Forward from: Tsegaye Ararssa
የወላይታ ሕዝብ የትግል መሪዎች መታሰርን አስመልክቶ ወብን ያወጣው አስቸኳይ መግለጫ
KMN:- Aug. 09/2020
================
መንግሥት ሠላማዊና ሕጋዊ የሆነውን የሕዝብ ጥያቄ ወደ ሁከት ለመቀየር የሚደርገው እንቅስቃሴ እንዲያቆም አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
ዛሬ ቀን ነሐሴ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የወላይታ ዞን አመራሮችና ከተላያየ አደረጃጀት የተወጣጡ የወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምሥረታ አስተባባሪ ካውንስል አማካሪ ቦርድ አባላት በወላይታ ጉታራ ስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት ድንገት በመጣው የመከላከያ ኃይል ታፍነው ታስረዋል፡፡ የወላይታ ዞን ኮር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተወካዮች፣ የድርጅታችን የዎብን አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ የወህዴግ ም/ሊቀመንበር፣ የተለያዩ አክትቪስቶች እና ሌሎች ክልል ምሥረታ አስተባባሪ ካውንስል አባላት ታፍነው ታስርዋል፡፡
የፌዴራልና የደቡብ ክልል መንግሥታት የወላይታ ሕዝብ ሠላማዊ ጥያቄ ወደ ሁከት ለመቀየር የሚደረገው ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲያቆም አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ የወላይታ ዞን አመራሮችንና የወላይታ ክልል ምሥረታ ካውንስል አማካሪ ቦርድ አባላትን፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችንና በአጠቃላይ የሕዝቡ የትግል መሪችን በማሠር የሚቆም ትግል የለም፡፡ ፍትሐዊ፣ ሕገ-መንግሥታዊና ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም የወላይታ ሕዝብ ለሚጠይቀው ጥያቄ በሠላም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አመራሮችንና ታጋዮችን የማሠር እርምጃ ፈፅሞ ሕገ-ወጥና የመብት ጥሰት ተግባር ነው፡፡
በመመሆኑም የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ ምላሽ እስኪሰጠው እና በሕገ-ወጥ መንገድ በሠላም ስብሰባ እያካሔዱ ሳሉ በወታደራዊ ከበባ የታሠሩ የወላይታ ሕዝብ የትግል መሪዎች እስኪፈቱ ድረስ ሁላችንም በአንድነት እስረኞች ነን፡፡ የታሠሩ ሰዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱና የወላይታ ሕዝብ በክልል የመደራጀት ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄ በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ
ነሐሴ 3 ቀን 2012 ዐ.ም
ዎላይታ ሶዶ