#በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ45,000 በልጧል። በአንድ ቀን ብቻ ከ2,700 በላይ ሰው ሞቷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ824,000 በልጧል።
#በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 759 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተድርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 18,100 ደርሷል።
#በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 1,194 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 94 ሰዎች ሞተዋል።
#በስፔን የሟቾች ቁጥር መጨመር እያሳየ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 435 ሰዎች ሞተዋል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 21,717 ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪ በአንድ ቀን 4,211 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 204,178 ደርሷል።
#በደቡብ ኮሪያ 11 ተጨማሪ ኬዞች ሪፖርት ተደርገዋል። ከአስራ አንዱ መካከል ስድስቱ (6) ከውጭ የገቡ ናቸው።
#ሲንጋፖር የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመግታት ያወጣቻቸውን ገደቦች እስከ June 1 አራዝማለች።
#በኳታር ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 608 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
#በቻይና ተጨማሪ 30 ኬዝ ተመዝግቧል። ሀያ ሶስቱ (23) ከውጭ የገቡ ናቸው።
#በማዳጋስካር ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት አዲስ ኬዝ እንዳልተመዘገበ ተሰምቷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 121 ሲሆኑ 52 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
#በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 2,586,639 ደርሷል። 179,942 ሰዎች ሞተዋል። 705,814 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።
https://telegram.me/jossiale2022