ክፍል-2 እውነተኛው የእስር ቤት ገጠመኝ
✍️ሰዎች ምንድን ነው ለማለት ለመጠየቅ መድፈር ተሳናቸው ድባቡ ትንሽ ያስፈራ ነበርና።ነሷራ አምናያዎቹ እሳት የሆነ ግልምጫቸውን መወርወር ጀመሩ እኔም ሓስቢየላህ ወኒዕመል ወኪል እያልኩ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ። አሁንም ባለሱፉ ከፌደራሎቹ ጋ ጠጋ ብሎ እንደማስጨነቅ አይነት መንገድ ተጠቅሞ ወደ ቤትህ ምራ በማለት ሲያንባርቅብኝ እኔም ኮስተር ብዬ ቤት የለኝም አልኩኝ
ሃሃሃሃ ቤት የለህም ጎዳና ነው ወይስ ጫካ የምት ኖረው በማለት አሾፉና ያችን ጥቁር ዱላ አስተካከሉ
✍️ኣሃ ሊወግሩኝ ነዋ ብዬ ተመትቸም ቤትም መርቸ ኣይይ ይሄማ አይሆንም ወዳጆቹ እንዲያዝኑ ጠላቶቸ ደስ እንድላቸው አላደርግም ብዬ ከውስጤ ጋ ተስማማሁና ወደ ቤት መምራቱን መረጥኩ ምክናያቱም ተመትቸም ቤትም በግድ መምራቴ አይቀርምና።
✍️ና ብለው ገፍተር ለማድረግ እየሞከሩ ፓትሮል ላይ ጫኑኝና በሒወቴ ጠባሳው የማይለቀኝን ስራ ሊሰሩ ወደ ሰፈር ቤት ፍተሻ ጉዞ ጀመርን።
✍️አንድ ባለሐብት ወንድም ስቴሽነሪ ሱቅ ላይ ተቀጥሬ እሰራ ስለነበር ከተማሪ እስከ የመንግስት ሰራተኛው በርካታው የከተማ ሕዝብ ያውቁኛልና በፓትሮል ተጭኘ ባዩ ጊዜ በድንጋጤ ራሱን የያዘ የሚያለቅስም መንገድ ዳር ቆሞ ሁኔታውንም የሚመለከት ሰው ሞልቷል።
✍️ፓትሮሉ ሰፈር በደረሰ ጊዜ የወታደሩን ድባብ ያዩ የሰፈር ሰወች ህፃናቶች ዋይታቸውን ለቀቁት።
፨ውሓ እየረጨሁ የማጫውታቸው በዚህ ጨዋታ ሱስ የሆነባቸው ከስራ ወደሰፈር መምጣቴን የሚጠባበቁት ህፃናቶች በዛች ቀን ግን ጨለማ የሆነባቸው መሳሪያ የደቀኑና የሰፈሩን ዋና ቦታዎች አቀባብለው በሚጠባበቁ ወታደሮች ተከብቤ ባዩኝ ጊዜ
😥ሰው የሚታሰረው ሰው ጋ ተጣልቶ መሆኑን ብቻ እሱኮ አይጣላም በማለት ከወላጆቻቸው ጋ ይዳረቃሉ።
✍️በዚህ መልኩ ግቢውን አቀባብለው የሚጠብቁ ወታደሮች ተመድበው የተወሰኑት እኔን ይዘው ወደ ቤት ውስጥ ገባን።
✍️እንደ እኔ ቤት ፍተሻ የሚባል ነገር በጣም አሳማሚ ከሕሊና የማይጠፋ ድርጊት ነው።
✍️ኪታቤን ከወጥ ጋ እያዳፉ ዘግናኙ የቤት ፍተሻ ተጀመረ ልብስን በጫማ እየረገጡና ውሓውንም እየደፉ ያጣድፉኝ ጀመር።
✍️አንዱ ፓስፓርት አገኘሁ ሲል ሌላኛው የስላቅ እየሳቀ ሶማሊያ ነው ሶሪያ የምትሄደው ይላል።
✍️ሌላው ፍላሾች አገኘሁ ሲል ኮርስ የሚሰጥበት ነው ይባባላሉ።የባንክ ደብተር አገኘሁ ሲለው ከአረብ አገር የሚቀበልበት ነዋ ይባባላሉ።
✍️ይሄ ሁሉ ኪታብ ምንድን ነው በማለት ከጫፍ ሲነካው ከመደርደሪያ ሙሉ ወረደ በጫማው ረገጠው እኔ ግን አሁን ደንዝዣለሁ
✍️ሰዓቱ እየመሸ ነው መግሪብ ደረሰ ያገኙትን ይዘው ከቤት ወጡና መሳሪያ አለህ አውጣ በማለት ያፋጥጡኝ ጀመር።እኔም እረ የለኝም አልኩ አንዱ ደብተራ አምንያ ማተቡን በእጁ ይዞ አንተ እኛን ልትገድል ነው በማለት በጥፊ ሊማታ ሲንደረደር አንድ ፌደራልና ፖሊስ እረፍ በሕግ ጥላ ስር ነው በማለት አስቆሙልኝ።
መሳሪያውን አውጣ እያሉ የተወሰነ ካስጨነቁኝ በሗላ ቀጥታ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ፓትሮል ላይ ጭነው ይዘውኝ ሄዱ።
✍️የመጀመሪያዋ የእስርቤት አዳር ......
https://t.me/SebahulKeyr