#ተሾመ_ምትኩ
#ሱሰኛሽ
ሰማይ ሲላወስ ፣ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ፣ ጨለማ ሲነግስ
ጨረቃ ስደምቅ ፣ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ፣ ከዛፍ ከቋጡ
ሰማይ ሲላወስ ፣ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ፣ ጨለማ ሲነግስ
ጨረቃ ስደምቅ ፣ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ፣ ከዛፍ ከቋጡ
አማል ያለብኝ ፣ እኔ ሱሰኛሽ
አይቼ አልጠግብሽ ፣ ውጬ አልጨርስሽ
መውደድሽ ግሎ ፣ ልቤን ተኮሰው
እኔስ የት ልግባ ፣ ወዴት ልድረሰው
መውደድሽ ግሎ ፣ ልቤን ተኮሰው
እኔስ የት ልግባ ፣ ወዴት ልድረሰው
የፍቅርሽ ብዛት ፣ ልቤ ውስጥ ገብቶ
አርበተበተኝ ፣ አንጀቴን በልቶ
እኔ ሱሰኛሽ ለሞጋግስሽ
እንደ ዳኤትም ፣ እስኪ ልድገምሽ
የፍቅርሽ ብዛት ፣ ልቤ ውስጥ ገብቶ
አርበተበተኝ ፣ አንጀቴን በልቶ
እኔ ሱሰኛሽ ለሞጋግስሽ
እንደ ዳኤትም ፣ እስኪ ልድገምሽ
ሰኞ ማክሰኞ ፣ ሮብ እና ሀሙስ
አርብ አመት በዓል ፣ ቀናቱ እስኪደርስ
ሱስ ያለኝ እኔ ፣ መች ያስችለኛል
ሲመሽ ሲነጋ ፣ አንቺን ይለኛል
ሱስ ያለኝ እኔ ፣ መች ያስችለኛል
ሲመሽ ሲነጋ ፣ አንቺን ይለኛል
እንደንጸባረቂ ፣ ፊትሽ ሲያበራ
መቃው አንገትሽ ፣ ከሩቅ ሲጣራ
ተልፈሰፈስኩኝ ፣ ጉልበት አነሰኝ
ልቤ ተነካብኝ ፣ መቻል አቃተኝ
እንደንጸባረቂ ፣ ፊትሽ ሲያበራ
መቃው አንገትሽ ፣ ከሩቅ ሲጣራ
ተልፈሰፈስኩኝ ፣ ጉልበት አነሰኝ
ልቤ ተነካብኝ ፣ መቻል አቃተኝ
አላስቀድስም ፣ ታቦት አላደርስ
የኔ ውዳሴ ፣ አንቺ የኔ መቅደስ
ሱባዔ አልገባ ፣ መቆሚያም የለኝ
ምርኩዜም አንቺ ፣ እስኪ አንቺው ባርኪኝ
ሱባዔ አልገባ ፣ መቆሚያም የለኝ
ምርኩዜም አንቺ ፣ እስኪ አንቺው ባርኪኝ
ሰማይ ሲላወስ ፣ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ፣ ጨለማ ሲነግስ
ጨረቃ ስደምቅ ፣ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ፣ ከዛፍ ከቋጡ
ሰማይ ሲላወስ ፣ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ፣ ጨለማ ሲነግስ
ጨረቃ ስደምቅ ፣ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ፣ ከዛፍ ከቋጡ
ሰማይ ሲላወስ ፣ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ፣ ጨለማ ሲነግስ
ጨረቃ ስደምቅ ፣ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ፣ ከዛፍ ከቋጡ
YBC music & Movie Join👇
👉
@ybcmusic17👉
@ybcmusic17