ኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን ለመገበያያነት ለመጠቀም የሚያስችል መመሪያ ልታወጣ እንደምትችል የብሔራዊ ባንክ ገዢ ጥቆማ ሰጡ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “የክሪፕቶ አሴትን” እና የዲጂታል ገንዘብን በኢትዮጵያ መጠቀም የሚያስችል መመሪያ ወደፊት ሊያወጣ እንደሚችል የተቋሙ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።
ብሔራዊ ባንክ መመሪያውን የሚያወጣው በማዕከላዊ ባንኪንግ፣ በገንዘብ ፖሊሲ እና በገንዘብ አስተዳደር ያሉ ዓለም አቀፍ “ለውጦችን” እና “እድገቶችን” እያየ መሆኑን አቶ ማሞ ተናግረዋል።
አቶ ማሞ ይህን ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአዋጅ ማሻሻያ ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 በተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀበት ወቅት ከፓርላማ አባል ለቀረበ ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ ነው።
የአሁኑ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ድንጋጌዎች መካከል ክሪፕቶ ከረንሲ እና የዲጂታል ገንዘብን መጠቀም የተመለከተው አንዱ ነው።
አዋጁ “አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ብሔራዊ ባንክ ካልፈቀደ በስተቀር፤ ክሪፕቶ ከረንሲ ወይም ሌላ ማንኛውንም ዲጂታል ወይም የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በመጠቀም ክፍያ መፈጸም አይችልም” ሲል ክልከላ ያስቀምጣል።
አዋጁን በመተላለፍ በእነዚህ መንገዶች ክፍያ የፈጸመ ማንኛውም ሰው፤ ከሶስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከአስር ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣም ተደንግጓል።
🦁 Source 🦁
https://ethiopiainsider.com/2024/14617/