#Ethiopia
ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡
ከተመሩት ረቂቅ አዋጆች መካከል አንዱ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ነው።
የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አዋጁ በስራ ላይ ከዋለ 6 አመት ያስቆጠረ መሆኑንና አሁን ካሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር ማጣጣም ማስፈለጉን ገልጸዋል።
የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሀይል ምልመላና መረጣ ግልጽነት ባለው ውድድርና ብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሁሉንም ባካተተና ብዝሀነትን በጠበቀ መልኩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ከተደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ፦
➡ የደሞዝ ጭማሪ፣
➡ የደሞዝ እርከን፣
➡ ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ማትጊያና ማበረታቻ ስርአት፣
➡ የሰራተኞች ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስልጠና አሰጣጥ ስራ ስምሪት እና ነጻ ገለልተኛ ስርአት መገንባት፣
➡ የመንግስት ሰራተኛነት ውል ማቋረጥና ማራዘም የሚሉና ሌሎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 13/2016 ሆኖ በሙሉ ደምጽ ለሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡
ሌሎች ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የተመሩ ረቂቅ አዋጆች ምንድናቸው ? በዚህ ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Ethiopia-05-14-8
@tikvahethiopia