Репост из: About Laws ስለህጎች🇪🇹
ስለ ኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ የምንዳስስ ይሆናል፡፡
በዚህ ክፍል ላይ ስለ ጋብቻ አይነቶች እና ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እንመለከታለን፡፡
ቤተሰብ ትልቅ ተቋም በመሆኑ የህግ ጥበቃ የሚደረግለት ተቋም ነው፡፡ የቤተሰባዊ ግንኙነት ከሚመሰረትባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ጋብቻ ነው፡፡
ጋብቻን እና ተያያዥ ጉዳዮች በፌደራል ደረጃ የሚዳኙት ወይም የሚገዙት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ዓ.ም ነው፡፡
በዚህ አዋጅ መሰረት በሶስተ አይነት መልኩ ጋብቻ ሊፈፀም እንደሚችል ተቀምጧል፡፡ እነዚህን የጋብቻ አይነቶች ከመመልከታችን በፊት ጋብቻ ለመፈጸመም ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን እናያለን፡፡፡
አንድ ሰው ጋብቻ ለመፈፀም በቅድሚያ ሊያሟሏቸው የሚገቡ አስፈላጊ እና አስገዳጅ ቅድመ ሆኔታዎች አሉ፡፡
የመጀመሪያ በተጋቢዎች መካከል ነጻ ፍቃድ መኖር ነው ፡፡ 2ኛው ተጋቢዎች 18 አመት እድሜ የሞላቸው መሆን ያለበት ሲሆን በልዩ ሁኔታ ግን በፍትህ ሚንስትሩ ፍቃድ ሲሰጥ 16 አመት ለጋብቻ የተፈቀደ ጊዜ ይሆናል፡፡
3ኛው ደግሞ በተጋቢዎች መካከል የስጋ እና የጋብቻ ዝምድና አለመኖር ነው፡፡
4ኛው ተጋቢዎቹ በሌላ ጋብቻ ውስጥ አለመሆናቸው ወይም በጋብቻ ላይ ሌላ ጋብቻ ያለመፈጸም ነው፡፡
5ኛው ተጋቢዎች በፍርድ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው
6ኛው እና የመጨረሻው ቅድመ ሁኔታ
ለሴት ልጅ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ቀሪ ከሆነ በኋላ ወይም ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ለ180 ቀን ወይም ለ 6 ወር ያህል ሌላ ጋብቻ እንዳትፈፅም የተደነገገ ክልከላ ነው፡፡
ቀደም ሲል እንደገለፅኩላችሁ ሶስት የጋብቻ አይነቶች አሉ፡፡
1ኛ. በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ወሳኝ ኩነት በመሄድ የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡
2ኛው. በሃይማኖት ስርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህ ማለት ደሞ በቤተክርስቲያን ስርአት፤ በሼርያ ህግ እና በሌሎችም የሃይማኖት ስርአቶች ሊፈጸም የሚችል የጋብቻ አይነት ነው፡፡
3ኛው እና የመጨረሻው የጋብቻ አይነት ደግሙ በባህላዊ ሰርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህም በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ ባህላዊ ስርአቶች የሚፈፀም የጋብቻ አይነት ነው፡፡
በቀጣይ ክፍል ደግሞ ስለጋብቻ ውጤቶች የማቀርብላችሁ ይሆናል፡፡
የነጺ ሎው via Alternative legal enlightenment/ALE*
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
#አለሕግ #Alehig
@NegereHig
https://t.me/NegereHig