🔷 ፅናት ( አል ኢስቲቃማ )
ፅናት ማለት አንድ ሰው በሚያምነበት ነገር ላይ ቀጥ ማለቱ ወይም በሚሰራው ስራ ላይ ቀጥ ማለቱ ነው ። ይህ በሐቅም በባጢልም ላይ ሊሆን ይችላል ። ባጢልን ይዞ አለቅም ማለትና በዛ ላይ መፅናት የተወገዘ ሲሆን ሐቅን ይዞ አለቅም ማለትና በዛ ላይ መፅናት የተወደደና የሚፈለግ ነው ።
በሐቅ ላይ የሚፀኑ ሰዎችን አላህ መለኮታዊ በሆነ ቃሉ ዱንያን ለቀው ወደ አኼራ በሚሄዱበት ጊዜ መላኢካ እንደሚወርድላቸውና አትፍሩ አትዘኑ ዘላሚዊ በሆነው የተድላ ሀገር ተደሰቱ እኛ በዱንያም በአኼም ወዳጆቻችሁ ነን እንደሚሉዋቸው እንዲሁም ከመሀሪውና አዛኙ ጌታ የተዘጋጀ ሰፍሳችሁ የምትሻውና ቃል ኪዳን የተገባላችሁ ፀጋ አለላችሁ እንደሚሉዋቸው እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –
« إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُونَ »
فصلت ( 30 )
" እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ "፡፡
« نَحْنُ أَوْلِيَاؤُكُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ ۖ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَشْتَهِي أَنفُسُكُمْ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ »
فصلت ( 31 )
«እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አልላችሁ ፡፡ ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምትፈልጉት ሁሉ አልላችሁ "፡፡
ይህ የተስፋ ቃል አምላካችን አላህ ነው ብለው ይህ የምስክርነት ቃላቸው የሚያስፈርደውን አላህ ያዘዘውን እየሰሩ የከለከለውን እየተከለከሉ የፀኑና ቀጥ ያሉ ሆነው በዚህ ሁኔታ ወደ አኼራ ለሚሄዱት ነው ።
የአንድ ሶመን ነሻጣ ይህን የተሰፋ ቃል አያሰጥም ። የሙእሚኖች ባህርይ በኢማናቸው ላይ መፅናት ነው ። በሐቅ ላይ ፅናት የጀነት ቁልፍ ናት የሚባለውም ለዚህ ነው ።
እንደሚታወቀው ይህ የረመዳን ወር ብዙ ሰዎችን ያነሽጣል ። ብዙዎች የተለያየ ዒባዳ ላይ ይጣዳሉ ። ሶላት ፣ ቂራአት ፣ ዚክር ፣ ሶደቃ ፣ ዚያራና የመሳሰሉ የዒባዳ አይነቶችን ይሰራሉ ። ነገር ግን አብዛኛዎች ረመዳን ሲያልቅ በዛው ይጠፋሉ ።
በተውበትና በዒባዳ ሲታጠብ የነበረው ስብእናቸው በዒዱ ማግስት በወንጀል ማጨቅየት ይጀምራሉ ።
ያ ዒባዳ ከንቱ ልፋት ሆኖ ይቀራል ። ሌሎች ደግሞ አሉ የተወሰነ ጊዜ በጀማዓ ሶላትና በለይል ሶላት ላይ ቀጥለው ማዝለቅ የማይችሉ ጥለው የሚወጡ ከእነዚህ የሚመደቡ ደግሞ በዐቂዳ ላይ የት ይደርሳሉ የተባሉ የነበሩ ከጊዜ በኃላ አልበሰልንም ነበር የሚሉ የነበሩበትን የሰለፎች መንገድ እንደ አዳር ልብስ አውልቀው የሚጥሉና ፍልስፍናን ይህ ነው የሰለፎች መንገድ የሚሉ ።
በሐቅ ላይ ፅናት የሚባለው ነገር አላህ ላገራለት ገር ቢሆንም ከሚፈታተኑት ነገሮች ብዛት አንፃር ከባድ ነው ። አላህ ሐቅን ያሳወቃችሁና ባለቤቱ የሆናችሁ ፅናት እንዲሰጣችሁ አላህን ለምኑ ።
በሐቅ ላይ ፀንተው ኖረው በሐቅ ላይ ሆነው አላህን ከሚገናኙት አላህ ያድርገን ።
" በሐቅ ላይ መፅናት የጀነት ቁልፍ ናት "
https://t.me/bahruteka