✝
ጰራቅሊጦስ✝
ጰራቅሊጦስ ከሦስቱ አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው።
✝የሚያፀና
✝ የሚያበረታ
✝እስትንፋስ ሕይወት ነው።
✝ጰራቅሊጦስ እንደ አብ እና እንደወልድ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ያለው ነው።
✝ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ እንደአብና አንደወልድ የራሱ ግብር ያለው ነው።
✝ጰራቅሊጦስ ከአብ የሰረፀ ነው።ግብሩ ከአብ መስረፅ ነው።
✝የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ ወልድ በጌትነቱ ለፍርድ ሲመጣ አብሮ ከአብ ጋር የሚመጣ ነው።
✝ጰራቅሊጦስ እንደአብና እንደወልድ ዘላለማዊ ነው።
✝ስልጣኑ ከአብና ከወልድ እኩል ነው።
✝ጰራቅሊጦስ በነብያት በሐዋርያት አንደበት አድሮ ይናገራል(ያናግራል)።
✝ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ 👉ጥበብን
👉እውቀትን
👉ምስጢርን ይገልፃል።
✝ጰራቅሊጦስ ከአለም አስቀድሞ የነበረ ነው።
(ዮሐ 14 )
------------
25 25 ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤
26 አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
27 27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።
የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ በሁላችንም ይሙላ።
አሜን አሜን አሜን
✝✝✝✝✝✝✝
✝
@yetsadikulejoch✝
✝
@yetsadikulejoch✝
✝
@yetsadikulejoch✝
✝✝✝✝✝✝✝✝