⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️
ይህ የወንድማችን ዒዘዲን ኢልያስ አውፍታ ጥያቄ ነው ።
የመልእክቱ ይዘት : –
ወደ ተከበሩት ሸይኽ ዐ/ሐሚድና ከሳቸው ጋር ያሉ መሻኢኾችና ዱዓቶች
አላህ ይጠብቃችሁ
ምስጋና የተባለ ሁሉ ለአላህ የተገባ ይሁን ። ሶለዋትና ሰላም ከሳቸው በኋላ ነብይ ለሌለው ነብይ ላይ ይሁን ።
በመቀጠል : –
ወደ ሁላችሁም የረቅርታ በመጠየቅና ዑዝር ማቅረብ እወዳለሁ ። ይህም የናንተን ክብር በመንካቴ ነው ። ክብራችሁን ለመንካት ሰበብ የሆነኝ በናንተና በኢብኑ ሙነወርና ከርሱ ጋር ካሉት ጋር ተፈጥሮ የነበረው ፊትና ነው ። እኔም በፊትናው በችኮላና በስሜታዊነት ጠልቀው ከገቡት ውስጥ ነበርኩ ። ምስጋና ለአላህ የተገባ ይሁን ። አሁን ሐቁ ግልፅ ሆኖልኛል የሰለፎችንም ሚንሀጅ አውቄያለሁ ። ማን በዚህ ጎዳና ላይ እየሄደ እንደሆንም ተረድቻለሁ ። እዚህ ጋር ግልፅ መሆን እፈልጋለሁ ። ሐቁ ከናንተ ጋር ነው ። አላህ መልካሙን ይግጠማችሁ ። እኔንም እናንተንም እስከ ሞት እለት ድረስ በሐቅ ላይ ያፅናን ።
ከርሶ ጋር ያሉና ክብራቸውን ከነካዃቸው ወንድሞች መካከል
ባሕሩ ተካ
ሱልጣን ሻኪር
ሸምሱ ጙልታ
ከሁላችሁም ላጠፋሁት ጥፋት ይቅርታ እንድታደርጉልኝ እመኛለሁ ። ወንድማችሁና ወዳጃችሁ
ዒዘዲን ኢልያስ ከሐላባ ከተማ "
➡️ ወንድማችን አሁን ያለው ዱባይ ነው ። ምክንያቱም የተላከበት አድራሻ የዱባይ ስለሆነ ። ሸይኻችን አውፍ እንደሚሉ እርግጠኛ ነኝ ። ወንድሞቼም እንደዚሁ ። በመሆኑም በኛ በኩል የሚፈለገው ሰዎች ሐቅ እንዲረዱ ነው ። ከዚህ በላይ የሚያስተደስት ነገር የለም ። የሚያስጨንቀው የሱና ክብር ነው ። ስለዚህ ወንድማችን አላህ ይቀበልህ አው እንዳልከውም እስከ እለተ ሞታችን ድረስ በሐቅ ላይ አላህ ያፅናን ።
https://t.me/bahruteka