የልባችሁን ምረጡ!➡️➡️➡️🗣️🗣️
እውነት እውነቱን አውሩ፣ ግልፅ ግልፁን አስቀምጡ። አሁን ላይ ተስፋችሁ ማነው? ያኖረኛል ብላችሁ የምታስቡት አካል ማነው? ሁሉነገራችሁን ብታጡ እንኳን ያ አካል አብሯችሁ ስለሆነ ብቻ ሙላትና እረፍት የሚሰማችሁ ማነው? ሰውን ተስፋ የሚያደርግ በርሱም ላይ የሚተማመን እርሱ የተረገመ ይሁን እንዲል መፅሐፍ። ይሔን እንኳን እያወቃችሁ በሰው ተደግፋችኋልን? ይሔን እየሰማችሁም ሰውን ተስፋ አድርጋችኋልን? ለማን ምንያህል ቦታ መስጠት እንዳለባችሁ ካላወቃችሁ መቼም ቢሆን ልባችሁ ሊያርፍ አይችልም። የሚያኖራችሁ ፈጣሪ ሆኖ ሳለ የማያኖራችሁ የሰው ልጅ ላይ አትጣበቁ፤ ብትወድቁ የሚያነሳችሁ፣ ብትሳሳቱ የሚያርማችሁ፣ ብትጠፉም የሚመልሳችሁ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ሰውን ከልክ በላይ በሰው ወይም ባላችሁ ነገር ላይ አትደገፉ። አፈጣሪ ውጪ ሌላው ምድራዊ ነገር ጠፊና አጥፊ ነው። ሲታይ ራሱ የማይጠፋ ይመስላል ነገር ግን ይጠፋል፣ ሲታሰብ ብዙና ሀይለኛ ይመስላል ሲጨበጥ ግን ምንም ነው። ሳይጨልም ንቁ፣ ጊዜው ሳያልፍ ተማሩ።
አዎ! ጨለማ በብረሃለን ይጠፋል፣ ብረሃን ለጨለማ እጁን ይሰጣል። ተፈጥሮ ፈረቃ አላት። ያለምንም ፈረቃ፣ ያለምንም የጊዜ ገደብ፣ ያለምንም እርከን የሚሰራ ግን ፈጣሪ ብቻ ነው። ዓለምን ከጥግ እስከ ጥግ አይታችኋታል፣ ባታዩአትም ስለርሷ ብዙ ሰምታችኋል፣ የምድር ምርጫ ምን አንደሆነ፣ ከእናንተ ምን እንደምትፈልግ፣ ማንስ ደግሞ እንደሚያዋጣችሁ በሚገባ ታውቃላችሁ።
የልባችሁን ምረጡ፣ ለሚያሳርፋችሁ ቦታ ስጡ፣ የሚያኖራችሁን አጥብቃችሁ ያዙ። በራሳችሁ ብርታት ብቻ ዛሬ ያላችሁበት ስፍራ አልደረሳችሁም፤ በዙሪያችሁ ባሉ ሰዎች እርዳታ ብቻ አሁን ያገኛችሁትን ነገር አላገኛችሁም። ባፈራችሁት ንብረት ወይም በገነባችሁት ዝና ብቻ ነፃ አልወጣችሁም። አወቃችሁትም አላወቃችሁትም፣ አስተዋላችሁትም አላስተዋላችሁትም፣ የሚገባውን ቦታና ክብር ሰጣችሁት አልሰጣችሁትም በእያንዳንዱ ጥቃቅን እርምጃዎቻችሁ ውስጥ ፈጣሪ ነበረ፣ ዋናው የእርሱ ስራ ነበረ።
አዎ! ጀግናዬ..! ብትረሳ ብትረሳ እስከዛሬ ያኖረህን፣ እዚህ ያደረሰህን፣ ብዙ ብዙ ነገር ያሳለፈህን የእርሱን የፈጣሪህን ውለታ እንዳትረሳ። በሁለት እግር ቆሞ መሔድ ትልቅ ፀጋ ነው፣ በራስ ፍላጎት ወደ ብዙ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ስጦታ ነው፣ ሌላው ቢቀር ለማማረርና የጎደለውን ነገር ለመጠየቅ እንኳን መመረጥ ያስፈልጋል። የትናንት ከባድ አስጨናቂ ጊዜ እስኪያልፍ ረጅም ነበር ሲያልፍ ግን ምንም ነው። ለሰውም ይሁን ለሰዎች ውለታቢስ አትሁን፣ አምላክህንም የምትፈልገውን ለመጠየቅ አትፈር። ከላይ ከላይ ሳይሆን የውስጥህን አውጥተህ ፈጣሪህን ጠይቅ። ሀሳብ ይዘህ አትተኛ፣ ራስህን እያስጨነክም ህይወትህን ለመግፋት አትሞክር። ልብህ አይደንግጥ፣ ውስጥህም አይረበሽ። ህይወት ብለህ የምትኖረውን ኑሮ በአምላክህ ፍቃድና በራስህ መንገድ ለመኖር ራስህን አሳምን።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
በ
YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻
SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1ምክረ-አዕምሮ/
@mikre_aimro 😊 💪