Forward from: ابدلكريم حسن
👉 ሰለፍይነት በድምፅ ብልጫ አይደለም ።
የሰለፍያ ዐቂዳና ሚንሀጅ በዋነኝነት በወላእና በራእ ( ሙወሒዶችን በመወዳጀት ፣ በመተባበር ፣ በማክበር ከጎናቸው በመሆን, የቢዳዓ ባልተቤቶችን በመጥላት ፣ በመራቅ ፣ በማሳነስ ፣ በማዋረድ ፣ ከእነረሱ በማስጠንቀቅና ለባጢላቸው ምላሽ በመስጠት) ላይ የተመሰረተ ነው ። ይህ ነው የሰለፍይነት መለኪያ ። አንድ ሰው ሰለፍይ መሆኑና አለመሆኑ የሚታወቀው ለሙብተዲዖች ባለው ጥላቻና ከእነርሱ በመራቁ ነው ። እገሌ ሙብተዲዕ ነው የሚባለው ይህን አስል ጥሶ ወይም ከሙብተዲዕ ጋር ተወዳጅቶ አብሮ ሲቀማመጥ ፣ አብሮ ሲበላ ፣ የዲን ስራ አብሮ ሲሰራ ፣ እሱን ሲያወድስ ፣ በነርሱ ላይ ረድ ሲደረግ የሚከፋውና የሚበሳጭ ከሆነና እነዚህ አካላት ሙብተዲዕ መሆናቸው በመረጃ ተነግሮት አልመለስም ሲል ነው ። የዚህ አይነቱ ሰው ወደደም ጠላም ሙብተዲዕ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰለፍይ ነው ብለው ቢጮሁም ። ሌት ከቀን ቢፅፉም ። ለሙብተዲዕ ዲፋዕ የሚያደርግ ፣ ሙብተዲዕን የሚያወድስ ፣ ወደ ሙብተዲዕ ሰዎችን የሚጣራ ሰለፍይ የሚሆነው በሙብተዲዕ አእምሮ ውስጥ እንጂ በሰለፍያ ሚዛን አይደለም ። እንዲህ አይነቱን ሰው ሰለፍይ ነው ለማሰኘት ድምፅ ማሰባሰብና ተከታይ ማብዛት ከዛው ጎራ እንዲመደብ የሚያደርግ እንጂ ሌላ ውጤት አያመጣም ።
ሰለፍይነት ማንም ሰው የወደደውን የሚያስገባበት የጠላውን የሚያስወጣበት ጎጆ ቤት አይደለም ። የራሱ ሚዛን ያለው መመለሻው ወደ ቁርኣንና ሐዲስ ሆኖ በሰለፎች ግንዛቤ ተግባራዊ የሚደረግ መርህ ቢሆን እንጂ ።
በሀገራችን የዳዕዋ ታሪክ ይህን መሰረት ሲያስተምሩ የነበሩ አካላት በተለያየ ጊዜ በተለያየ ምክንያት ያስተማሩትን የሰለፍያ መርህ ጥሰው ወደ ቢዳዓ አንጃዎች እየገቡ ወጣቱን ለማደናገር ሰለፍዮች ናቸው የሚል ድምፅ ሲያሰባስቡ ይታያል ።
🔹 ከእነዚህ አካላት አንዱ የሆኑት የኢብኑ መስዑድ ሰዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች በሰለፍያ መርህ ላይ በነበሩበት ጊዜ በኢኽዋኖችና ሱፍዮች መካከል የተደረገውን ስምምነት የሰለፍያን መርህ የናደ የቀደምቶችን መሰዋእትነት ዋጋ ያሳጣ ስምምነት ነው ትክክለኛን እስልምና አይወክልም ብለው ረድ አድርገው ህዝበ ሙስሊሙን ከኢኽዋን መሪ የሆኑት ከዶክተር ጀይላንና ሙሐመድ ሓሚዲንና ከመሳሰሉት አስጠንቅቀው ሰለፍዮች አለመሆናቸውን በአደባባይ አውጀው ነበር ። ይህ የኢብኑ መስዑዶች አቋም እንቅልፍ የነሳቸው የኢኽዋን መሪዎች በዋና ዋና የኢብኑ መስዑድ ሰዎች ላይ ስራ መስራት ጀመሩ ። ያለመሰልቸት በሚገርም ትእግስት እቅዳቸውን ለማሳካት የሰሩት ኢኽዋኖች ያለሙት እውን ሆኖ የመርከዙን ሀላፊዎች በመረባቸው ጠልፈው በተራቸው የመርከዙ ሰዎች በአደባባይ ከሱፍዮችና ከኢኽዋኖች ጋር አንድ ነን አሉ ። አንድነታቸውንም አብረው በመብላትና በመጠጣት ለህዝበ ሙስሊሙ አሳዩ ። በመቀጠልም በሂደት መርከዙ ወደ ጎራቸው እንዲደባለቅ አደረጉ ከዚያም ከመጅሊሱ የስልጣን ፍርፋሪ ለቅምሻ ያክል ጣል አድርገውላቸው ከስራቸው ሆነው ጭራቸውን እንዲያስለመልሙ አደረጉዋቸው ። ‼
🔹 ሁለተኛው አካል የዚህን የመርከዙ ሰዎች ሚንሀጅ ቀይሮ ከኢኽዋን ጋር መስራት በዋነኝነት ሲዋጉና ሲያስጠነቅቁ የነበሩት እነኢብኑ ሙነወር ናቸው ። የነኢብኑ ሙነወር የረድ ብትር መቋም የከበዳቸው የመርከዙ ሰዎች ከአለቆቻቸው ከነዶክተር ጀይላን በተሰጣቸው የቤት ስራ መሰረት ቀን ከለሊት በእነርሱ ላይ መስራት ጀመሩ በማይታመንና ግራ በሚያጋባ መልኩ እንዲህ አይነት ከሙታን መንፈስ አምላኪዎች አንድ ከምንሆን ቀባሪ አጥተን ጀናዛችን አሞራ ይብላው ብለው የመርከዙ ሰዎችን የአንድነት ጥሪ ሲያወግዙና ኢኽዋን በዘፈነ ቁጥር ካላጨበጨብኩኝ ማለት ምንድነው ደመረኩሙላህ ሲሉ የነበሩት እነኢብኑ ሙነወር አቋም ቀይረው የመርከዙ ሰዎች ሰለፍዮች ናቸው ብለው ድምፅ መስጠት ጀመሩ ። በዚህ አላቆሙም ድንበር ታልፎባቸዋል በእነርሱ ላይ ብይን የሰጡ ዑለሞች ብይናቸው ተቀባይነት የለውም ችኩል ናቸው የሚሉትን አያውቁም ሽበታቸው የእንጨት ሽበት ነው ውሸታሞች ዘግይተው የመጡ ሀዳድዮች ናቸውና የመሳሰሉ ዘለፋና ብይን መስጠት ጀመሩ ።‼ እነዚህ አካላት ሰለፍይነት በድምፅ ብልጫና በተከታይ ብዛት የሚለካ ይመስል የወጣቱን አእምሮ ከመመዘኛው አውጥተው የተለያየ ቀመርና አመክንዮ በመደርደር ሰለፍዮች ናቸው ብሎ ከባድ መሀላ እንዲምል ማድረጉን ተያይዘውታል ። ይሁን እንጂ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባው አሁንም ሰለፍይነት በድምፅ ብልጫ አለመሆኑን ነው ።
አላህ ሐቅን አውቀን የምንከተለውና ባጢልን አውቀን የምንርቀው ያድረገን ።
https://t.me/bahruteka