የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ማስፈጸሚያ 62.7 ቢሊዮን ብር አጽድቋል፡፡ የተመደበው የበጀት መጠንም ከባለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ15.3 ቢሊዮን ወይም 32.4 በመቶ ብልጫ እንዳለው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ ገልፀዋል፡፡
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
የኮሪያ ጦርነት ያበቃበትን 67ኛ ዓመት በማስመልከት ንግግር ያደረጉት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ”በገነባነው አስተማማኝ እና ውጤታማ ራስን የመከላከያ ኒዩክለር ከዚህ በኋላ በዚህ ምድር ላይ ከማንም ጋር ጦርነት አይኖርብንም” በማለት ሀገራቸው ከየትኛውም ሀገር የጦርነት ሥጋት እንደማይኖርባት መግለጻቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ኮሪያ ሴንትራል ኒውስ ኤጅንሲ ዘግቧል፡፡ -#AlAin
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
የክረምት የችግኝ ተከላ መርኃግብራት!
በደቡብ ክልል በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በአንድ ጀንበር 60 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሀግብር ተካሂዷል፡፡ ዘንድሮ በክልሉ 1ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1ነጥብ 3 ቢሊየን ያህሉን ማሳካት መቻሉ ተነግሯል፡፡
በክልሉ በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ በተካሄደ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ የኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ እንደገለፁት ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ 5ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት 3ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች መትከል ተችሏል፡፡
በተያያዘ ዜና በኦሮሚያ ክልል ነገ ሀምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም 304 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። ክልሉ እስካሁን ከ2.3 ቢሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ኃብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ገልጸዋል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
በባህር ዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የነበሩ 1ዐዐ ታራሚዎች በይቅርታ መፈታታቸው ተገልጿል!
በባህር ዳር ከተማ ማረሚያ ቤት መደበኛ የይቅርታ መስፈርቱን ያሟሉ ወንድ 99 ሴት 1 በድምሩ 1ዐዐ ታራሚዎች በይቅርታ መፈታታቸው ተገልጿል፡፡ ታራሚዎቹ በይቅርታ መመሪያው መሰረት ተቋሙ የሚሰጠው እርምት፣ የትምህርት የስልጠና በአግባቡ የተከታተሉ ናቸው ተብሏል፡፡
በይቅርታ የተፈቱ ታራሚዎች በመደበኛ የይቅርታ መስፈርቱን ያሟሉ የህግ ታራሚዎች ሲሆኑ በፍርድ ላይ ያሉ መመሪያ ቁጥር 32ዐዐዐ/ 2010 መሰረት ያደረጉ ታራሚዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ውብሸት መኮነን መግለጻቸውን የክልሉ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
ካናል ፕላስ ከ50 በላይ ቻናሎችን ይዞ በኢትዮጵያ አገልግሎት ሊጀምር ነው!
የካናል ፕላስ የቴሌቪዥን ቻናል ከኢውቴልሳት ኮሚይኒኬሽን ጋር በመተባበር በቀጥዩ የፈረንጆች አመት ለኢትዮጵያውያን ተጠዋሚዎች በመደበኛና በከፍተኛ ጥራት ደረጃዎች የሚቀርቡ 50 ያህል ቻናሎችን ለማድረስ ዝግጅት መጀመሩን ቢዝነስ ዋየር የተሰኘው መካነድር አስታውቋል።
በመጠነኛ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ይቀርባሉ ተብለው የሚጠበቁት ከ50 በላይ የሚደርሱት ቻናሎች ለኢትዮጵያ የብሮድካስቲንግ ኢንዱስትሪን እንደሚያሳድግ የታመነ ሲሆን የካናል ፕላስ ሊቀመንበር የሆኑት ዣክ ዱ ፑይ ድርጅታቸው ወደገበያው በሚገባበት ወቅት ድርጅታቸው ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች የተሻለ አማራጭን ይዞ ይመጣል ሲሉ ገልጸዋል።
#AddisZeybe
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
#UPDATE
የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አቶ አረጋ ከበደን ለክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊነት በእጩነት አቅርበው ምክር ቤቱ በአንድ ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ የክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲሾሙ ወስኗል።
አቶ አረጋ ከበደ ለጋስ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በልማት አስተዳደር፣ ሁለተኛ ድግሪያቸውን በንግድ ሥራ አመራር በከፍተኛ ማእረግ እንዳጠናቀቁ ግለታሪካቸው በቀረበበት ወቅት ተነግሯል።በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይም አገልግለዋል ተብሏል።
ምክር ቤቱ የዳኞችን ሹመትም አጽድቋል። ለጠቅላይ ፍርድ ቤት 14 ዳኞች በአንድ ተቃውሞ፣ አራት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በሙሉ ድምጽ፣ 166 አዲስ የወረዳ ዳኞች በሙሉ ድምጽ ተሹመው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
#አብመድ