አል-ፋሩቅ islamic


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


«ያ አላህ! ባልሰራበት እንኳ ወደ በጎ ነገር
ያመላከተ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ፡፡»
ማሳሰቢያ:- Leave Channel ከማለቶ በፊት
ያልተመቾት ነገር ካለ ያሳውቁን!
💻. #Channel_create_ሀምሌ _3_2013 ዓ.ል
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
🍂. ሀሳብ፣አስተያየት ካሎት ☞ ✍ @Allfaruq_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አስገራሚ ታሪክ ነው

አንዱ ሚስቱን ይመታታል። በአጋጣሚ ሊገድላት ሳያስብ በእጁ ትሞትበታለች። ጉዳዩ ይፋ ወጥቶ ዕዳ እንዳይኾንበት ምን ማድረግ እንዳለበት ያስባል። አስቦ አሰላስሎ በስተመጨረሻም አንድ ሀሳብ መጣለት። እርሱም ወደ ሰፈራቸው አዋቂ ነኝ ባይ ሰው ጋር መሄድ ነበር። ታዲያ ይሄ አዋቂ ተብዬ ሰውም መፍትሄ የሚለውን ሀሳብ እንዲህ ሲል ይመክረዋል ። ደጅህ ላይ ተቀምጥና ቆንጆ ወጣት ሲያልፍ ካየህ "አንዳች የምታግዘኝ ነገር አለ" በለውና ወደ ቤትህ አስገባው።

ከዚያም ግደለውና ከባለቤትህ እሬሳ ጋር አጠገብ ለአጠገብ አጋድመው ። የርሷን ቤተሰቦች ጥራና " ከዚህ ወጣት ጋር ሲያመነዝሩ ስመለከት እራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ እርምጃ ስወስድባቸው በእጄ ሞቱ" ብለህ ንገራቸው አለው።

አባ ውራውም መላ ነው ተብሎ የተነገረውን ተቀብሎ ደጃፉ ላይ ሄዶ ቁጭ ብሎ መጠባበቅ ይጀምራል። ብዙም ሳይቆይ አንድ ወጣት በአጠገቡ ሲያልፍ ተመለከተና "ወንድም አንዴ ላስቸግርህ? የሆነች ነገር እንድታግዘኝ ፈልጌህ ነበር" ብሎ አስማምቶ ወደ ቤት ያስገባዋል።

እንደተመከረውም ይገድለውና ከሚስቱ ጀነዛ አጠገብ ያጋድመዋል ። የሚስቱ ቤተዘመዶች ሲመጡም በዝሙት ላይ አግኝቷቸው ራሱን መቆጣጠር አቅቶት እርምጃ እንደወሰደባቸው ይነግራቸዋል። እነርሱም ጥፋተኛ ሳያደርጉት ምክኒያቱን ይረዱትና ይተዉታል።

ይሄንን የማምለጫ ዘዴ ነግሮት የነበረው ሰውዬ ገዳዩ ከምን
እንደደረሰ ሊጠይቀው ቤቱ ይከሰታል። ገዳዩ ሰውዬም የመከረውን እንዳደረገና እንደተሳካለት በኩራትና በምስጋና ይነግረዋል። እስኪ የገደልከውን ልጅ አሳየኝ ብሎ አዋቂ ተብዬው ይጠይቀዋል። ገዳዩ ወስዶ ሲያሳየውም ለካስ የተገደለው የራሱ የአዋቂ ነኝ ባዩ ልጅ ኖሯል! በሳሉት ቢለዋ
መቆረጥ ይሉሃል እንደዚህ ነው!

ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ ዐ) እንዲህ ይላሉ ። ለተንኮል ሰይፉን የሳለ እራሱ ይቆረጥበታል። ለወንድሙ ጉድጓድ
የቆፈረ ራሱ ይገባበታል። የሌሎችን ነውር አደባባይ የሚበትን የራሱ ነውር አደባባይ ይታይበታል።

ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉ

𝐉𝐨𝐢𝐧 & 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
@Alfaruq_islamic
@Alfaruq_islamic
★∩∩∩∩∩∩∩∩∩∩∩★


የኢስላም ጠላትና ትንሹ ታዳጊው ልጅ
………………………………………………………
@Alfaruq_islamic

✍ለኢስላም ጠላትነቱ የታወቀ አንድ ሰዉ ነበር በጊዜው በቦታው ላይ ማንም ያልመለሰለት ሶስት ታዋቂ ጥያቄዎች ነበሩት።


ባግዳር ላይ ካሉ አዋቂዎች አንዳቸውም ጥያቄዉን የመለሰለት አልነበረም ። በዚህም ምክንያት ሰዉየዉ እስልምና ላይ በግልፅ ይቀልድ ነበር


ኢስላምንና ሙስሊሞችን መንገር ላይ በህዝብ ፊት ያጥላላ ነበር አንድ ቀን ትንሽየ ልጅ እድሜዉ ገና አስር አመት የሆነ ታዳጊ ልጅ ሰዉየዉ ሶስቱ ጥያቄዎችን ደጋግሞ በማንሳት በንገር ላይ በህዝብ ፊት ሙስሊሞች ላይ ሲጮህና ሲቀልድ ይሰማዋል።

ይህ ታዳጊ የአስር አመት ልጅ ሰዉየዉ ተናግሮ እስኪጨርስ በዝምታ ከጠበቀ በኋላ ሰዉየዉን ሊጋፈጠዉ ወሰነ ።

ልጁ ወደ ሰዉየዉ ፊት ለፊት በመራመድ ጥያቄዎችህን እኔ እጋፈጣቸዋለሁ በማለት አሳወቀዉ ። ሰዉየዉ ጎንበስ ብሎ ልጁን ሲያየው ይበልጥ ማፌዙን ተያያዘው ።


የአስር አመት ልጅ እኔን ሊጋፈጠኝ ነው በቃ እናንተ ህዝቦች ማድረግ የምትችሉት ይህን ብቻ ነዉ በማለት ይስቃል ይሳቃል ይህ ታዳጊ ልጅ በአላህ ፍቃድ ጥያቄዎቹን ለመመለስ በትዕግስት የሰዉየዉን ምላሽ ይጠባበቅ ጀመር ።


በመጨረሻም ሰዉየዉ እስኪ እንስማህ የሚል የፌዝ ሞራል የዚህ ታዳጊ ልጅ ላይ አወረደበት።

የአካባቢው ሰዎች በአጠቃላይ ለአንዳንድ ጉዳያቸው በሚሰባሰቡበት ግልፅ የስብሰባ ቦታ ተሰባሰቡ ሰዉየዉ ከፍ ያለ ቦታ ወጣና ድምፁን ከፍ በማድረግ የመጀመሪያ ጥያቄዉን አቀረበ።

ባሁኑ ሰአት ፈጣሪያችሁ ምን እያደረገ ነዉ?? ይህ ትንሽ ልጅ ለትንሽ ጊዜ አሰበና ጥያቄዉን ይመልስለት ዘንድ ሰዉየዉን ካለበት ከፍታ ቦታ ላይ ወደታች እንድወርድና እሱ ከፍ እንድል ጠየቀዉ።

ምን እኔ ወደታች እንድወርድ ትፈልጋለህ ? ትንሹ ልጅ አዎን ጥያቄህን እንድመልስ ትፈልጋለህ አይደል ካለህበት ዉረድ አለዉ ።

ሰዉየዉ ካለበት ከፍታ ቦታ ወደታች ወረደ ትንሹ ልጁ ትንሽ እግሩን በመጠቀም ከፍታዉ ላይ ወጣና በጥያቄዉ ምላሹን ሰጠ። የአላህ በነዚህ ህዝቦችህ ፊት አንተ ምስክሬ ነህ ካፊር ወደታች እንደሚሆንና ሙስሊም ከፍ እንደሚል የገባኸዉን ቃል አደረከዉ አለ።

ሰዎች በአጠቃላይ በምላሹ ተገርመው ተክቢር አሏሁ አክበር አሉ ሰዉየዉ በጣም አፈረ። በድርቅና ሁለተኛውን ጥያቄ ጠየቀ ። ከፈጣሪያችሁ በፊት ምን ይገኝ ነበር ?? ትንሹ ልጅ በደንብ አሰበና ለሰዉየዉ ከአስር ጀምሮ ወደሗላ እንድቆጥር ይጠይቀዋል ።

ሰዉየዉ ቆጠረ.10. 9. 8. 7. 6. 5. 4. 3. 2. 1. 0. ልጁ ጠየቀ ከዜሮ በኋላ ምን ይመጣል ? ሰዉየዉ አላዉቅም ምንም አለዉ። በትክክል ከአላህ በፊት ምንም አልነበረም እርሱ ፍፁምና የማይሞት ነዉ።

ሰዎች በድጋሜ ተክቢር አሏሁ አክበር በማለት ለልጁ አድናቆታቸውን ገለፁ ። የሰዉየዉ ፊት ቢለዋወጥም ሶስተኛ ጥያቄውን ከማቅረብ ወደ ሗላ አላለም። ፊጣሪያችሁ ወደየትኛው አቅጣጫ ነው የዞረዉ? በማለት የመጨረሻ ጥያቄዉን አቀረበ።

ትንሹ ልጅ አሰብ አደረገና ሻማ ይዘዉለት እንድመጡ ጠየቀ በጥያቄው መሠረት ሻማ አቀረበለት እና አበራዉ ። ሰዉየዉ በዚህ ሻማ ደግሞ ምን ልታረጋግጥልን ነዉ በማለት አፌዘ።

ልጁም ይህ የሻማ መብራት ወደ የትኛው አቅጣጫ ነው የሚበራው ሲል ጥያቄዉን በጥያቄ መለሰለት ሰዉየዉ በሁሉም አቅጣጫ ሲል መለሰለት ልጁም የአላህ ኑር ብረሀን የትም ቦታ አለ።

@Alfaruq_islamic

እርሱ በእዉቀቱ ሁሉም ቦታ አለ እርሱ በእዉቀቱ የማይገኝበት ቦታ የለም ። በማለት መለሰለት የተሰበሰቡት ሰዎች በአጠቃላይ በተክቢራ ቦታዉን አቀለጡት ። ሰዉየዉም በልጁ መልስ በመገረምና ለጥያቄዎቹ መልሹን በማግኘቱ እስልምናን በመቀበል የልጁ ተማሪ ሆነ ።ይህ ትንሽየ ልጅ ማን ይመስላችኋል ?

ከመሪዎቻችን ከእስልምና ሙሁሮች አንዱ የሆኑት


#ትዕግስቴን__ወድጄለሁ!!


ከእለታት በአንድ ቀን አንድ ሰውዬ የቆሾሻ ልብስ ለብሶ ወደ አንድ ሆቴል ይገበል፤
ሆቴል ውስጥ ቁጭ ብሎ ትእዛዝ ስጠብቅ ከእሱ በኋላ የመጡ ሰዎች ትእዛዝ ቀድሞ በመምጣቱ ተገርሞ አሁንም ዝም ብሎ ይቀመጣል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ለግሩፕ ሆነው ጥሩ ልብስ የለበሱ ሴቶች እና ወንዶች አጠገቡ ቁጭ አሉ

እሱ ዝም ብሎ ቁጭ ብሏል እነሱ ግን እንደሱ ዝም ብሎ ቁጭ ማለት አልቻሉም፤
ይህ ሰውዬ ይኼን ቆሻሸ ልብስ ለብሶ እዚህ ቤት ውስጥ ምን ይሠራል?
እያሉ መሳቅ ሙድ መያዝ ቀጠሉ.....

አሁንም የሱ ትእዛዝ አልመጣም የልጆቹ ትእዛዝ ግን ቀድሞ መጣ።

በዚህ የተናደደ ሰውዬ ጥሎ ሊወጣ ሲል አስተናጋጁ ይመጣና ይቅርታ የኔ ወንድም የአንተ ትእዛዝ አሁን እየመጣ ነው
ትንሽ ጠብቅ ይላቸዋል

ሰውዬውም በል አፍጥን ሲል ይቅርታ ጌታዬ የርሷ ትእዛዝ ልዩ ትእዛዝ ስለሆነ ጊዜ ይወስዳል ደግሞ የርሷን ትእዛዝ የተቀበለ ሰው ሌላ ሰው ነው ብሎ ጥሎ ሄደ።

ሰውዬው በአስተናጋጁ ንግግር ተገርመው እሁን እኔ ምን ልዩ የሆነ ትእዛዝ ሰጣሁኝ? ከእኔ ትእዛዝ ተመሳሳይ የሆነ ትእዛዝ ከእኔ ቀድሞ እየመጣ አይደል ብሎ ግን ትእግስት ይሻላል ብሎ በትዕግሥት ጠበቀ።


ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ትእዛዙ መጣ
ነገር ግን ትእዛዙ የመጣው በአስተናጋጆች እጅ ሳይሆን በራሱ በሆቴሉ ባለቤት ነው።
ለከ የሆቴሉ ባለቤት ለሰውዬው የልጅነት ምርጡ ጓደኛው ነው
ትእዛዙ የቆየው የልጅነት ጓደኛው ምርጥ ምግብ ገብዞ ሰርፕራይዝ ለማድረግ ሽር ጉድ ሲል ነው።

አሁን እንደቅድሙ በሰዬው ላይ ማንም መቀለድ አልቻለም
አጠገቡ የተቀመጡ ቅድም የሳቁ ሰዎች ሁሉ እዚህ ቤት እንደዚህ አይነት ምግብም አለ ወይ እያሉ ሰውዬውን መድናቅ ጀመሩ
ፊቱን በሰውዬው ላይ አዞሩት
እንግዲህ ህይወት እንደዚህ ናት!
የት እና መቼ እድል ከህይወትህ ንጉሥ ሁሉንም ነገር ማድረግ ከሚችለው ደስ ያለህን ሁሉ ከሚሰጥህ ፈጣሪ ጋር ወስደህ እንደምተገኘህ አታውቅም ስለዚህ ሁሌም በትዕግሥት ጠብቅ።
አንድኣንድ ጊዜ ነገሮችን ቀስ ያሉትም ለበጎ ነው ብለክ አስብ!!


ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉ

𝐉𝐨𝐢𝐧 & 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
@Alfaruq_islamic
@Alfaruq_islamic
★∩∩∩∩∩∩∩∩∩∩∩★


ሳያነቡ እንዳያልፉ በስተመጨረሻ ሼር ያድርጉ

#የደሴቷ ብቸኛ ነዋሪ....
@Alfaruq_islamic

በርካታ ሰዎችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች አንዲት መርከብ በድንገት በተከሰተ ከባድ ማዕበል ምክንያት ባህሩ ውስጥ ትሰጥማለች። ከተሳፋሪዎቹ መካከል ታድያ በአላህ ተአምር አንድ ሰው ብቻ ይተርፋል። ይህም ሰው በውሃው እየተገፋ አንዲት ደሴት ላይ ራሱን ያገኘዋል።


እርዳታ ለመጠየቅ በደሴቷ እየተዘዋወረ ሰው ለማፈላለግ ቢሞክርም ምንም ዓይነት የሰው ዘር ማግኘት አልቻለም። በአካባቢው ማዕብሉ ከሚያናውጠው ባህርና ከወፎች ድምፅ በስተቀር የሚሰማ ነገርም የለም። በዚህን ግዜ በትንሽየዋ #ደሴት ውስጥ የሚኖረው ብቸኛው ሰው እርሱ ብቻ መሆኑን ሲያረጋግጥ በጣም ተጨነቀ። ፍርሃትም አደረበት። ከዚህ አስፈሪ ችግር ያወጣውም ዘንድ አላህን ለመነ።

አንዳች የአላህ ተዓምር መጥቶ ወደ ቤቱ የሚመለስበት ሁኔታ እስኪፈጠር ግን በደሴቷ ውስጥ መቆየቱ እንደማይቀር በማሰብም የሚጠለልበት ትንሽ ግዜያዊ ጎጆ ቤት ሰራ። አንገቱ ላይ ባንጠለጠለው ቦርሳ መሰል ይዞት የነበረውንም እቃ ጎጆዋ ቤት ውስጥ አስቀመጠ።

ወደ ጫካው በመግባትም የተለያዩ የሚበሉ ፍራፍሬዎችንና ቅጠላ ቅጠሎችን ማግኘት ቻለ። በዚሁ ሁኔታ በደሴቷ መኖር ጀመረ.....

ከዕለታት አንድ ቀን ምግብ ፍለጋ ወደ #ጫካው ሄዶ ሲመለስ ትንሿ ጎጆ ቤቱ በእሳት እየተቀጣጠለች ደረሰ። በተመለከተው አጋጣሚ በጣም አዘነ። የበለጠ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትም አደረበት።

"አላህ ሆይ! ለምንድን ነው እንዲህ ዓይነት ነገር የምትፈፅምብኝ!?" በማለትም በጣም አለቀሰ።

በተከታዬ ቀን የሆነ ድምፅ ከእንቅልፋ ቀሰቀሰው። ወደ ደሴቷ እየቀረበች የነበረች አንዲት መርከብ ናት ከእንቅልፋ የቀሰቀሰችው። መርከቧ እሱን ለመውሰድ ነበር ወደ ደሴቱ የመጣችው።

ሁኔታውን ማመን ያቃተው ሰውዬው "በዚህ አካባቢ እኔ መኖሬን ማን ነገራችሁ?" በማለት መርከቧ ላይ የነበሩትን ሰዎች ጠየቀ። እነርሱም "ትናንት ከዚህ አካባቢ የሚወጣ #ጭስ አይተን ነው የመጣነው" ሲሉ መለሱለት።
@Alfaruq_islamic

#አስተምህሮት.....

እኛ ሰዎች አጋጣሚዎች ሁሉ መጥፎ ሲሆኑብን በቀላሉ ተስፋ እንቆርጣለን። እንዲህ በቀላሉ መሸነፍ የለብንም። ምክንያቱም አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እኛን በተመለከተ ሁል ጊዜ ስራ ላይ መሆኑን መዝንጋት የለብንም። በመከራችንና በህመማችን ወቅትም እንኳ ቢሆን እርሱ አይረሳንም።



ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉ

𝐉𝐨𝐢𝐧 & 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
@Alfaruq_islamic
@Alfaruq_islamic
★∩∩∩∩∩∩∩∩∩∩∩★

Показано 4 последних публикаций.

156

подписчиков
Статистика канала