህ በኋላ ሊመልሳት የወደደ (የፈለገ) እንደሆነ እንደ አዲስ "ኒካሕ" በማድረግ
(መመለስ ይችላል።)
2· (ሌላው) ተመሳሳይ የሆነው ፍቺ ፦
አንድ ወንድ (ያገባትን) "ኒካሕ" ያሰረላትን ባለቤቱን (አብሯት ገብቶ መኖር ሳይጀምር) አንድ ጊዜ ከፈታት
(እቺ ሴት) "ባሂን" ትሆናለች።
ይህም ማለት "በይኑነተ ሱግራ"
ማለት ነው።
(ከፈለገ) አዲስ "ኒካሕ" በማድረግ
(መመለስ ይችላል።)
وأما الطلاق البائن بينونة كبرى: فهو أن يطلق زوجته التي دخل بها ثلاث تطليقات في مجالس متفرقة وكل طلقة منها في طهر، فهذا طلاق بائن بينونة كبرى ولا تحل له بعد ذلك حتى تنكح زوجا غيره.
👉 " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ "በይኑነተ ኩብራ" የሚባለው ከሆነ …
እርሱ (ባልዬው) ያቺ ያገባት በሆነችው ባለቤቱ ላይ ገብቶ አብሮ እየኖረ …
በተለያየ ጊዜ ሦስት ፍቺን ከፈታትና
ሁሉንም ፍቺ ሲፈታት ደግሞ "ጣሂር"
(ከወር አበባ ደም) ንፁህ ከነበረች ይህ
ዓይነቱ ፍቺ " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ "በይኑነተ ኩብራ" የሚባለው ነው።
ከዚህ በኋላ ሌላ ባል አግብታ (እስከምትፈታ) ድረስ ለርሱ የተፈቀደች አትሆንም።
وقول السائل: هل في الطلاق البائن عدة؟
الجواب: نعم فيه عدة، البينونة الصغرى، والبينونة الكبرى، كلها فيها عدة، إلا التي طلقها قبل الدخول بها فليس عليها عدة، أول ما يطلقها تصير بائنا وليس عليها عدة، لقول الله تعالى: { يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نَكَحْتُمُ الْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِن قَبْلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ فَمَا لَكُمْ عَلَيْهِنَّ مِنْ عِدَّةٍ تَعْتَدُّونَهَا ۖ فَمَتِّعُوهُنَّ وَسَرِّحُوهُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا }.
አጠላቁ አል–ባኢን (በሚለው ፍቺ) ውስጥ "ዒዳ" መቁጠር አለን ?
ለሚለው ጥያቄው ፦
መልሱ ፦ አዎ ! ዒዳ አለው።
"በይኑነተ ኩብራ" እና "በይኑነተ ሱግራ"
ሁሉም ዒዳ አለው።
ባልዬው ካገባት በኋላ (አብሯት ለመኖር)
ሳይገባ በፊት የፈታት እንደሆነ በርሷ ላይ "ዒዳ" የለባትም ፤ (የሚለው ሲቀር …)
መጀመሪያውንም የፈታት እንደሆነ "ባሂን" ትሆናለች። በርሷ ላይ "ዒዳ" የለባትም።
ከፍ ላለው ለአላህ ንግግር ሲባል ፦
(( " እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ምእምናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኩዋቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም፡፡ አጣቅሟቸውም ፤ (ጉርሻ ስጧቸው)፡፡ መልካም ማሰናበትንም
አሰናብቷቸው፡፡ " ))
【አል–አሕዛብ(49)】
وقول السائل: هل فيه المراجعة؟ الجواب: تكون المراجعة على ما سبق بيانه، والله أعلم.
አጠላቁ አል–ባኢን (በሚለው ፍቺ) ውስጥ መመለስ አለን ? ለሚለው ጥያቄው ፦
መልሱ ፦ መመለስ የሚለው ነገር ማብራሪያው እንዳስቀደምነው ነው።
የበለጠውን ዐዋቂ አላህ ነው !!!
*═════ ❁✿❁ ══ ❁✿❁ ═*
ታላቁ ሸይኽ አቢ አብዱረሕማን
ረሻድ ቢን አሕመድ አል–ዳለዒ
https://t.me/amr_nahy1… ኢስማኤል ወርቁ …
موقع الشيـخ حفظـه الله :
https://www.sh-rashad.com/ *للاشتراك في قناتنا على التيلجرام اضغط على هذا الرابط 👇🏾👇🏾*
https://t.me/rshad11