TIKVAH-MAGAZINE:
#ችሎት
ከሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ ወንጀል በተከሰሱ በእነ ሻምበል ማማር ጌትነት መዝገብ የሚገኙ 49 ተከሳሾች በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሽታ ምክኒያት ከሰኔ 22 ቀን 2012ዓ.ም ጀምሮ አስከ ሐምሌ 17 ቀን 2012ዓ.ም በተለያዩ የስራ ቀናት በመነጣጠል ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡
ሃምሌ 17 ቀን 2012ዓ.ም በዋለው ችሎት የምስክር አሰማምን በተመለከተ የትኛው ምስክር በየትኛው ተከሳሽ ላይ እንደሚመሰክር በመለየት ለፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 24 ቀን 2012ዓ.ም እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በእነ ሻምበል ማማር ጌትነት መዝገብ የሚገኙ አጠቃላይ ተከሳሾች 55 ሲሆኑ ከስድስቱ ተከሳሾች ወስጥ አራቱ ተከሳሾች ላይ የጋዜጣ ጥሪ መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡
https://telegra.ph/ANRSAG-07-25
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
10ሺህ የሚደርሱ ወገኖችን ለመደገፍ ጥረት እየተደረገ ነው!
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ግርግር ለተፈናቀሉ 7 ሺህ 800 ሰዎች የዕለት ደራሽ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ ዳመነ ዳሮታ አስታውቀዋል።
ኮሚሽኑ ድጋፉን እያደረገ ያለው ምግብና ምግብ ነክ ድጋፎችን ሲሆን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀትም እስከ 10ሺህ የሚደርሱትን ወገኖች ለመደገፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን ተነሱ!
የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ካይሬ ከስልጣን ተነስተዋል፡፡ ካይሬ ከስልጣን የተወገዱት የሀገሪቱ የታችኛው ፓርላማ አባላት ጠቅላይ ምኒስትሩን ከሥልጣን ለማንሳት የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በ170 ድጋፍ በ8 ተቃውሞ በመጽደቁ ነው፡፡
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ መሐመድ ሙርሳል "ጠቅላይ ምኒስትሩ ለፌድራል እና የክልል መንግሥታት የጸጥታ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅ ብሔራዊ የጸጥታ ኃይል ሳያዋቅሩ ቀርተዋል" ሲሉ ከሥልጣን የተነሱበትን ምክንያት አብራርተዋል።
ጠቅላይ ምኒስትሩ ከሥልጣን መነሳታቸው ከተረጋገጠ በኋላ መጪው የሶማሊያ ምርጫ በሚካሔድበት የጊዜ ሰሌዳ ጉዳይ በምክር ቤቱ ውዝግብ ተነስቷል። ሐሳን አሊ ኻይሬ የሶማሊያ ጠቅላይ ምኒስትር ሆነው ሥልጣን የጨበጡት የካቲት 2009 ዓ.ም ነበር። -#AlAin -#DW