Alain Amharic


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በሐዋሳ በዓሉን አስመልክቶ ለችግረኞች የተደረገ ድጋፍ

1 ሺ 441ኛውን የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን አስመልክቶ በሐዋሳ ከተማ ለ450 ችግረኛ ቤተሰቦች የሚሆን የእርድ ከብቶች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=l7SgNy9PpU0
አል ዐይን አማርኛን ይከተሉ ላይክ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ!
ድረ-ገጽ https://am.al-ain.com
ፌስቡክ https://www.facebook.com/AlAinAmharic/
ቴሌግራም https://t.me/alainamharic
ትዊተር https://twitter.com/AlainAmharic
ዩ-ቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCcdnPQepsScsqMWOtrBDd2w/about
ይወዳጁን!
ቤተሰብ ይሁኑ!
ከኮሮና ይጠንቀቁ!
ራስዎንና ቤተሰብዎን ወገንዎንም ይጠብቁ!
እስካልተገደዱ ድረስ በቤትዎ ይቆዩ! https://www.youtube.com/watch?v=l7SgNy9PpU0


በኢትዮጵያ በጽኑ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በጽኑ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃዎች አመለከቱ፡፡
ሚኒስቴሩ ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን ይፋ ባደረገበት መረጃው 134 ሰዎች በጽኑ መታመማቸውን ጠቁሟል፡፡
የጽኑ ታማሚዎቹ ቁጥር ትናንት ሃምሌ 22 ቀን 2012 ዓ/ም በሚኒስቴሩ ሪፖርት ከተደረገው የ68 ታማሚዎች ብልጫ አለው፡፡
ባለፉት ተከታታይ 4 ቀናት በጽኑ ታመዋል የተባሉት ሰዎች ቁጥር 66 ነበረ፡፡
“በፅኑ የታመሙ እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው” የሚል ጽሁፍን ከሰሞኑ በይፋዊ የማህበረሰብ ገጻቸው ያሰፈሩት ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ “ስርጭቱን ለመቀነስና በቁጥጥር ስር ለማዋል የተቀመጡትን ጥንቃቄዎች ሁሌም እንተግብር” የሚል መልዕክትን ማስቀመጣቸው የሚታወስ ነው፡፡




ተጨማሪ 805 ሰዎች በቫይረሱ ተያዙ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 9 ሺ 786 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 805 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
78 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ያስታወቁት ሚኒስትሯ 134 ሰዎች በጽኑ መታመማቸውንና የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት 9 ሺ 587 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው በሚገኙባት ኢትዮጵያ 6 ሺ 763 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ263 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺ 615 መድረሱም እስካሁን በተደረገ 413 ሺ 397 የላቦራቶሪ ምርመራ ተረጋግጧል፡፡








ዶናልድ ትራምፕ የ2020 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲዘገይ ጥሪ አቀረቡ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳር 2020 የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲዘገይ በትዊተር ገጻቸው ጥሪ ማቅረባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት በኢሜልና በፖስታ ሊደረግ የታሰበው የሕዳሩ ምርጫ እንዳይጭበረበር ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ ሕዳር የሚካሄደው ምርጫ የማይዘገይ ከሆነ በታሪክ ከፍተኛ የሆነ የድምጽ ማጭበርበር ሊከሰት እንደሚችል ግምት አስቀምጠዋል፡፡ የተሳሳተ ውጤት ከሚመጣ ምርጫው ቢዘገይ የሚል ሃሳብ ያቀረቡት ትራምፕ የሰው ልጆች የጤና ስጋት ውስጥ በማይገቡበትና አስተማማኝ በሆነ መልኩ ድምጽ መስጠት እስከሚችሉ ድረስ ምርጫው እንዲዘገይ ሀሳብ አቅርበዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝበ ሙስሊሙ ለግድቡ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ላበረከተው አስተዋጽኦ አመሰገኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ የሚከበረውን የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የዘንድሮው አረፋ በተለያዩ ምክንያቶች ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ለየት ያለ ትርጉም አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ውኃ ሙሌት በተሳካበት ጊዜ የሚከበር መሆኑን በከፍተኛ ሐሴት ውስጥ ሆኖ በዓሉን ለመቀበልና ለማክበር እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ሙስሊሞች ለተገኘው ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ለከፈሉት መስዋዕትነትም አመስግነዋል፡፡
በዓሉ መልካም ሰዎች ለመልካም ዓላማ ሲሉ እጅግ ውድ የሆነ ሀብታቸውን፣ ልጃቸውን የሰጡበት “የመሥዋዕትነት በዓል” ነው ያሉም ሲሆን ከዚህ በተቃራኒው ባላቸው እኩይ ዓላማ በወንድምና እህቶቻቸው ላይ ሳይቀር በትር የሚያነሱ አካላትን ህዝበ ሙስሊሙ “በጥበብ እንዲያስተምራቸው አደራ” ብለዋል፡፡
የዘንድሮው በዓል ዓለም በኮሮና ወረርሽኝ እየተፈተነች ባለችበት ወቅት የሚከበር ነው ያሉት ዐቢይ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ ጥንቃቄ እንዲያከብረውና ወረርሽኙን መከላከልን እንደ አንድ ሃይማኖታዊ ግዴታ አድርጎ ሊወስደው ይገባልም ነው ያሉት፡፡
አቅማቸው ደከም ያሉ ወገኖች እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
“በቀሪ የግድቡ ሥራዎች ላይ እንድንረባረብና የአረንጓዴ አሻራችንን በስኬት እንድንወጣ ከሁላችንም ይጠበቃል” ሲሉም የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።




በአሜሪካ በእያንዳንዷ ደቂቃ ሞት እየተመዘገበ ነው

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ150 ሺ አሻቅቧል፡፡
ይህም በእያንዳንዷ ደቂቃ አንድ ሰው እየሞተ መሆኑን የሚመለክት ነው፡፡
ትናንት ረቡዕ ብቻ 1 ሺ 461 ሰዎች ሞተዋል፡፡
ይህ ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ 1 ሺ 484 ሰዎች ከሞቱበት እ.ኤ.አ ከግንቦት 27 2020 ወዲህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛው ሪከርድ ነው፡፡
በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁ 20 የዓለማችን ሃገራት ውስጥ ቀዳሚ የሆነችው አሜሪካ በሟቾች ቁጥር 6ኛ ነች፡፡
ከ1 መቶ ሺ ሰዎች መካከልም በአማካይ 45ቱ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ይሞታሉ፡፡
በእንዲህ ኣይነቱ የአማካይ ንጻሬ ዩናይትድ ኪንግደም፣ስፔን፣ጣሊያን፣ፔሩ እና ቺሊ ብቻ ናቸው አሜሪካን የሚቀድሙት፡፡




ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ይካሄዳል የተባለው ምርጫ እንዳማያሳስባቸው ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የፌደሬሽን ምክርቤት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት “ምርጫ 2012” ሲራዘም የሁሉም ክልሎች ስልጣን እንዲራዘም ስለተወሰነ፤ሕወሓት ምርጫ እድርጎ ስልጣኑን ለሌላ ፓርቲ እስካልሰጠ ድረስ እንደማያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ የምርጫ ቦርድ አቋቁም እየሰራ መሆኑ አስታውቋል፡፡

የትግራይ ክልል የፌደራል መንግስት ኮሮናን እንደሰበብ ተጠቀመበት እንጂ ከመጀመሪያውም ምርጫውን ለማካሄድ ፍላጎት አልነበረውም ሲል ይከሳል፡፡ የፌደራል መንግስት በበኩሉ ምርጫ ለማካሄድ ጽኑ ፍላጎት ከነበራቸው ፓርቲዎች አንዱ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጿል፤ይህን ትችትም አይቀበለውም፡፡https://am.al-ain.com/article/pm-abiy-says-planned-tigray-election-is-not-bothering-him


የዘንድሮው ሃጅ መዘጋትና የውጭ ግብይት ተጽዕኖ

ሞቃዲሾ ይህን የምታጣው በታላቁ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት ላይ ታቀርብ የነበረው የእርድ እንስሳት ቁጥር በእጅጉ በመቀነሱ ምክንያት ነው፡፡
https://am.al-ain.com/article/somalia-will-lose-500-million-this-year-as-its-livestock-misses-out-on-hajj-to-saudi-arabia


ሶማሊያ የዘንድሮው ሃጅ በመዘጋቱ ምክንያት እስከ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ታጣለች

የዘንድሮው የሃጅ የጉዞ ስነ ስርዓት መቋረጡ ሶማሊያን 5 መቶ ሚሊዮን ዶላር እንደሚያሳጣት ኳርትዝ አፍሪካ የተሰኘ የዜና አውታር ዘገበ፡፡
ሞቃዲሾ ይህን የምታጣው በታላቁ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት ላይ ታቀርብ የነበረው የእርድ እንስሳት ቁጥር በእጅጉ በመቀነሱ ምክንያት ነው፡፡
ይህም ግመልን የመሳሰሉ የቁም እንስሳትን በመላክ ከወጪ ንግዱ ታገኝ የነበረውን ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገንዘብ ያሳጣታል፡፡




ተመድ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ766ሺ በላይ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ገንዘብ አጠረኝ አለ

ተመድ ለስደተኞቹ ከሚያስፈልገው 385 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 72 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘት ማግኘቱን ገልጿል፡፡ከፈረንጆቹ ሰኔ 30 ጀምሮ ኮሚሽኑ ከ766ሺ በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በኢትዮጵያ በስተኞች ካምፕና በስድስት ክልሎች ይገኛሉ፡፡https://am.al-ain.com/article/unhcr-says-faces-critical-financial-shortage-to-meet-refugees-demand


አሜሪካ በጀርመን ካላት ጦር 12 ሺ ገደማው ልታስወጣ ነው


ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጀርመን ካለው የሃገራቸው ጦር ውስጥ 11 ሺ 900ው እንዲወጣ ትዕዛዝ ስለመስጠታቸው ለጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡
ከአሁን በኋላ ልንታለል የምንችልበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ጀርመንን በቸልተኝነት ኮንነዋል፡፡
ትራምፕ ከአጠቃላይ አመታዊ የሃገር ውስጥ ምርቷ 2 በመቶ ያህሉን ለሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ለማበርከት የገባችውን ቃል አልጠበቀችም በሚል ጀርመንን መውቀሳቸው የሚታወስ ነው፡፡
ጀርመንን ለቆ ይወጣል ካሉት ጦር ውስጥ 5 ሺ 600 ያህሉን ጣልያንና ቤልጂዬምን ወደ መሳሰሉ የአውሮፓ ሃገራት የማዘዋወር እቅድ እንዳላቸውም ነው የእንግሊዙ ኢቭኒንግ ስታንዳርድ የዘገበው፡፡




ተመድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት የገንዘብ እጥረት ገጠመው

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ)የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ ለስደተኞች አስፈላጊ የሆኑ የምግብ፣የትምህርት፣ የጤናና የመጠለያ ፍላጎቶችን ለማሟላት ከሚያስፈልገው 385 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 72 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘት መቻሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከፈረንጆቹ ሰኔ 30 ጀምሮ ኮሚሽኑ ከ766ሺ በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በኢትዮጵያ በስተኞች ካምፕና በስድስት ክልሎች ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኡጋንዳ ቀጥሎ በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡

Показано 20 последних публикаций.

861

подписчиков
Статистика канала